ethiox.com
ethiox.com
Donate!
web hosting service
SELECT command denied to user 'kcgvincw_fusion1'@'localhost' for table 'fusion_site_links'
Latest Links

  


  


  


  


  

Search

Enter Keywords:


እስላማዊ ማህበራት ለሙስሊሙ መብት መከበር ድምጻቸውን
Articlesእስላማዊ ማህበራት ለሙስሊሙ መብት መከበር ድምጻቸውን ያሰሙ       

የአልቁድስ ሳምንታዊ እስላማዊ ጋዜጣ አዘጋጅ አቶ ኢዘዲን መሀመድ በስም ማጥፋት ወንጀል በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጠቅላይ ጽህፈት ቤትና በሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ተከሶ ፍርድ ቤት ቀርቦ የአንድ አመት ጽኑ እስራት ተፈርዶበት ወህኒ በወረደ ጊዜ የጋዜጣውን መቀጠልና ቤተሰቡን የመንከባከቡን ሀላፊነት ተሸክሞ ሲተገብር የቆየው የአስራሰባት አመቱ ወጣት አክረም ኢዘዲን እሱም ልክ እንደ አባቱ በሥም ማጣፈት ወንጀል በአፋር መስጂድ ተከሶ አባቱ ከእስር በተፈታበት እለት በተራው ወደ እስር መላኩን ሰማን። ወጣት አክረም የታሰረው የአፋር መስጊድ እንቅስቃሴን የሚተች ጽሁፍ ጋዜጣው ላይ አትሟል በሚል ተወንጅሎ ነው። ወጣቱ የታሰረው ክስ ተመስርቶበትና በፍርድ ቤት ተፈርዶበት ሳይሆን በህገወጥ መንገድ ነው። ወጣት አክረም የተከሰሰበት ጉዳይ በነጻነት ሀሳብን የመግለጽ መብትን በሚደነግገው የፌዴራል ህግ በሚመለከተው ጉዳይ ቢሆንም ወደ እስር የተወረወረው ወደ ከሳሾቹ ግዛት ተወስዶ ነው።

እንግዲህ ከላይ የተጠቀሱትን ጉዳዮች በሙሉ ብንመረምር ወጣቱ ላይ የተወሰዱት እርምጃዎች በሙሉ ተገቢ አለመሆናቸውን እንመለከታለን። አንድ ጋዜጠኛ የአንድን ህዝባዊ ድርጅት አሰራር የመገምገምም ሙያዊ ግዴታ አለበት። የድርጅቱን አሰራር የማወደስም ሆነ የመንቀፍ መብቱ የተጠበቀ ነው። ትችት የቀረበበት አካል የቀረበበት ወቀሳ ተገቢ አይደለም፣ ህገ ወጥ ነው፣ በወቀሳውም ሳቢያ ተጎድቻለሁ የሚል ሀሳብ ካለውና ነገሩ በፍርድ ቤት እንዲታይለት ከፈለገ ክሱን ለፍርድ ቤት አቅርቦ ይሟገታል እንጂ በዘፈቀደ ማንንም የማሳሰር መብትም ሆነ ስልጣን የለውም። ደግሞም የመታሰር ነገር ቢኖር እንኳን ወጣት አክረም የተከሰሰበት ጉዳይ የዋስ መብትን የሚያስከለክል ስላልሆነ ከዚሁ ባላለፈ ነበር። ሌላው አስገራሚው ጉዳይ ደግሞ ወጣት አክረም ኢዘዲን አፋር ክልል ተወስዶ መታሰሩ ነው። ይህ ጉዳይ ህግን የተጻረረና እርምጃው በወጣቱ ህይወት ላይ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ ያላገናዘበ ነው።

እንግዲህ ለዚህ ሁሉ ኢሰባዊና ህገወጥ እርምጃ በዋነኛነት ተጠያቂው በከሳሽነት የተፈረጀው የአፋር መስጊድ ወይንም አዲስ አበባ ድረስ መጥተው ልጁን ወደ አፋር ክልል የወሰዱት ፖሊሶች ወይንም ወጣቱን ከቤቱ በህገ ወጥ መንገድ አስገድደው በመውሰድ ለአፋር ፖሊስ ያስረከቡት የአዲስ አበባ ፖሊሶች ናቸው ብሎ በደፈናው ለመናገር አይቻልም።  

ነብዮ መሃመድ ሶአወ በአደባባይ ሲዘለፉ፤ ቁርአን በአሳፋሪ መልኩ ሲዋረድና መስጊዶች በየቦታው ሲፈራርሱ ድምጻቸውን ያላሰሙት የአፋር መስጊድ ባለስልጣኖች አሁን ለምን ድክመታችን ተጋለጠብን ብለው በመቆጨት ክስ ማቅረባቸው አሳዛኛና አሳፋሪ ቢሆንም እነኝህ ሰዎች ማንንም ሰው በትእዛዝ ማሳሰር እንደማይችሉ ለማንም ግልጽ ነው። የአፋር ፖሊስም እንዲሁ ከፌዴራሉ ፖሊስ ይሁንታን ካላገኘ በስተቀር እንዲህ ህገ ወጥ በሆነ ሁኔታ ሰውን እንደ ላም እየነዳ ለመሄድ የሚያስችል ስልጣንም ሆነ የፖለቲካ ጡንቻ እንደሌለው ሁላችንም የምናውቀው ጉዳይ ነው። ፌዴራል ፖሊስ ደግሞ እንዲህ ያለው የሀገሪቱን ህገ መንግሥት የተጻረረ ተግባር ሲፈጸም በጣቶቹ መካከል ተመልክቶ በዝምታ ያለፈው ያለ ምክንያት አይደለም። ነገሩ በጥሞና ሲታይ የአክረም መታሰር የፍርድ ሳይሆን የፖለቲካ መልእክት ያዘለ ውሳኔ ነው የሚመስለው። ህዝበ ሙስሊሙን ሳይሆን ሥርአቱን እንዲያገለግሉ በመንግስት የተሾሙ የስርአቱ  አገልጋዮች ላይ ማንም ደፍሮ ደምጹን እንዳያሰማ ለማስፈራራት ሲባል፤ መስጊዱም እንዲከስ፣ ፖሊሱም አዲስ አበባ ድረስ ሄዶ ተከሳሹን ወደ አፋር በማምጣት እንዲያስር፣ የአዲስ አበባውም ፖሊስ ወጣቱን እንዲያስረክብ ከበላይ የተላለፈ መመሪያ ሳይኖር አይቀርም ብሎ መጠርጠር መስመር ዘለልነት አይደለም።

ሌላው በጣም አስገራሚውና አስደማሚው ነገር ደግም እዚህ በዲያስፖራ የሚገኙትና ለሙስሊሙ ሰብአዊ መብት መታገል ከተመሰረትንበት አላማዎች መካከል አንዱ ነው በማለት ያወጁት፤ እንደ በድርና በአወሮፓ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ኔት ወርክን የመሳሰሉት እስላማዊ ማህበራት በዚህ ጉዳይ ላይ ድምጻቸውን አለማሰማታቸው ነው። እርግጥ ነው የአክረም ኢዘዲን መታሰር ሙስሊሙን ብቻ ሳይሆን ጠቅላላውን ለሰብአዊና ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት መከበር እንታገላለን የሚሉ አካላትን በሙሉ የሚመለከት ጉዳይ ነው። ሆኖም ግን ክርስቲያኑ ወገን ላይ እንጂ ሙስሊሙ ኢትዮጵያዊ ላይ ለሚደርሰው በደል ደንታ የሌላቸው በኢትዮጵያዊነት ሥም የሚንቀሳቀሱት በመቶዎች የሚቆጠሩት ክርስቲያን - ወገን ሚዲያዎችና ማህበራት ታዳጊ ወጣት አክረም ኢዘዲን ላይ ለተፈጸመው ህገወጥ ተግባር ትኩረት ባይሰጡት የተለመደ ነውና አይገርምም፤ ነገር ግን ሙስሊም - ወገን ነን የሚሉት ማህበራት ጉዳዩን አስመልክቶ መግለጫ የመስጠትን ያህል እንኳ ተራ ነገር ማድረግ ሳይችሉ መቅረታቸው በጣም የሚያሳስብ ጉዳይ ነው፡፡ ወጣት አክረም ኢዘዲን ላይ የተፈጸመው ድርጊት ህገ ወጥ፣ ኢሰባዊና ኢትዮጵያ የፈረመችውን የልጆችን መብት የሚደነግገውን የተባበሩት መንግስታት ህግ የጣሰ ነው። ይህም በመሆኑ እነኝህ በዲይስፖራ የሚገኙት እስላማዊ ማህበራት ቢያንስ በወጣት አክረም ኢዘዲን ላይ የደረሰውን ኢፍትሀዊ ድርጊት የሚቃወሙ መሆናቸውን ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላትና እንደ አምነስቲ፣ ዩኒሴፍና ለጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅቶች እንዲያውቁት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል እንላለን። አላሁ አለም!   
         
 

Radio Negashi

http://radionegashi.ethiopianmuslims.net/index.php?option=com_content&view=article&id=188:2010-10-26-17-59-25&catid=44:analysis&Itemid=59


posted on 0 Comments · 5427 Reads · Print
Comments
No Comments have been Posted.
Post Comment
Please Login to Post a Comment.
Ratings
Rating is available to Members only.

Please login or register to vote.

No Ratings have been Posted.
Special Links

Login
Username

PasswordNot a member yet?
Click here to register.

Forgotten your password?
Request a new one here.
Latest Articles
Ethiopia(ጋ&#48...
Manipulating Aid
An Ethiopian Scholar...
Somali Investment in...
Message from Maakelawi
Search

Enter Keywords: