ethiox.com
ethiox.com
Donate!
web hosting service
SELECT command denied to user 'kcgvincw_fusion1'@'localhost' for table 'fusion_site_links'
Latest Links

  


  


  


  


  

Search

Enter Keywords:


ማን ያቸንፋል፤ Colts versus Saints?
Amharicማን ያቸንፋል፤ Colts versus Saints?ሽጉጦች ወይስ ቅዱሶች? እምነት ወይስ ሀይማኖት?

ከኦቦ አራዳ ሻውል 3-3-10

መግቢያ


በአንድ በኩል፣ በስሜ ልጠራ፤ መፍትሔ ከደብተራው ጋራ በሚል ርእስ ስጽፍ ሰነባብቻለሁ፣ ሆኖም አመርቂ የሆነ ነቀፌታም ሆነ ምስጋና አላገኘሁበትም አግኝቸ ከሆነም አላውቀውም።
ጽሑፌ ያተኩር የነበረው በምሁራኖች በተለይም በኣካዳሚያ ማዕረጋቸው ብቻ ለመጠራት የሚሽቀዳደሙ እንደነ ዶ/ር፣ አንጂነር፣ ኤኮኖሚስት ወዘተ ነኝ እየተባባሉ ሞያውንና ጥበቡ ሳይኖራቸው በንድፈ ሐሳብ (ቴዎሪ) ብቻ እየተነዱ ከመፍትሔ ይልቅ ሙግትን የሚያስቀድሙ ግኡዝ ምሁራንን ከጽንሐተ ምሁራን (ረሰርቸርስ) አጋር በመሆን በኤትዮጵያ ምድር ለሚደረገው የሥርዓት(Eway Revolution) ለውጥ ይረዳል ከሚል በጎ አስተሳሰብ የመነጨ ነበር። ነውም።በሌላ በኩል ደግሞ ዘመኑ እየተቀያየረ ስለሆነ መረጃ ኢንፎርመሽን ብቻውን ብቁ ስላልሆነ ማለት ጊዜው ያለፈበት ስለሆነ በእውቀትና በጥበብ መራመድ ስለአስፈለገ ለዚሁም የሚረዳ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ስለሆነ በእንግሊዝኛው ቋንቋ ቢጻፍ ለአሁኑና ለመጪው ትውልድ ጠቀሜታ ይኖረዋል በሚል ግንዛቤ ነበር።በተጨማሪም መዝገበ ቃላቶቻችን ለማሳደግ።


በሽጉጦች ወይስ በቅዱሶች?

በዚህ ጽሑፌ የዛሬ ሶስት ሳምንት እሁድ ቀን ማለትም እንደ ኮዔ አቆጣጠ 02-07-10 ስለተደረገው 44ኛው (XLIV) የሱፐር ባውል ፉትቦል አስመልክቶ ነው። በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ ወደ 107 ሚሊዮን ገደማ የቲቪ ፐሮግራም ተመልካች የሳበ ጨዋታ ነበር።በዚሁ ጨዋታ ሳቢያ ምክንያት አባቶች ያስተላለፉልን አስተሳስብ (የሚታረመውን አርመን?) ለመጪው ትውልድ ትምህርት ይሆናል ብዬ ስለ አሰብኩ እነሆ መልእክቱ እንደሚከተለው ቀርበዋል። የዛሬ አርባ ዓመት ገደማ ለሥራ ጉዳይ አሥመራ ሄጄ ስለ ነበር አባቴ በጦርነቱ ምክንያት ከዓዱ (አገሩ) ተፈናቅሎ አሥመራ ከተማ አገኘሁት። በጊዜው የጠየቀኝ ጥያቄ እንዲህ ነበር። ራዲዮን ሲያወራ አንድ ሰው በደረቱ ድንጋይ ያስፈልጣል፤ ምላጭ ይበላል፤ አሜሪካኖች ጨረቃ ላይ አረፉ የሚል ነበር። ምንም መልስ ሳልሰጥ ይህ ሁሏ ውሸት ነው ብሎ ሲጨርስ እነሆ አሁን ደግሞ የውንድሜ ልጅ ጀሆቭሀ ሆነዋል መሰለኝ መስቀሉን አይሳለምም ያለው አንትስ ብሎ መስቀሉን ሲያወጣው ቶሎ ብዬ መስቀል በእንቲአነ ፤መስቀል ቤዛነ እያልኩ ስሳለም ያለ ቃለ-አጋኖ ጠፍተው የነበሩ ዓይኖቹ በሩ። የመጨረሻ የተሰናበትኩት በዚሁ ሁኔታ ነበር።ነገሩ እንዲህ ነው። ድንጋይ የሚስፈልጠው ሰውዬ በደሴ ከተማ በአንድ ሆቴል ውስጥ ተከራይተን ነበር። ካራንቡላችንን ከተጫወትን በኋላ ድንጋዩን በደረቱ አስፈልጦናል። የጨርቃ ጉዳይም በኪሴ መጽሔት ይዣለሁ ፤ የሰው ልጅ ጨረቃ ላይ አረፈ የሚል ሽፋን ነበረበት።ይህ ሁኔታ በእምነት ወይም በሃይማኖት፤ በሰላም ወይም በግጭት ወይም ደግሞ በሌላ የቅራኔ አፈታት ተመልክታችሁ መልሱ ለእናንተ አንባቢያን እተወዋለሁ።ይህንን ታሪክ ለልጄ ስነግረው በፍጹም ትርጉም የለሽ ይሆንበት ነበር እስከ አለፈው የ44ኛው (XLIV) የሱፐር ቦል ጨዋታ ድረስ።የፉትቦል ሙሉውን ጨዋታ ለመጀመሪያ ጊዜ ከልጄ ጋር ሆኘ አየሁት። ልጄ ጨዋታው ሳይጀመር ማን ያቸንፋል ብሎ ጠየቀኝ።ልጅ ማን ያቸንፋል?

አባት፡ ማንና ማን ናቸው?

ልጅ፡ Colts against Saints (ኮልትsና ሰይንትስ)አባት፡ ይኸማ ምን ይጠየቃል፤ ቶሎ ብዬ ሰይንትስ አልኩትልጅ፡ ለምን?አባት፡ ከሽጉጥና ከመስቀል ማን ያቸንፋል ትለኛለህ? ለነገሩ አንተ ጴንጤ መሰልከኝ፤ ነህ እንዴ?ልጅ፡ ብሆንስ?አባት፡ በመስቀሉ አታምንማ!ልጅ፡ መላእክት መስቀል ይሸከማሉ እንዴ?አባት፡ ታድያ ሽጉጥ የሚታጠቁ ይመስለሀል?ልጅ፡በፈገግታ በችሎታ ከሆነ፣ ባለሽጉጦች ነው የሚያሸንፉት አንተ በምትለው ግና ቅዱሳን ናቸው የሚቀናቸው ለነገሩማ እኔም የሰይንትስ ደጋፊ ነኝ ብሎኝ አረፈ።በመጨረሻው ውጤቱ እንደተጠበቀው ሆኖ፤ በእረፍት ጊዜ 10-3 በሆነ ውጤት አለቀ። በ13 የተለከፍኩ መሆኔን ልጄ አውቆ ኖረዋል መሰል በውጤቱ ሳይገረም የቀረ አይመስለኝም። J=10 : C=3 JC=13= Jesus Christ ብለህ አይደል የምትዘረዝርው ብሎ አስደነገጠኝ። ልጄ እኔ የምጽፈው ሆነ የምሰራው የሚያውቅ አይመስለኝም ነበር ምክንያቱም የአሁኑ ዘመን ልጆቻችን እኛ እናውቃለን፣ እናንተ ሽማግለዎች ምን እንደምትሉና እንዴት እንደምታስቡ ግራ ስለሚያጋባ ነው እያሉ ከወላጆቻቸው ስለሚርቁ አውቅ ስለ ነበር ነው።ለማነኛውም መደበኛ ጨዋታው ካለቀ በኋላ ሰፋ ባለ መንገድ ስለ የአሜሪካ ፉትቦል ጨዋታ አስረዳኝ። ከዝርዝሩ ባጭሩ እነሆ ድሪው ብሪስ የሚባለው አቀባባይ ተጫዋች (Quarterback) ቀደም ብሎ ለሳንዲያጎ ቻርጀር ሲጫወት የሚወረውርበት እጁ ተጎዳ።በዚሁ ምክንያት የፉትቦል ሙያው ተበላሸ ተብሎ ተገመተ። የሚቀጥረውም ጠፋ። ነገር ግን አላባማ ስቴትስ ሄዶ የእጅ ጥገና አደረገ።የእግዚአብሔር ጉዳይ ሆኖ በሌላ በኩል ደግሞ አሠልጣኙ ሺያን ፐይተን (Coach) ለመጀመሪያ ጊዜ የአሥልጣኝነት ቦታ ተሰጥቶት የቅዱሳት (saints )ቡድን አሠልጣኝ (coach) ሆኖ ተቀጠረ። አሠልጣኙ ብሪስን እኔና አንተ ሆነን ይህ የወደቀ ቡድንና በካቴሪና ምክንያት የወደቀ እስቴት ከወደቀበት እናንሳው ተባብለው እነሆ ከአራት ዓመት በኋላ ለዚህ ታላቅ ድል በቁ። ብሎ አስረዳኝ።በ2009 ውድድር ሲጀምሩ 13 ጨዋታ በማቸነፍ ለጥሎ ማለፍ አንደኛ ሥፍራ ይዘው ነው ያለፉት።

እንግዲህ ብዙዎቻችሁ እንዳያችሁት በመተማመን ብሪስ የተናገረው እንዲህ የሚል ነበር።ይህ የእግዚአብሔር ጥሪ ነው። የሕጻን ልጁ ዓመት በዛው ዕለት ስለዋለ ብሪስ ልጁን በማቀፍና በመሳም አከበረ። የኒው ኦርሊንስ ከተማም ፈነደቀች። ካተሪና ተቸነፈች፤ ዓለምም ትምህርት አገኘች።በሰይንትስ ቡድን፣ በገልፍ ባሕር ሰላጤ እና በኒው ኦርሊንስ ከተማ ውህደት ተፈጠረ። ተስፋ፤ ህልም እና ትግል ተቀናጁ። ኤትዮጵያም ከምትከተለው ብልሹ ሥርዓት የሚያድናት ይኖር ይሆን? ማን ያውቃል?

በእምነት ወይስ በሀይማኖት?

መስቀሉ ምንን ያመለክታል? ለምንስ በኤትዮጵያ ወሎ ክፍለ ሀገር ውስጥ ለምን ቁራጩ አለ? የጉራጌ ብሔረ ሰብስ ለምን መስቀልን በከፍተኛ ደረጃ ሊያከብረው ተነሳ? መስቀል የሚጠላ ወይ የሚፈራ ነገር ሆኖ ነው? ወይንስ ጌታ ሲሰቃይ ላለማየት በሚል ሰበብ ነው? እኔ አላውቅም።

ጆሆቫዎቹ መስቀልን እንደ ሽጉጥ ነው የሚያዩት ማለትም የግድያ መሳሪያ ብለው ስለሚቆጥሩት አያምኑበትም። ጰንጤዎቹ ደግሞ መስቀል የሃይማኖት ጉዳይ ስላልሆነ በቀጥታ እየሱስን ማግኘት ስለሚቻል መስቀሉ የመገናኛ መሳሪያ አይደለም ይላሉ።በሌላ አነጋገር እየሱስ ሲነሳ እንጂ ሲሞት ማየት ይሳናቸዋል። የአሁኑ ወጣት ኤትዮጵያዊ ፖለቲከኛ ዓይነት፣ ስለ አሳለፋችሁት ስቃይ አትንገሩን ባዮች።

እንደነ አባቴ እምነት ከሆነ ግና መስቀሉ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ለማስተማርና ለማዳን አንዱ ልጁን ልኮ በእኩያን ሰዎች ሲሰቃይ በዓይናችን አይተን ሁሌም አምላክን እንድናስታውሰው እና እንዳንረሳው ይመስለኛል።

በተጨማሪም ለእንደነ አባቴ ቀይ፣ብጫ፣ እና አረንጓዴ ሰንደቅ የቤተ ክርስቲያን አርማ እንደመሆኑ ልክ እንደ መስቀሉ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ለመግባት የሚጠቀሙበት የመገናኛ መሳሪያቸው ነበር እንጂ እንደአሁኑ ፖለቲከኞች ባንዴራ የኔ ነው ያንተ አይደለም እያሉ ሕዝብ ከሕዝብ የሚያፋጅ መሆን አልነበረበትም።

በእኛ አብዮት እምነት ከሆነ ደግሞ እንደሚከተለው ይሆናል።

የኤትዮጵያ አብዮት የመሩት ጓዶች የኢየሱስን ትምህርታዊ አካሄድ ሲያስተምሩ ሊሰቃዩ እንደሚችሉ እያወቁ ትግሉን ለኤትዮጵያ ሕዝብ ሲሉ ተሰውተዋል። ነገር ግና በአሁኑ ጊዜ እንደ ሞኞች እየተቆጠሩ ይገኛሉ እንዲያውም አልፎ ተርፎ መቀጣት አለባቸው የሚሉም አሉ። የዚሁ አቀንቃኝ የሆኑ አንዳንድ የጴንጤ ተከታዮች እኛ ብቻ ነን የትግላችሁን ፍሬ መብላት ያለብን እያሉ ይገኛሉ። የክርስቶስ መሰቀልና መነሳት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ መሆናቸውን ይረሳሉ። በዓለማዊ አነጋገር የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ አባባል ነው።


አስተሳሰብ/ውይይት

ደብተራው ሀይማኖተኛ ነበር? ብለው የሚጠይቁኝ አሉ። መልሴ የለም አማኝ ነበር ስላቸው ክሬዚ ብለው ይተዉኛል።

ብዙ ጊዜ ሰዎች ኤትዮጵያውያን ሀይማነተኞች ናቸው ብለው ሲገልጹልን እሰማለሁ። በእኔ አስተያየት ግና አይደለንም ነው። ብዙ ኤትዮጵያውያን መጽሐፍ ቅዱስ ላለማንበብ ዋና ጉዳያቸው አድርገውት ነበር። ክርስቶስ ባስተማረው ትምህርት ላይ ብቻ እያተኮርን በባሕላዊና በኦርቶዶክሳዊ ቤተክርስቲያን አስተምሮ እንድናተኩር ሆነናል። ይህ መጥፎ ነገር ነው ወይስ ሸጋ ጉዳይ። እንወያይበት።

ለመሆኑ በሀይማኖትና በእምነት ያለው ልዩነት ምንድን ነው?

በእንግሊዘኛ መዝገበ ቃላት ብዙ ዝርዝር መግለጫ አለ። የተፈጥሮ ሀይማኖት፣ የተዋሕዶ ሀይማኖት፣ የራዕይ ሀይማኖት፣ የአይሁድ ሀይማኖት፣ የጣዖት ሀይማኖት፣ የኤትክስ ሀይማኖት የመሳሰሉት ሁሉ ይገኛሉ።

እነዚህ ሀይማነቶች ከእምነት ጽንሰ ሓሳብ ጋር ተቃራኒ ናቸው።

እምነት እምነት ነው። ፌዝ=ብሊፍ (Faith-Belief) የግል ነው።አንድን ግለ-ሰብ ጥንካሬው የሚለካው በዚሁ ነው። ሀይማኖት ግና ብዙኋን ተሰባስበው በአንድ ላይ ማመንን ይለዋል።

ሀይማኖት የሚያስፈልገው እምነትን ለመቐጣጠር ነው። እምነት ደግሞ በበኩሉ ሀይማኖትን ለመግታት ነው። በሌላ አነጋገር ሀይማኖት የሰው ልጅ እግዚአብሔርን ለማግኘት (Reach Out) የሚያመላክት ትርጓሜ ሲኖረው እምነት ግና እግዚአብሔር መቀበልን ያመለክታል።

አሁንም በሌላ አነጋገር እምነት የመጨረሻ ግብ አይደለም። በቀላሉ አማርኛ እውነት የአእምሮ ቅበላ ጉዳይ ነው።

ሀይማኖት ግዳማዊ (ውጫዊ) ነገር ነው። እምነት ደግሞ እኛኑ ምንነታችንን የሚገልጽ ይሆናል። ሀይማኖት እምነታችን የምንገልጽበት ባሕላዊ ልምዶችን ይጨምራል።

እምነት የእውነትን መሰረታዊ ግንዛቤያችን ነው። ዓለምን በምን መነጸር እንደምንረዳት፣ ለየትኞቹ እሴቶች ቅድሚያ እንደምንሰጣቸው፣ የትኞቹ ቅዱሳት፣ የትኞቹስ ሀቅ ወይ ውሸት፣ ምንስ ለማግኘት ብለን ነው የምንኖረው ለሚለው ሁላ መፍትሔ ሰጪ ነው።

እንደ እኔ ከሆነ የኤትዮጵያ ተዋሕዶ ክርስቲያን ሀይማኖት አይደለም ምክንያቱም የሰው ልጅ ሙከራው ወደ እግዚአብሔር ለመድረስ የሚያደርገው ጥረት ሳይሆን እግዚአብሔር ራሱ ለሰው ልጅ እንደሚደርስ እምነተ-ኤትዮጵያውነት ስለሆነ ነው።

የኦርቶዶክስ እምነት በግል የተመሰረተ በፈጣሪው (እግዚአብሔር) እና በተፈጠረው የሰው ልጅ የሚያተኩር ስለመሆኑ ይመስለኛል።

የኢየሱስ ክርስቶስ ጉዳይም በሕይወት-በሞትና በመነሳት ያለ ክስተት ስለሆነ ኤትዮጵያውያን ወድቀው እንደሚነሱ እሙን ነው።


በአሁኑ ጊዜ ምን መደረግ አለበት?


መስቀል ምንድን ነው? ለክርስቲያን ሕዝብ ምንን ያመለክታል? ባለፈው ሳምንት ለምሳሌ የአሜሪካን ም/ፕረሲደንት ሚስተር ጆ ባይደን በግንባራቸው አመድ ተቀብተው በጋዜጣ ታይተዋል። አመዱ የመስቀሉ ሳይሆን አይቀርም፣ አቶ ባይደን የካቶሊክ ተከታይ ናቸውና።

አባቴ መስቀሉን ያሳለመኝ ዋናው ምክንያት መስቀሉ ቃል በቃል ሊያድነን ሳይሆን በምግባራችን እንደ ምልክት/አርማ ማለት እንደ ባንዲራ በየዕለቱ የሰው ልጅ ችግርን መቋቋም እንደሚያስፈልገው ክርስቶስም በመስቀሉ ምክንያት መሸከምም ሆነ በመስቀሉ እንደ ሰው እንድናውቀው ተብሎ ነው። አሁን በፊልምና በቴሌቭጅን እንደሚያሳዩን ዐይነት።

በኤትዮጵያ ኮሚኒቲ አካባቢ የአቶ ሀይለ ገሪማንና የአቶ ዓሊ ሁሴን የስቃይ ፊልም እያየን ነው። ከፊልሙ እየተማርን ነው ወይስ እያመን? መልሱ ለአንባቢያን።

እኔ ደግሞ ከአባቴ በሳይንስ ሂሳብ አስቤ ላለመጣላት ለመግባባት ስል ዝም ብዬ ስለ ድንጋይ አስፈላጩና ጨረቃ ላይ ማረፍ ልከራከረው አልፈልግሁም፣ በጊዜው አያስፈልግም ነበር።

ያሁኑ ልጄ ጴንጤ ነህ ስለው ብሆንስ ማለቱ መብቱ ነው። ልታስተምረኝ አትችልም ልትመርጥልኝ አትችልም የሚል ስለሆነ ለማብራራት አልፈለግኩም። አያስፈልግም። ሀይማኖት የግል ነው አገር ግና የጋራ ነው ተብሎ የለ።

መደምደሚያ

ኤትዮጵያውያን በምን ምክንያት ነው ሊስማሙ ያልቻሉት ለሚለው ጥያቄ እንደሚከተለው ለምግለጽ ተሞክረዋል።ጽንሰ ሐሳቡ የተወሰደው ከሪክ ዋረን (በፕረሲደንት ኦባማ ምረቃ ጊዜ ቃል-ቡራኬ የሰጡ ቄስ ናቸው) መጽሓፍ ነው።

አንደኛ፤ በጥፋታቸውና በፀፀታቸው ምክንያት ከጥፋታቸው እየሸሹ ወይም ከአፍረታቸው እየተደበቁ ይገኛሉ ይላል። በአሁኑ ጊዜ በርከት ያሉ ኤትዮጵያውያን ደግሞ በፀፀትም በአፍረትም ምክንያት ነገሮችን እያባባሱ ናቸው ።

ሁለተኛ፤ በይቅርታ ጥላቻቸውንና ንዴታቸውን እንዳያበርዱ እየደጋገሙ ባለፈው ጊዜያቸው ሁኔታቸውንና ድርጊታቸው በጭንቅላታቸው ተሸክመው በውስጣቸው እያረሩ ወይም እንደ ቦንብ እየፈነዱ ናቸው ይላል።በጥላቻና በንዴት ስለሚነዱ ኤትዮጵያውያንም በብዛት አሉ።

ሶስተኛ፤ በፍርሃት እየተነዱ አስከፊ ሙከራ፣ ያልጠበቁት ሁኔታ፣በእምነትና በፍቅር ወደፊት መራመድ ስለአቃታቸው ነው ይላሉ ቄስ ዋረን።

ኢሕአፓ ፍትህ ለማስገኝት ብሎ ብዙ አባሎቹና ደጋፊዎቹ ስቃይ ስለደረሰባቸው ፤ ኤርትራዊያን አርነታቸውን ለማግኝት ሲባል ብዙ መስዋእትነት ከፈሉ፤ ነጻነታቸው ካገኙ በኋላ ደግሞ ያልተጠበቀ በባድሜ ጦርነት ሳቢያ ብዙ ዘመድ አዝማድ ስለተሰዋባቸው። ብዙ ኢትዮጵያውያን ቀይ ባሕር የኛ ባሕር ነው ብለው እምነት ስለነበረባቸው ቀይ ባሕርን ለማስጠበቅ ሲሉ ብዙ ብዙ መስዋእት ከፍለዋል። በዚሁ ሳቢያ ፍቅርና እምነት ስለጠፋ ብዙ ኤትዮጵያውያን ችግር ላይ ናቸው።

አራተኛ፤ በፍቅር ንዋይ ለተጠመዱ እድሜያቸውን ሙሉ ለመበልጸግ ብዙ ደስታ ለማግኘት፤ ብዙ ሀብት የበለጠ ደህንነት ስለሚሰጣቸው ስለፈለጉ። ስግብግብነት ብቻውን ጊዜያዊ ደስታ መሆኑን ስለማይገነዘቡ ፤ ለራስህ ዋጋ መስጠትና ለንብረትህ ዋጋ መስጠት ልዩነት እንዳለው ስለማያውቁ ብዙ ችግር ውስጥ ይዘፈቃሉ ይላሉ ቄስ ዋረን። በእኛ አገር ደግሞ፤ ለምሳሌ የወያኔ መሪዎችን አርአያነት ይመለከተዋል።

አምስትኛ፤ መፍትሔው ከእግዚአብሔ ጋር ግንኙነት ሆኖ ሳለ ፍላጎቻቸው የተመሰረተው ሁሌም በሌሎች አለኝታ ስለሚሆን ክፍተኛ ችግር ይገጥማቸዋል።ቄስ ሪክ ዋረን በኣላማ ላይ ያተኮረ ሕይወት በሚል መጽሀፋቸው እንደ መፍትሔ ገልጸውታል።

እንደዚሁም በእኛ ኮሚኒቲ ብዙ ሕዝብ ወገንተኛነትን ሲያጠቃው ይታያል።ምናልባትም ከእምነት ወይ ከሀይማኖት ጉድለት ሳይሆን አይቀርም በሚል ተስፋ ይህንን ለውይይት አቀረብኩ። ከዕውቀት ማነስ ከሆነ ደግሞ ይቅርታ እጠይቃለሁ።


ጥያቄ ወይም አስተያየት ካላችሁ woldetewolde@yahoo.com


posted on 0 Comments · 6479 Reads · Print
Comments
No Comments have been Posted.
Post Comment
Please Login to Post a Comment.
Ratings
Rating is available to Members only.

Please login or register to vote.

No Ratings have been Posted.
Special Links

Login
Username

PasswordNot a member yet?
Click here to register.

Forgotten your password?
Request a new one here.
Latest Articles
Ethiopia(ጋ&#48...
Manipulating Aid
An Ethiopian Scholar...
Somali Investment in...
Message from Maakelawi
Search

Enter Keywords: