Author Topic: Finote Democracy ፍካሬ ዜና ሐምሌ 7 ቀን 2010 ዓ.ም  (Read 2750 times)

staff3

  • Global Moderator
  • Newbie
  • *****
  • Posts: 260
#Finote Democracy ፍካሬ ዜና ሐምሌ 7 ቀን 2010 ዓ.ም. 14 July 2019 Weekly NEWS SUMMARY)
##ርዕሰ ዜና##ኢህአዴግ የተባለው የወያኔ  የዘር አገዛዝ ጭምብል የመንኮታኮቱ የመጨረሻው ምዕራፍ መጀመሩ በገዛ እጁ ተጋለጠ #አሜሪካ፣ ከዘረኛው አገዛዝ ጋር ወታደራዊ ልምምድ ለማድረግ መወሰኗ አነጋጋሪ መሆኑ ታወቀ #ኦህዴድ/ኦዴፓ የሕዝብን ሰላም በወረበሎች እየበጠበጠ መሆኑ ተጋለጠ #ዘረኛው አገዛዝ ዜጎችን እያፈሰ ማሰሩን መቀጠሉ ተሰማ #ለሲዳማ ጥያቄ ዘረኛው አገዛዝ ምላሽ ባለመሰጠቱ ቀውስ ሊከሰት ይችላል የሚል ሰጋት ማሳደሩ ተሰምቷል #የዘረኛው አገዛዝ ጦር ቃል­አቀባይ፣ ትችት በጦሩ ላይ እንዳይሰነዘር ማስጠንቀቁ አነጋጋሪ መሆኑ ተነገረ ##ዝርዝር ዜናዎች#

#ኢህአዴግ የተባለው የወያኔ  የዘር አገዛዝ ጭምብል የመንኮታኮቱ የመጨረሻው ምዕራፍ መጀመሩ በገዛ እጁ ተጋለጠ

 ባሳለፍነው  ሳምንት፣  ህወሓት  የዘረኝነት መርዝ  እየጋተ  ላሳደገው  በቅርብ  ጊዜ አዴፓ  መሆኑን  ለለፈፈው ቡችላው ማስጠንቀቂያ ማሰማቱን ተከትሎ ከባህር ዳርም የአጸፋ ምላሽ መሰጠቱ የጋብቻ ሰነዳቸው ነትቦ እየተቦጨቀ ለመሆኑ ማሳያ  ነው ተብሏል፡፡  ይህ  አሁን  አዴፓ  ነን  ያለው  ቡድን  ህወሓት  ሲመሰርተው  ኢህዴን የሚል  ስያሜ  ሰጥቶት እንደነበር  የሚታወስ መሆኑን  የሚያነሱ ወገኖች  እንደሚሉት ቡድኑ  የተመሰረተው  በኢሕአፓ  አንጃዎች  እንደነበርና የኢሕአፓ አገር አቀፋዊ እንቅስቃሴን ለማኮላሸት ታስቦ እነደ ነበር ያስረዳሉ፡፡ የዚህ ኢሕዴን የተባለ የህወሓት ቡድን የአማራ ወጣት ገበሬዎችን በኢሕአፓ አባልነት እያሰቃየ መግደሉ፣ ኋላም በኢሕአፓ አመራሮች በእነ ጸገየ­ደብተራው እና በሌሎች ኢሕአፓዎች መታፈንና ደብዛቸው መጥፋት ቀጥተኛ የወንጀሉ ተሳታፊ እንደነበር በርካቶች ያስረዳሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም  ሱዳን  ተሰደው  የነበሩ  የኢሕአፓ  አባላትን  እያሳፈነ  የገደለ  አረመኔ ድርጅት  መሆኑ  ሊሸፈን አይገባውም እየተባለ ነው፡፡ ይህ ድርጅት ብአዴን ወደ እሚለው ስያሜ እንዲቀየር የተደረገው በሟቹ አረመኔ መለስ ዜናዊ ቀጭን ትእዛዝ መሆኑም በስፋት የሚታወቅ ነው፡፡ ብአዴን የሆነበት ከ1984 ዓ.ም አንስቶ በአማራው ሕዝብ ላይ  በኦነግና  በህወሓት  የተከፈተውን  መጠነ  ሰፊ  የጥፋት  ዘመቻ ለመመከት በስመ­ጥሩ  ሀኪም  ፕሮፌሰር  አስራት ወልደየስ የተቋቋመው የመላው አማራ አንድነት ድርጅት (መኢአድን) እንቅስቃሴ ለማሽመድመድ የተቋቋመ መሆኑና በአርባጉጉ እና በበደኖ ለደረሱት ጭፍጨፋዎች ኢህዴን/ብአዴን ከሌሎቹ ከህወሓትና ከኦነግ ጋር በወንጀሉ ተጠያቂ ነው  እየተባለ  ነው፡፡  ከዚህም  በላይ  በአማራ  ሕዝብ  ላይ የተለጠፉበትን  “ነፍጠኛ፣  ትምክህተኛ፣  …ወዘተ”  የሚሉ የስድብ ውርጅብኞችን በአማራ ሕዝብ ላይ ሲያወርድ የነበረ በመሆኑ የቡድኑ ቁንጮዎች ለሕዝባዊ ፍርድ መቅረብ ይገባቸዋል  የሚል  አሰተያየት  እየተስተጋባ  ፣  መሆኑን  መረዳት  ተችሏል፡፡ ይህ  ቡድን  የዛሬ  አንድ  አመት  ግድም ስያሜውን  አዴፓ  የማድረጉ  ሚስጥርም ያለፈ  ታሪኩን  እንዳይነሳ  የቡድኑ  ቁንጮ  አመራሮች  እነደመቀና  ደጉን የመሳሰሉ ከሕዝባዊ  ፍርድ  ነፃ  እንዲሆኑ  ታስቦ  የተደረገ መሆኑን  የፖለቲካ  አዋቂዎች ያስረዳሉ፡፡ አዴፓ  የተባለው ቡድን በመግለጫው ወያኔ ከተመሰረተበት አንስቶ በአማራ ሕዝብ ላይ የጥፋት ነጋሪት መጎሰሙን መቀጠሉን ሲኮንን እራሱ  አዴፓ  የተባለው ቡድን  በአማራ  ሕዝብ  ስም  ተሰይሞ  የአማራን  ሕዝብ  ሲጨፈጭፍና ሲያስጨፈጭፍ ለመክረሙ  የሚፈናቀሉ፣  በአሰቃቂ  ሁኔታ  የሚገደሉ፣  የአማራ እናቶች  እንዲመክኑ  ማድረጉ፣  በከሚሴና  በካራቆሬ ቤተክርስቲያን  ሲጋይ፣  በርካቶች ሲጨፈጨፉ፣  …ወዘተ  በቸልታ  እንዲታለፍ  ማድረጉ  የአዴፓን  የአማራ  ሕዝብ ጠላትነት የሚያሳይ መሆኑን ብዙዎች ሲያነሱ ይሰማል፡፡ በቅርቡም የአብን አመራር አባላትንና ተራ አባላትን እያሳደደ የሚያሳስረው፣  የአዲስ  አበባ  ባለአደራ  ኮሚቴ አባላትን  እያሰረ  ያለው  አዴፓ  መሆኑን  በማንሳት፤  አዴፓ፣  እንደ ህወሓት፣  እንደ ኦህዴድ/ኦዴፓ፣  በአጠቃላይ  ኢህአዴግ  በሚባለው  ጭምብል  ስር  የተሰባሰቡና ግብረ­በላ  የሆኑ ቡድኖች ሁሉ የአማራ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ደመኛ ጠላቶች ናቸው፡፡ አዴፓ በመግለጫው ሹሞቹ በአርሲ ያቆሙትን የአኖሌ  ሀውልት  እንዲነሳ ለምን አልጠየቀም ብሎ ማንሳትም  ተገቢና  የአዴፓዎችን ማንነት  የሚያጋልጥ ይሆናልም እየተባለ ነው፡፡ ከዚህ ባለፈም አዴፓ በእርግጥ ከአዲሱ ጌታው ከኦዴፓ ጉያ ከወጣና በራሱ ሳምባ መተንፈስ ከጀመረ ለምን  የወያኔ ዘረኛ ህገ­አራዊት በመባል  የሚጠራው (ሕገ መንግሥት) ይሻር  የሚል ጥሪ  አላሰማም፣  አዴፓ  ለምን የጄነራል አሳምነው ጽጌ ግድያ በእነ ዐብይ የተቀነባበረ መሆኑን አላጋለጠም፣ አዴፓ በመግለጫው እንዳለው ጥፋተኛ ባለመሆኑ ይቅርታ እንደማጠይቅ ቢሆንም በቅርቡ እንኳ እያደረገ ያለው እስራት  ፣ የኦዴፓ አጋሰስነትን እንጂ ሌላ ባለመሆኑ  ህወሓት  በሚጠየቅበት  ወንጀል ሁሉ  እነደመቀ፣  እነገዱ፣  እና  በዙሪያቸው  የተኮለኮሉ  ሁሉ  ተጠያቂዎች መሆናቸውም  በአትኩሮት  ሊታይ  የሚገባው  እነደሆነ  በርካቶች  ሲያነሱ  ይሰማል፡፡ ከህወሓት  መግለጫ  መገንዘብ የሚቻለው በአዴፓ ስም በድፍን የአማራ ሕዝብ ላይ የጦርነት ክተት አዋጅ ማወጁን ሲሆን ለዚህ የሚሰጠው ምላሽ እንደመስተዋት የተሰነጣጠቁትን  ዘረኛ  ፋሽስቶች  ከስር  መሰረታቸው  መንግሎ  ለመጣል በዴሞክራሲያዊ  የአንድነት ኃይሎች የተቀናጀ ትግል መሆኑን የፖለቲካ አዋቂዎች ያስረዳሉ፡፡ በቅርቡ ከውስጥ አወቆች አፈትልኮ ከወጣ መረጃ መገንዘብ  የተቻለው በአሜሪካ  አማካይነት ኦዴፓ  ከእነ ብርሀኑ  ነጋና  አንዳርጋቸው ጽጌ ቡድን  ጋር በመሆን  ስያሜ ለውጥ በማድረግ አዲስ ተብዬ የፖለቲካ ቡድን ሊመሰርቱና ቀስ በቀስ በብሔረሰብ የሚጠሩ ድርጅቶች እንዲከስሙ ሴራው  መነደፉን  መረዳት  ተችሏል፡፡  ሁለቱ  ግለሰቦች  በኤርትራ  በረሀ  ወጣቶችን  ሲጨፈጨፉና  በባዶ  ወሬ የወጣቶችን የትግል ሞራል በመስለባቸው እና በተደጋጋሚ አረመኔው ኢሳያስን ዴሞክራት እንደሆን የአይጥ ምስክር ዲምቢጥ እንዲሉ ወሽካታ ምስክርነት በመስጠታቸው ሰብእናቸው የተዋረደ በመሆኑ የሚቋቋመው ቡድን ላይ ጥቁር ጥላቸው  ሊያጠላበት  እንደሚችልና ተቀባይነቱ  ሊዋረድ  እንደሚችል  የፖለቲካ  አዋቂዎች  ያስረዳሉ፡፡  ከዚህ በመነሳትም ይህን ሁኔታ  ለመቋቋም  ህወሓት ውስጥ ውስጡን   እያደረገው ያለውን  መጠነ  ሰፊ ሀገር  የማተራመስ ዘመቻና  የእርስ  በርስ  ደም  ማፋሰስ  ዘመቻ  በሰፊው  ሊቀጥል እንደሚችል  ካወጣው  መግለጫ  መገንዘብ  መቻሉም እየተወሳ ነው።

#አሜሪካ፣ ከዘረኛው አገዛዝ ጋር ወታደራዊ ልምምድ ለማድረግ መወሰኗ አነጋጋሪ መሆኑ ታወቀ

 አሜሪካ በሰላም አስከባሪነት ስም የዘረኛው አገዛዝ ወታደራዊ ጡንቻን ለማፈርጠም ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ የጋራ የስልጠና ልምምዶችን ማድረጓ የሚታወስ ነው ፡፡ ዘረኛው አገዛዝ ለአሜሪካ አድሮ በኢትዮጵያ ምድር የሰው አልባ የአሜሪካ ጄቶች የሚንደረደሩበት አርባ ምንጭ ላይ መሬት ሰጥቶ የሶማሌውን አሸባሪ ቡድ አልሽባብን በማውደም ስም  ንጹሀን  የሶማሌ  ዜጎች  እንዲጨፈጨፉ መደረጉም  የሚታወስ እንደሆነ  ይነገራል፡፡  እንዲህ  ያለውን፣ መሬትን ለኃያል  ሀገር  የጥፋት  ጄቶች መንደርደሪያነት  የሚሰጡ  ሀገራት  በሕዝብ  የተጠሉና  ስርዓታቸው ጨቋኝና  በዝባዥ የሆኑ  እንደሆኑ  በጉዳዩ  ላይ  ጥናት  ያካሄዱ  የዓለም  ተቋማት  ማጋለጣቸውን በርካቶች  በማንሳት፤  አሜሪካ ለምትጭራቸው  ጦርነቶች  የውጪ  ኃይል  ለማሰባሰብ እነዲህ  ባለው  በሰላም  አስከባሪ  ስም  ስልጠና  በመስጠት ለእሳት  እየማገደች እንደሆነ  ዓለም­አቀፍ  የፖለቲካ  ተንታኞች  ያስረዳሉ፡፡  ስልጠናው  የሚሰጥበት  ቦታ በሚስጥር የተያዘ ሲሆን በስልጠናው የሚሳተፉት ሀገራት፣ ብራዚል፣ ካናዳ፣ ቡሩንዲ፣ ጂቡቲ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ኬንያ፣ ኔዘርላንድ፣ ርዋንዳ፣ ሶማሌ፣ ኡጋንዳ፣ እንግሊዝ ሲሆኑ የሚካሄደው ከሐምሌ 8 እስከ 24 መሆኑ  ከአሜሪካ ኤምባሲ ከወጣው መግለጫ መገንዘብ ተችሏል።
#ኦህዴድ/ኦዴፓ የሕዝብን ሰላም በወረበሎች እየበጠበጠ መሆኑ ተጋለጠ
 ከዛሬ  አንድ  አመት  ቀደም  ሲል “ቄሮ”  በሚል  ስያሜ  ኦዴፓ  የተሰኘው  የአሁኑ ገዢ  ቡድን  በተለያዩ  አቅጣጫዎች በትግል  ስም  ሁከትን  ሲፈጥር፣  ቤቶችን  በእሳት ሲያቃጥል፣  የተለያዩ  ተሸከርካሪዎችን  በእሳት  ሲያጋይ፣  አውራ መንገዶችን በመዝጋት ዜጎችን  ሲዘርፍ፣  የአማራ  ገበሬዎችን  በአሰቃቂ  ሁኔታ  ሲያስገድል፣  ሲያፈናቅል፣ …ወዘተ መክረሙ የሚታወቅ እንደሆነ በርካቶች በምሬት ሲያስረዱ ይደመጣል፡፡ በአዲስ አበባ ዙሪያ በጋራ ቤቶች የሚኖሩ ዜጎችን  በር  እያንኳኩ ለቃችሁ  ውጡ  እያሉ እንዲያስፈራሩ  መደረጋቸውና  አማራና  ክርስቲያንን  በሜንጫ  በማለቱ በኢትዮጵያ ሕዝብ  ጥርስ  የተነከሰበት  ባለሜንጫ  አሸባሪ  በቂሊንጦ  የጋራ  መኖሪያ  መንደር በመገኘት  አጠና  ላይ ሚስማር ጠቅጥቀው ሕዝብን ለመጨፍጨፍ ለተሰበሰቡ በቄሮ ስም ለሚጠሩ ወሮበሎች “በሏቸው”  የሚል ንግግር ማሰማቱን  የሚያስታውሱ እንደሚሉት  ኦዴፓ  የተባለው  አገዛዝ  በእንዲህ  ወጣቶችን  ቄሮ  በሚል  የሽብር ንቅናቄ በማደራጀት ሕዝባዊ ተቃውሞዎችን  ለማሽመድመድ መታቀዱን  ለመገመት አያዳግትም  እየተባለ  ነው፡፡  ባሳለፍነው ሳምንት የአዲስ አበባ ባላደራ ኮሚቴ፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ ተብዬው ከሰኔ ሠላሳ አንስቶ ህጋዊነት እንደሌለውና በገፍ እተፈጸመ  ያለው እስር  ህገ­ወጥ  መሆኑን  እያስረዱ  ባለበት  (በዚህ  ሳምንት)  ታከለ  ኡማ  የላካቸው ቄሮ  ተብዬ ወሮበሎች  ሁከት  በመፍጠር  ጋዜጣዊ  መግለጫው  እንዲቋረጥ ማድረጋቸው  የማሸበር  እንቅስቃሴው  አካል  መሆኑ በትኩረት ሊታይ ይገባዋል ተብሏል።

#ዘረኛው አገዛዝ ዜጎችን እያፈሰ ማሰሩን መቀጠሉ ተሰማ

 ከሁለት ሳምንት በፊት በወያኔና ኦዴፓ የተቀነባበሩትን ግድያዎች ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ  ለሀገር  አንድነትና ለህግ  የበላይነት  የሚቆረቆሩ ዜጎች  እየታሰሩ መሆናቸውና  ብዙዎቹም  የታሰሩበት  ስፍራ  ድብቅ  መደረጉ  በስፋት እየተነገረ ነው፡፡ በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት የአዲስ አበባ ባላደራ ኮሚቴ አባል የሆነው ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ፣ የአብን የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆነው ክርስቲን ታደለ በአፋኞች ተይዘው መታሰራቸው ታውቋል፡፡ በተመሳሳይም በባህር ዳር እና በጎንደርም በርካታ ወጣቶች እየታሰሩ መሆናቸውን ተያይዞ ከደረሰን ዜና መገንዘብ ተችሏል።
#ለሲዳማ ጥያቄ ዘረኛው አገዛዝ ምላሽ ባለመሰጠቱ ቀውስ ሊከሰት ይችላል የሚል ሰጋት ማሳደሩ ተሰምቷል

 ሲዳማ፣ “ደቡብ”  ከሚባለው የወያኔ የአገዛዝ መዋቅር ወጥቶ ብቻውን በክልልነት እንዲቆም የቀረበው ጥያቄ ምላሽ ሳያገኝ  ድፍን  ዓመት  በማለፉ  የሲዳማ  የፖለቲካ ድርጅቶች  በተናጠል የሲዳማን ክልልነት ለማወጅ ሐምሌ 11 የመጨረሻ ቀን መሆኑን አሳውቀው እየተጠባበቁ መሆናቸው እየተነገረ  ነው፡፡

 ሹሙ  ለዚህ ጥያቄ የሰጠው ምላሽ በትዕግስት ካልጠበቁ እርምጃ  እንደሚወስድ ሲሆን ይህ ደግሞ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ያፈሰሰውን  በመቶዎች የሚቆጠር የሲዳማዎችን ደም በአስከፊ ሁኔታ ለመድገም እንደሆነ ከፉከራው መረዳት ይቻላል ተብሏል፡፡ ቀድሞም ቢሆን  ልክ እንደ ጭምብሉ ኢህአዴግ እንደሚባለው ግንባር፣ ክልል የሚለውም  ከፋሽስቱ ጣሊያን የተወረሰውን የከፋፍለህ ግዛ ይትባሃልም መፈረካከሱ አይቀሬ መሆኑን ከዚህ ከሲዳማ እንቅስቃሴ መገንዘብ  ይቻላል  እየተባለ ነው፡፡  ከዚህ  በመነሳትም  የወያኔ  የመጨቆኛና የመከፋፈያ መሳርያ  የሆነው ሕገ­ወያኔም ተቦጫጭቆ  በእሳት ጋይቶ አመድ መሆኑ አይቀሬ ነው እየተባለ ነው።

#የዘረኛው አገዛዝ ጦር ቃል­አቀባይ፣ ትችት በጦሩ ላይ እንዳይሰነዘር ማስጠንቀቁ አነጋጋሪ መሆኑ ተነገረ

 መሀመድ  ተሰማ  የተባለ  የዘረኛው  አገዛዝ  ጄኔራል  ባሳለፍነው  ሳምንት፣ የአገዛዙን ጦር በሚተቹ ላይ እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምሩ የተሰነዘረው ዛቻ አነጋጋሪ መሆኑ ታወቀ፡፡ በመሰረቱ ሃያ ስምንት አመታት ሙሉ ንፁሀን ዜጎችን ሲጨፈጭፍ የነበረው  አጋዚ  የሚል መጠሪያ  የተለጠፈለት ጦር  ለመሆኑ ምንም  እንደማያከራክር ብዙዎች በሐረር  ነፍሰ­ጡሯን  ለመድፈር  ሲሞክሩ  ስታመልጣቸው  የገደሏት  ይህ  ስነ­ስርዐት  እንዳለው  የሚነገርለት  ጦር አባላት  አይደሉምን  የሚል ጥያቄ  በርካቶች በምሬት ሲያነሱ ይሰማል፡፡ በጉደር አባትና ልጁን መኖሪያ ግቢያውን ዘልቀው የእሩምታ  ጥይት አዝንበው የገደሏቸው፣ በጎንደር የ14 አመት ህፃን የገደሉ፣ በአዲስ  አበባ፣ ወንድራድ ትምህርት ቤት አቅራቢያ፣ ሽብሬ የምትባል ወጣትን የገደሉ፣ የዚህ ዘረኛው አገዛዝ ጦር አባላት መሆናቸውንም አገር ያወቀው መራራ ሐቅ ሆኖ ሳለ ጦሩን አይተች መባሉ የጉዳዩ አዝማሚያ ሌላ ጠረን እንዳለው እየተነገረ ይገኛል፡፡ በሰሜን ሸዋ በከሚሴ፣ በአጣዬ፣ ሰሞኑን እንኳ በማንዱራ፣ ገነተ­ማርያም ቀበሌ የአማራ ኗሪዎች በጉሙዞች በቀስትና በጥይት ሲጨፈጨፉ  አማሮችን  እያዳፉ  ያስር  የነበረው ይኸው የዘረኛው ቡድን ጦር መሆኑን የጉዳቱ ሰለባዎች ሲገልጹ ተሰምተዋል፡፡ የፖለቲካ አዋቂዎች በተጨባጭ ከሚታየው የሀገሪቱ ምስቅልቅል የፖለቲካ ሁኔታ በመነሳት በማረጋጋት  ስም  ሹሙን  በመፈንገል  ጄነራሎቹ  ስልጣን  እንዲጨብጡ  የባእዳን ኃይሎች ሴራ ከመጎንጎን እንደማያርፉ አስጠንቅቀዋል።

#ለዝርዝር ዜናዎች > ከታች ይጫኑ (to listen detail news click below)

To Read: http://www.finote.org/Fikarezena.pdf
To Listen PART 1: http://www.finote.org/TodayPart1.mp3
You Tube: https://youtu.be/X0vQTYPFVog

http://www.eprp.com
« Last Edit: July 14, 2019, 05:02:48 PM by staff3 »