Recent Posts

Pages: 1 2 3 4 [5] 6 7 8 9 10
41
በፍኖተ ዴሞክራሲ የኢትዮጵያ አንድነት ራዲዮ
በ ጥር 14 ቀን 2011 ዓም የተላለፈ ሐተታ

አቅጣጫውና ግቡን ያላወቀ ለውጥ ከንቱ ነው

በሀገራችን ለመሰረታዊ ለውጥ ሲካሄድ የነበረው ሕዝባዊ ተደናቅፎ በባእዳን ድጋፍ የይስሙላ ለውጥ ሂደት ከተጀመረ ወራትን አስቆጥሯል። ሕዝብ የሚጠበቀውን ጉጉትና ፍላጎት ለሟሟላት ገና አልተሳካለትም ብሎ መደምደሙ ምክንያታዊ ነው ማለት ግን ይከብዳል ። ዘመናትን ያስቆጠሩ ሀገራዊ ችግሮችን በወራት ቀርቶ በዐመታት ለማስወገድ ፤ የበርካታ ኃይሎችንና የመላውን ህዝብ ትብብርንና ንቁ ተሳትፎን ይጠይቃል ። ሕዝባዊና ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን መገንባት ከወሳኞቹ ጉዳዮች የመጀመሪያውን ረድፍ ይይዛሉ። እነኝህን ሁሉ በግምት ወስጥ ማስገባት ለሚታሰበው ዐላማ ስኬታማነት ዋስትና ይሆናሉ።ከሁሉ በፊት ግን የዴሞክራሲ ግንባታ የቅድሚያ ቅድሚያ ጉዳይ ሊሆን ይገባል ። እነኝህን ወሳኝ ጉዳዮች ታሳቢ አድርጎ መንቀሳቀስ አማራጭ አይኖረውም ። የዴሞክራሲን መሠረት መጣል ተሳትፎንና ድጋፍን የሚያረጋግጥ ሲሆን የሕዝብ ሙሉ ተሳትፎ ውጤት ሊያስመዘግብ የሚችለው ደግሞ፤ ዴሞራሲያዊ ተቋማቱ ነፃና ገለልተኛ ሆነው ሲመሰረቱ ብቻ ነው። ህዝብን መሰረት ያደረገ ስር ነቀል ለውጥ እንዲመጣ ከተፈተለገ ደግሞ የወደፊቱን አቅጣጫ ሊያመላክት የሚችል በግድ አቅጣጫና ግብን መቀየስና በተግባር መተርጎም ያስፈልጋል። ይኽ ጉዳይ ፤ አከራካሪ ሊሆን አይችልም ። አቅጣጫና ግብን ለመቀየስ ደግሞ የሀገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ በሚገባ መረዳትን ይጠይቃል። ይህ መኖር አለበት ስንል ህዝብ የስልጣን ምንጭ የሚሆንበትን ዓላማ በግልጽ አስቀምጦ ወደ ግቡ የሚወስዱትን ሂደቶች እየተቆጣጠሩ ዘላቂ ግቡ እውን እንዲሆን ማድረግ ነው። እንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ አሁን ለህዝብ ግልጽ ሆኖ ይታያል ማለት አይቻልም ። የሀገሪቱን ሁለንተናዊ ችግሮች በቅጡ ያልተገነዘበ ማነኛውም ኃይል፤ የስር ነቀል ለውጥ ሂደትን መቀበል ይቸግረዋል። ውስብስብ የሆነውን የሀገሪቱን ችግር ሳይረዱ ፤ መፍትሄ ማግኘት ያስቸግራል። በዚህ ምክንያት ነው ያገራችንን ችግር ለመፍታት ያልተቻለው። ሕዝባዊው ለውጥ ፤ የተሳካለትን የሽግግር ጉዞ እንዳይራመድ መሰናክል የገጠመውም አንደኛው ምክንያት፤ ይኽ ይመስላል ። የሀገሪቱ ችግሮች፤ ድርብ ድርብር ፤ ውስብስብና ውጥንቅጥ፤ ጥልፍልፍና መላ ቅጡ የጠፋበት ነው። የመፍትሄው ፍለጋ ሂደት፤ በሆይ ሆይና በውቂው -ደብልቂ ፤ በግርግር፤ በያዘው- ልቀቀውና በመደነባበር የሚፈታ አይደለም ። በረጋ መንፈስ፤ አስተውሎና አርቆ በማሰብ ሊስተናገድ ይገባል። የሰከነ አዕምሮን አንግቦ መንቀሳቀስ፤ ዘለቄታው የተሳካ ይሆናል ። እወደድ ባይነት ብቻውን ሩቅ ምዕራፍ አያስኬድም ። የህዝብን ፍላጎትና ጥያቄ ማስተናገድ የሚቻለው ፤ በህዝብ ወገንተኝነት እንጅ፤ ህዝበኝነት (ፖፕሊስት ) በመሆን አይደለም። በመፈክር ንባቤ ሀገር አይገነባም ። በአደባባይ ጠርሙስ በመስበር የሕዝብን ልቦና አዕምሮ ማስተናገድ


አንዳልተቻለ ካለፈ ታሪክ መማር ይገባል ።ሀገርና ሕዝብ አደጋ ላይ ሲወድቁ ፤ እግሬ አውጭኝ ብሎ በአሳፋሪ ሁኔታ መሸሽ ፤ ለተተኪው ትውልድ አንገት ሰባሪ ታሪክን ጥሎ ማለፍ እንጅ ፤ መልካም ቅርስ አይሆንም። ህዝብና መንግሥት፤ አንድ ካካል አንድ አምሳል ሆነው ካልተሰለፉ፤ ሀገር ባለቤት ታጣለች። ባለቤት ያጣ ሕዝብና ሀገር የማንም መጫወቻ ሆኖ ይቀራል። የዛሬይቷ ሀገራችን በዚህ ሁኔታ ላይ ትገኛለች ብሎ መደምደም ከዕውነት የራቀ አይደለም ። ኢትዮጵያ እንደ ሀገር በርካታ ውስብስብ ችግሮች ተደቅነውባታል አንደኛ ነገር ፤ዜጎቿ እንደ ዜግነት ክብርና ምልዑነት ሳይሆን ፤ በዘርና በቋንቋ፤ ፍርክስካሽ ተመድበው እንዲታዩ በመሆናቸው ነው ። ይኽም ሁኔታ ዜግነታቸው ብቻ ሳይሆን፤ ሰብዕናቸውንም ጭምር አዋርዶታል ። ሁለተኛ ነገር ፤ መልክዓ ምድሯ፤ በምልዑነት ሳይሆን፤ በፍርክሥክሥነት / በክልልነት ተጨማትራ እንድትታይ ተደርጋለች ። አዲሱ ትውልድ፤ ሀገሩን የሚያያት ፤ በኢትዮጵያነቷ ሳይሆን ፤ በፍራክሽን ሂሳብ አግባብነት ሆኗል ። ኢትዮጵያ ተብላ ትጠራ አትጠራ፤ ኢትዮጵያ ትኑር/ አትኑር ደንታ አንዳይሰጠው ሆኖ እንዲያድግ እየተደረገ ትውልድ ሆኗል ። ክልል፤ ለአንድ ሀገር ዜጎች መኖሪያ ሳይሆን ፤ ለክብት ግጦሽ ማሰማሪያ፤ መናሃሪያና ማጎሪያ ቦታ ነው ። ሀገር እንደ ሀገር ፤ መቆጠሯ እየቀረ፤ በየክልሉ ተኮድኩዳና ፤ ተደይና እንድትቀር ተፈርዶባታል ። ይኽንን ያደረጉት ባለ ስንኩል አዕምሮዎቹ የዘረኛ አገዛዝ አራማጆች ወያኔዎቹ ናቸው ። አሁን ግን፤ በሕዝባዊው ዓመፅ ዋጋቸውን እየከፈሉ በመክሰም ሂደት ውስጥ ይገኛሉ ። ለዚህም፤ ወጣቱ ትውልድ ምስጋና ይድረሰው ! ከባድ መሥዋዕት ከፍሏልና ! ሦስተኛ ነገር ፤ መንግሥት የሚባለውን መስፈርት የሚያሟላም ሆነ ሥልጣኑን ከህዝብ የተቀበለ ተቋም በሀገሪቱ ውስጥ የለም ። ህጋዊነትም የሕዝብ ተቀባይነት ያለው ኃይል የለም። ሀገሪቱን እንደ ሀገር ፤ ዳር ድንበሯም ፤ የግዛት ልዋላዊነትም ሆነ ዜጎቿንም እንደ ዜጎች፤አዋኅዶና አስከብሮ ያለ መንግሥታዊ ተቋም ይታያል ለማለት አያስደፍርም። ኢትዮጵያ እንደ ሀገር መቀጥል እንዳትችል ያደረጓት ዘረኞች ጥንታዊቷንና ታሪካዊነቷን እንደ ሀገር እያጠፉ ፤ ወደ ዘመነ- መሳፍንት የጉልት መንደር እንድተገባ ለማድረግ እየተወራጩ ይገኛሉ ። የጦር አበጋዞችና ያካባቢ ታጣቂ ነፍጠኞች የየግላቸውን ግዛትና የአገዛዝ ሥርዓት እያሰፈኑ የአገሪቱን ህልውና አደጋ ውስጥ እንዲወድቅ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ አገሪቱ በአሁኑ ወቅት ብዙሃን ባለነፍጥ ወጠጤዎች የሚደነፉባት መሬት በመሆኗ ፤ ማን እንደሚቆጣጠራትና ወደ የትስ አቅጣጫ አንደምትሄድ እንኳ ማንም ወገን ሊያውቅ ከማይቻልበት ደረጃ ተደርሷል ። አካሄዱ፤ ፍኖተ- ካርታ ( ሮድ ማፕ) ስሌለለው፤ ህዝብ ግራ ተጋብቷል። የባሰ እንዳይመጣ ከመጨነቅ ሌላ ምርጫ አጥቷል ።


" ለኢትዮጵያ ሕዝብ፤ የአንድ መቶ ዐመት የቤት ሥራ እንሰጠዋልን። " ብለው ያሰቡት ዕቅድ በተግባር እየታየ ነው ። ይህንን ትንቢት በተግባር ለመፈፀም አሁን ሥልጣኑን የተረከበው የአገዛዝ ቡድን፤ አውቆም ይሁን ሳያውቀው ሀላፊነቱን ወስዷል። በእነርሱ አመለካከት፤ ኢትዮጵያን ማዘመን ማለት፤ ወደ 18ተኛው ክፍለ ዘመን እንደ ነበረችበት የጨለማ ዘመን የኋላ ዙር ጉዞ ማስኬድ ሆኗል ። ሀገርን እንደ ኩበት ጠፍጥፎ መስራት ቀላል የሚመሰላቸው የዘረኛ አገዝ አራማጆች ፤ በቀላሉ በማይበጣጠሰውና በብዙ ክርና ማግ የተዋሃደውን የህዝብ አንድነት ለማፍረስ ላለፉት ሃያ ሰባት ዐመታት ሞክረው ነበር ። ሳይሳካላቸው ቀርቶ፤ እነርሱም ፤ እንደ ዮዲት ጉዲት ፤ እንደ ግራኝ መሃመደና እንደ ደርቡሾች መና ሆነው ቀርተዋል ። አሁን በሥልጣን ላይ የሚገኙት የወያኔ ቅሪቶች፤ " ከታሪክ ያልተማረ፤ ራሱን ሲረግም ይኖራል " እየህነባቸው ነው። በስልጣን ላይ ያሉት አዲሶቹ ሹሞች የሽግግር ስምሪት አቅጣጫ ለመስጠትና ሕዝባዊው ኃይል እንዲያገኝና የታሰበውንም ግብ እንዲመታ ለማድረግ መሠረታዊ የሆነ የሥርዓት ለውጥ የሚገኝበትን ሁኔታ ከማመቻቸት ይልቅ በጥገና ለውጥና ፤ በአዝጋሚና ተንፏቃቂ ማጥ ውስጥ እየዳከሩ ይገኛሉ። ዞሮ ዞሮ፤ ለዘላቂ ሠላምም ሆነ ለአስተማማኝ የለውጥ ሂደት የሚከተሉት ጉዳዮች መረጋግጥ ተፈጥሯዊ ነው ተብሎ ይታመናል ።

1ኛ. ሀገራችን መሠረታዊ የሆነ የሥር ዓት ለውጥ እንጅ የጥገና ለውጥ አያስፈልጋትም። አሁን ላለው ሀገራዊ ችግር መንስዔው ፤ በውሸት ትርክትና በቋንቋ ላይ የተመሰረተው ህገመንግሥት ተብየው የወያኔ ፕሮግራም ሰነድ ነው። ይኽ ህገ መንግሥት ላንዴና ለመጨረሻው ወወገድ አለበት ። አሁን በየቦታው የሚካሄደው የእርስ በርስ የዜጎች ፍጅት ፤ መሠረታዊ ምክንያቱ ወያኔ የፈጠረው የክልል አገዛዝ ነው። ይህ ጠንቅ ደግሞ በዘር ላይ የተገነባው ህገመንግሥቱ የፈጠረው በመሆኑ፤እርሱ ካልተወገደ በቀር ፤ ዜጎች በሠላም አብረው እንደወትሯቸው ለመኖር አይችሉም።

2ኛ. መርዘኛውን ህገመንግሥት የቀረፀው ይኽ ጠንቀኛ ዘረኛው ሥርዓት በመሆኑ፤ እንደ ሥር ዓት፤ እስከ ጣጣው ካልተወገደ፤ ስር የሰደደው የሀገሪቱ ችግር ይወገዳል ማለት ዘበት ነው ። በመሆኑም፤ መሠረታዊ የሥር ዓት ለውጥ እንጅ፤ ለጥገና ለውጥ ጊዜና ሃብት ማባከን የኢትዮጵያን ሕዝብ እንደመክዳት ይቆጠራል።

3ኛ. በሀገሪቱ ሠላምና መረጋጋት መምጣት የሚችለው፤ በየደረጃቸው ቅደም- ተከተል ፤ ሦስት ጉዳዮች ዕውን ሲሆኑ ብቻ ነው። እነርሱም ፡------- ሀ. ዴሞክራሲ በመላው ሀገሪቱ ሲስፍና ዜጎቿም ያለቅድመ ሁኔታ ተጠቃሚና ሙሉ ተሳታፊ ሲሆኑ ነው። ለ. የሽግግር ወቅት ፤ ከሙሉ ኃላፊነቱና ግዴታው፤ ተግባሩና ዕድሜው በህዝብ ስምምነት ህጋዊነቱ ተረጋግጦ ሲታዎጅ ነው። ሐ. የሀገሪቱ ዜጎች፤ በወኪሎቻቸው አማክኝነት የተዘጋጀውን የሕገመንግሥት ረቂቅ ፤ በሕዝበ-ውሳኔ (ረፈረንደም) ከጸደቀ በኋላ ፤ በዜጎች ቀጥታ ተሳትፎ በሚመጣ ምርጫ፤ ዴሞክራቲክ መንግሥት ሲቋቋም ብቻ ነው።

ኢትዮጵያ ሀገራችን፤ ከላይ በቅደም ተከተል በሰፈሩት ሂደትች ካላለፈች በስተቀር ፤ በጥግና ለውጥ ዘላቂ ሠላምና መረጋጋት ፤ ታገኛለች ተብሎ አይታሰብም ። ለዘላቂ ሠላምና መረጋጋት፤ ይህንንም ዕውን ለማድረግ የሚያስችለውን መሠረታዊ ለውጥ ከሚፈልጉ ጋር ተባብሮ ለመስራት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ። በሌሎች ድግስ ሄዶ ፍርፋሪ መጠየቅ፤ ቡኩርናን ፤ በጭብጥ ምስር መለወጥ ስለሚሆንብን ፤ያንን አናደርገውም! የምንታገልበት መርሆም አይፈቅድም !

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኖራለች ! ጸረ ወያኔ ጸረ ኢሕአዴግ ትግላችን ተፋፍሞ ይቀጥል !!
FinoteHateta_January_24_2019.pdf
PDF Link:
https://www.ethiox.com/articles2/FinoteHateta_January_24_2019.pdf
42
Websites To Get online Freelance Jobs or Workers....

https://www.ethiox.com/work/Websites To Get Freelance Jobs.pdf
43
ኢትዮጵያችን ምን እየሆነች እንደሆነ ግልፅ አርጎ የሚያሳይ ማጠቃለያ:
January 5, 2019 Konjit Sitotaw

በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ቦረና ዞን ሞያሌ ከተማ በገሪና ቦረና ጎሳዎች መካከል ባለው ግጭት ከህዳር ወር መጀመሪያ ጀምሮ ከ50 በላይ የሰዎች ህይዎት ጠፍቷል፣ ከፍተኛ የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመትም ደርሷል።

* ከዚህ በተጨማሪ ታህሳስ 8 ቀን 2011 ዓ.ም ሞያሌ ከተማ በቀለ ሞላ ሆቴል ውስጥ በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት የ12 ሰዎች ህይዎት ጠፍቷል።

* በነቀምቴ፣ በነጆ፣ ጋሆ ቄቤ፣ በሀሮ ሊሙ በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በተፈፀሙ ጥቃቶች ከ30 በላይ ሰዎች ህይወት የጠፋ ሲሆን አንድ ሰው ቆስሏል። መንግስት በአካባቢው የሚገኙ የኦነግ ታጣቂዎች ድርጊቱን እንደፈፀሙት ቢያመላክትም እስካሁን ማረጋገጫ አልተገኘለትም።

* በ17/04/2011 ዓ.ም የጊቶ ጊዳ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ፅ/ቤት ሀላፊ ባልታወቀ አካል በነቀምቴ ከተማ ውስጥ ተገድለዋል። በዚሁ እለት በነቀምቴ ከተማ በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች 2 ሰዎች ተገድለዋል።

* በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምዕራብ ጎንደር ዞን ከህዳር 22 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በጭልጋና በደንቢያ አካባቢዎች በአማራና በቅማንት ማህበረሰብ መካከል በተነሳ ግጭት ቢያንስ የ50 ዜጐች ህይወት አልፏል፣ ከፍተኛ የሆነ ንብረት መውደምና ቃጠሎ ደርሷል፣ ዘረፋና ማፈናቀል ተፈፅሟል። በአሁኑ ሰዓትም ከፍተኛ የጸጥታ ችግር ያለ ሲሆን የክልሉ መንግስት ችግሩን ለመፍታት ወንጀለኞችን በህግ ቁጥጥር ስር እያዋለ እንደሚገኝ ከአካባቢው ለሰመጉ የደረሱት መረጃዎች ያመላክታሉ።

* ሲዳማ ዞን በንሳና ቦና ወረዳዎች “መሬታችን ለኢንቬስተር አላግባብ ተሰጥቷል” በሚል ምክንያት የተፈጠረ አለመግባባት በወረዳው ካቢኔ አንመራም ወደሚል ተቃውሞ ተሸጋግሮ ከህዳር ወር አጋማሽ ጀምሮ በተቃውሞ ላይ የነበሩ 29 የሀገር ሽማግሌዎች በበንሳ ፖሊስ ጣቢያታስረው ይገኛሉ፤ በዞኑ በሊላ ወረዳ ከምዕራብ ጉጅ ዞን በሚያዋስን ድንበር ላይ ከህዳር ወር ጀምሮ በተፈጸመ ጥቃትና ግጭት ከ25 እስከ 35 የሚገመት የሰው ህይዎት መጥፋቱን፤ በሚሊዮን ብር የሚገመት የግልና የመንግስት ንብረት መውደሙን የሰመጉ ምንጮች ገልፀዋል።

* በምዕራብ ጉጂ ዞንና በደቡብ ክልል ቡርጂ ወረዳ ከ03/04/2011ዓ.ም ጀምሮ በታጠቁ ኃይሎች በተፈፀመ ጥቃት የ13 ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል፤ የአካል ጉዳት ደርሷል፤ ግምቱ ያልታወቀ ንብረት ተዘርፏል

* በጉራጌ ዞን በመስቃንና ማረቆ ማህበረሰብ መካከል ከመስከረም 03 ቀን 2011 ዓም ጀምሮ በተፈፀሙ ግጭቶች ቁጥራቸው ከ50 (ሃምሳ) በላይ ዜጐች ህይወት ጠፍቷል፣ በሰው አካል እና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል፤ በርካታ ዜጐችም ከመኖሪያ ቀያቸው ተሰደዋል። ከችግሩ ጋር በተያያዘ የሁለቱም ወረዳ አስተዳዳሪዎችና የመንግስት ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ዉለው ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል።

* የራያ ህዝብ የማንነት ጥያቄ ያነሱ ዜጐች በጥቅምት ወር መጀመሪያ ጀምሮ ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣታቸው ምክንያት የ5 ዜጐች ህይወት ማለፉን ገልፆ ሰመጉ ጋዜጣዊ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። ከዚሁ የራያ ህዝብ የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ከጥቅምት ወር ጀምሮ 761 የማህበረሰቡ ተወላጆች መቀሌ፣ ማይጨው፣ ውቅሮ፣ ተንቤን ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ እስር ቤቶች ታስረው እንደሚገኙ የራያ የማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ ለሰመጉ ገልጿል፤

* በደቡብ ክልል አማሮ ኬሌ ወረዳ በአማሮና በጉጂ መካከል ከሁለት አመት በላይ በቀጠለ ግጭት በርካታ ሰዎች ተገድለዋል፣ ቤት ንብረታቸው ወድሟል። በ10/04/2011 ዓ.ም የአማሮ አርሶ አደሮች ንብረት የሆኑ 156 ከብቶች በጉጂዎች በመወሰዳቸው ግጭት ተቀስቅሶ የአማሮ ኬሌ ተወላጅ የሆነ አንድ አርሶ አደር ህይወት ማለፉን ሰመጉ አረጋግጧል፤

* ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በያሶን ወረዳ ይኖሩ የነበሩ ቁጥራቸው 1,200 የሚሆኑ የአማራ ብሄር ተወላጆች ተፈናቅለው ከህዳር 15 ቀን 2011 ዓም ጀምሮ ባህርዳር ከተማ ዘን ዘልማ በሚገኝ የገበያ ማዕከል ተጠልለው ይገኛሉ፤

* በቦረና ዞን ተልተሌ ወረዳ በሚኖሩ የቡርጂና ኮንሶ ተወላጆች ታህሳስ 10 ቀን 2011 ዓ.ም በቦረና ተወላጆች መኖሪያ ቤቶቻቸው ተቃጥሎ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ተደርገዋል። ተፈናቃዮቹም ጃርሶ ቀበሌ ተጠልለው ቢገኙም፤ ከዚህም ቦታ ለቀው እንዲሄዱ የተለያዩ ጫናዎች እየተደረገባቸው መሆኑን ከአካባቢው ለሰመጉ የደረሱት መረጃዎች ያመላክታሉ፤

* ጥቅምት 18 ቀን 2011 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ በገንደ ገራዳ፣ ገንዳ ቦዬ እንዲሁም ገንደ ተስፋ የተባሉ አካባቢዎች ከህገ ወጥ የመሬት ወረራና እንዲሁም ከጸጥታ ኃይሎች ጋር በተፈጠረ ግጭት ፖሊስም ሁኔታውን ለማረጋጋት በወሰደው እርምጃ የሁለት ሰዎች ህይዎት አልፏል። 6 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው በድል ጮራ ሆስፒታል ህክምና ላይ ይገኛሉ፤

* ጥቅምት 21 ቀን 2011 ዓ.ም ድሬዳዋ ዙሪያ ቢራ የሚባል ቀበሌ 1 ማህበር በኦሮሞና በሱማሌ ጎሳዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት 12 የሚሆኑ ቤቶች መቃጠላቸውን፣ እንዲሁም 4 ሰዎች በጥይት ተመተው ቆስለው በህክምና ላይ ይገኛሉ፤

* ታህሳስ 13/2011 ዓ.ም ጀምሮ በምስራቅ ኢትዮጵያ በሱማሌ ክልልና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ በሆኑት ሲቲ ዞንና ምስራቅ ሃራርጌ ዞን የረር ጎታ በሚባል አካባቢ ብሄርን መሰረት ያደረገ ግጭት ተከሰቶ የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል፤

* በቡሌ ሆራ ዩንቨርሲቲ ከታህሳስ 4 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ከአማራ ክልል የመጡ ተማሪዎችን በገጀራ፣ በጩቤና በፌሮ ብረት በማስፈራራትና ድብደባ በመፈፀም ተማሪዎቹ ከማደሪያቸው መውጣታቸውን፣ አንድ ተማሪም ከሦስተኛ ፎቅ ወድቆ በደረሰበት ጉዳት ሆስፒታል ገብቷል። ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመመለስ እንደተከለከሉ የገለጹት ተማሪዎች ወደ ማደሪያቸውም ለመመለስ ያልቻሉ ሲሆን በዩንቨርሲቲው ግቢ ውስጥ በመከላከያ ተከበው ጥበቃ እየተደረገላቸው ቆይተዋል። ችግሩን ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ቢደረግም ተማሪዎች ለደህንነታቸው ስጋት እንዳላቸው በመግለፅ ለ12 ቀናት ሜዳ ላይ ውለው ካደሩ በኋላ ዩኒቨርሲቲውን ለቀው ወደየቤተሰቦቻቸው ተመልሰዋል። ግቢውን ለቀው ከመውጣታቸው በፊትም በተደራጁ ኃይሎች በድንጋይ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው እና ከ10 በላይ ተማሪዎች በደረሰባቸው ጉዳት ለህክምና መወሰዳቸውን ሰመጉ አረጋግጧል።

* የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በነቀምቴ፣ በነጆ፣ ጋሆ ቄቤ፣ በሀሮ ሊሙ በ03/03/2011 ዓ.ም ለሞቱ ዜጎች ሀዘናቸውን ለመግለጽ በ25/03/2011 ዓ.ም በወጡበት ወቅት 15 ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በታጠቁ የመንግስት ኃይሎች በጥይት ተመተው አንዱ ህይወቱ ሲያልፍ 13 ሆስፒታል ታክመው ወጥተዋል። አንድ ተማሪ በነቀምቴ ሪፈራል ሆስፒታል ተኝቶ ህክምናውን እየተከታተለ ይገኛል።

* ጅማ፣ አምቦ፣ ደብረ ብርሃን፣ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲዎች፤ እንዲሁም በሀዋሳ ከተማ አዲስ ከተማ መሠናዶ ትምህርት ቤት በተማሪዎች መካከል ብሔርን መሠረት ያደረጉ ግጭቶች ተቀስቅሰው ተማሪዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ የመማር ማስተማር ሒደቱም በተለያየ ወቅት ተቋርጦ ቆይቷል።

Via Elias Meseret & የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ)
45
Finote Democracy ፍካሬ ዜና -ታኅሣስ 21 ቀን 2011 ዓ.ም.
(30 December 2018 Weekly NEWS SUMMARY)
   
EPRP PR   
   
#ርዕሰ ዜና#
#በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በድንበር፣ በግጦሽ መሬት፣ በመማሪያና በሥራ ቋንቋ ምርጫ፣ መሬት ለቃችሁ ውጡ ግጭቱ ቀጥሏል
#አሁንም በሜቴክ ስም በርካታ ገንዘብ እየተዘረፈ መሆኑን ማወቅ ተችሏል
#ኤርትራ ድንበሯን የዘጋችበት ምክንያት እያነጋገረ ነው ተባለ
#የሁለተኛ ደረጃ መምህራን ስብሰባ መዘጋጀቱ ተሰማ
#በአዲስ አበባ የዳቦ ዋጋ ጭማሪ ሊደረግ መሆኑ እየተሰማ ነው
#ባንኮች ግዙፍ ብድሮችን ለመፈጸም የአቅም ውስንነት ስላላቸው ግንባታዎች እየተስተጓጎሉ መሆኑ ታወቀ
#ከኢትዮጵያ ህዝብ እሩቡ በአእምሮ ህመም እንደሚሰቃይ ተገለጸ

##ዝርዝር ዜናዎች##   

#በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በድንበር፣ በግጦሽ መሬት፣ በመማሪያና በሥራ ቋንቋ ምርጫ፣ መሬት ለቃችሁ ውጡ ግጭቱ ቀጥሏል
 በተለያዩ  የሀገሪቱ  አካባቢዎች  በድንበር፣  በግጦሽ መሬት፣  በመማሪያና  በሥራ ቋንቋ  ምርጫ፣ መሬት  ለቃችሁ ውጡ በሚል ጽንፈኛ አመለካከት ኩታ ገጠም የሆኑ ጎሳዎች እየተጋጩ በርካታ ሰዎች እየተገደሉና በጽኑ እየቆሰሉ መሆናቸውን ከተለያዩ ምንጮች  መረዳት  ተችሏል፡፡  በአንዳንድ  አካባቢዎች  የጤና  ተቋማት  ለቁስለኞች ህክምና  እንዳይሰጡ  ዛቻ ያዘሉ  መልዕክቶች  እየተላለፉ  መሆናቸውም  ይነገራል፡፡ በወለጋ  የሚካሄደው  ግጭት  ምንም  እንኳ  ኦነግ  የማያዘው ያፈነገጠ ኃይል እንደሆነ በተለያዩ ጊዜያት የተገለጸ ቢሆንም፣ ኦነግ ሊታመን እንደማይችል በርካቶች ያስረዳሉ፡፡ ወለጋ ላይ  እየተካሄደ  ያለው  ሕዝባዊ  ቀውስ  በሐረር፣  በባሌና  በአርሲ እንደሚከሰት ስጋት  ማሳደሩን  መገንዘብ  ተችሏል፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት ጉጂና ቡርጂ፣ አፋርና ኦሮሞዎች፣ አፋርና ኢሳዎች፣ ተጋጭተው በርካታ ንፁሀን ዜጎች ተገድለዋል፡፡ ይህን መሰል ግጭቶች ሊስፋፉና በየቦታው የእርስ በእርስ ግጭቶች ሰዎች ሊፈናቀሉ፣ ሊገደሉ፣ ንብረቶቻቸው ሊዘረፉ፣ እናቶችና እህቶች ሊደፈሩ ይችላል የሚል ስጋት ያሳድራል ተብሎ እየተሰጋ ነው።

#አሁንም በሜቴክ ስም በርካታ ገንዘብ እየተዘረፈ መሆኑን ማወቅ ተችሏል
 ሜቴክ የሚለውን ስያሜ አዲስ የሚባለው ዘረኛ አገዛዝ በመቀየር ኢኮሥኮ ማለቱ የሚታወስ ሲሆን አዲሱ ሜቴክን አዲሱ  አገዛዝ  እያሠራው  መሆኑ  ሲታሰብ  አዲስ የሙስና  መረብ  እየተዘረጋ  ነው  የሚል  ጥርጣሬ  እያጫረ  ነው ተብሏል፡፡  በቅርቡ አራት  ኪሎ  የሚገኘው  የጠቅላይ ሚንስት ገንዘብ  በኢኮሥኮ  እየተገነባ  እንደሆነ መረዳት  ተችሏል፡፡  ይህ  አጥር  በኮሎኔል  መንግሥቱ  ዘመን  ከአምስት  ጊዜ በላይ እየፈረሰ  መገንባቱ  የሚታወስ  ሲሆን  በመለስም  ከሁለት  ጊዜ  በላይ  መሰራቱ የሚታወስ  ነው  ተብሏል፡፡ በአሁኑ የጨረባ ፖለቲካም ወቅትም ከሁሉ አስቀድሞ ይህ አጥር አፍርሶ አጥር መገንባት ወቅታዊነቱ ሌላ ሳይሆን ገንዘብ ለመቀርጠፍ በስሌት የተገባበት መሆኑ እንደማያጠራጥር ብዙዎች ያስረዳሉ፡፡ መድኃኒት መግዣ በጠፋበት፣ ነዳጅ  በዱቤ  በሚመጣበት፣  ውሀና  ኤሌክትሪክ  በወረፋ  በየአስራ  አምስት  ቀኑ በሆኑበት፣  ጎዳና  የሚኖሩ  ህፃናት እየበዙ ባለበት፣ የአጥር ግንባታው አነጋጋሪነት እየጨመረ መሆኑን ተረድተናል።

#ኤርትራ ድንበሯን የዘጋችበት ምክንያት እያነጋገረ ነው ተባለ
 በአፍሪካ ረጅም ዘመናትን ካስቆጠሩ አምባገነን ገዢዎች አንዱ የሆነው ኢሳያስና የቢጤው ዘረኛ አገዛዝ መሞዳሞድ የአገዛዞቹ  እንጂ  የሕዝብ  ባለመሆኑ  ሳይውል ሳያድር  መፈረካከሱ  የማይቀር  መሆኑ  እየተነገረ  ነበር፡፡ ከታማኝ ምንጮች  ከተገኘው መረጃ፣  ታህሳስ  አምስት  ኢሳያስ ወደ  ሶማሊያ  ባቀናበት ወቅት  አምባገነኑን  ቡድን ከሥልጣን ለማስወገድ  ማሴራቸው የተደረሰባቸው በርካታ የጦር መኮንኖች ኢራ  ኢሮ በሚባል  እስር  ቤት  መታሰራቸው ታውቋል፡፡ በዚህ የከፍተኛ መኮንኖች እስር ስብሀት ኤፍሬም ተጠያቂ በመሆኑ እሱን ለማስወገድ የመጀመሪያው ዙር የሳዋ  ሰልጣኝ  የነበረና ከኤርትራ  ጠፍቶ  ኢትዮጵያ  ውስጥ  የሚኖር  የተጀመረውን  ነፃ  ዝውውር በመጠቀም ወደ ኤርትራ የገባ ሲሆን የበቀል እርምጃ በስብሀት ኤፍሬም ላይ እዲወስድ ይህን መፈንቅለ­መንግሥት ካቀነባበረው ቡድን መመሪያ ተሰጥቶት ያደረገው መሆኑን መገንዘብ ተችሏል፡፡ የታሰሩት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች በአሁኑ ወቅት በኢሳያስ ቀጥተኛ ቁጥጥር ስር ወደሚገኘው ማርያም ግቢ ወህኒ ቤት ተዛውረው ቁም ስቅላቸውን እያዩ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡ ሱዳን እየጋመ ያለው የለውጥ ቋያ ኤርትራ ውስጥም መቀጣጠሉ አይቀርም እየተባለ ነው፡፡ ከእንግዲህ ኢሳያስ እያሰረና እየገደለ የኤርትራ ሕዝብን እየረገጠ የመግዛት የመጨረሻው  ምዕራፉ  ሊዘጋ መቃረቡን  በርካቶች ያስረዳሉ።

#የሁለተኛ ደረጃ መምህራን ስብሰባ መዘጋጀቱ ተሰማ
 ባሳለፍነው  ሳምንት  ከተለያዩ  የሁለተኛ  ደረጃ  ትምህርት  ቤቶች  ከተገኘው መረጃ  ዘረኛው  አገዛዝ  የመምህራን ተወካዮችን ለመሰብሰብ እቅድ መያዙን ነው፡፡ የስብሰባው አስፈላጊነት ከትምህርት ሥራ ጋር ቀጥኛ ተዛምዶ ባለው ርእስ  ላይ  ሳይሆን  ዋነኛው ጉዳይ  እየተስፋፋ  ያለውን  የጎሳ  ግጭት  ለማስቆም  መምህራንን  “በሰላም  ካድሬነት” ለመጠቀም ታስቦ ነው ተብሏል፡፡ በስብሰባው መምህራን የደሞዝ ጭማሪን፣ የትምህርት ጥራትን፣ በትምህርት ቤቶች የተሰንራፋውን የሙስና ወረርሽኝን፣ ከሁሉም በላይ ህጋዊ ማህበራቸው የተገፈፈው የመንቀሳቀስ መብቱ እንዲከበርና አሁን በመምህራን  ስም የማህበሩ መሪ ነን የሚሉት በወያኔ የተሰየሙ በመሆናቸው እንዲሰናበቱ አንስተው መሟገታቸው አይቀርም ተብሏል።

#በአዲስ አበባ የዳቦ ዋጋ ጭማሪ ሊደረግ መሆኑ እየተሰማ ነው
 በርካታ  የዳቦ  መጋገሪያዎች  በህገ­ወጥነት  የዳቦ  ዋጋ  ጨምረዋል፣  የዳቦውንም መጠን  ቀንሰዋል፡፡ በተጨማሪም ብዙዎቹ ዳቦ መጋገሪያዎች የዳቦ አመራረታቸውና የሚያመርቱበት  ሁኔታና  ቦታ  ለጤና  በጣም  ጠንቅ  ናቸው ተብሏል፡፡ ይህን  ሁኔታ ለማስተካከል  ምንም  ዓይነት  እርምጃ  ሳይወሰድ  ባለበት  የዋጋ  ጭማሪ  ለማድረግ በሕግ እንዲፈቀድ ከዳቦ ጋጋሪዎች የቀረበው ጥያቄ እያነጋገረ ነው ተብሏል፡፡ ይህ የዳቦ ዋጋ ጭማሪ በእርግጥም ከአጠቃላይ ገበያው  ጋር  በተያያዥነት  መቅረቡ ሲታወቅ ዋናው  ጉዳይ  ግን  ከአብዛኛው  ሕዝብ  አቅም  ጋር  ሊገናዘብ  ይገባዋል የሚል አስተያየት ሲሰጥ ይሰማል፡፡ ጭማሪው ከነዳጅ ዋጋ፣ ከውጪ ምንዛሪ፣ ከቤት ኪራይ፣ ከሠራተኛ ደሞዝ ጋር በተያያዘ የቀረበ ሲሆን በሌላ አንፃር ደግሞ የሕዝቡ የመግዛት አቅም ደካማ በመሆኑ ይህ ዳቦ ላይ የሚደረግ ጭማሪ በሱዳንና በቱኒዚያ የተከሰቱ አመጾችን ሊያስከትል ይችላል የሚል ግምት እየተሰጠ ነው ተብሏል።

#ባንኮች ግዙፍ ብድሮችን ለመፈጸም የአቅም ውስንነት ስላላቸው ግንባታዎች እየተስተጓጎሉ መሆኑ ታወቀ
 እንደሚታወቀው  ለግዙፍ  የግንባታ  ሥራዎች  የግል  ባንኮች  አቅማቸው  ደካማ በመሆኑ  በማበደሩ  ተሰማርተው አያውቁም፡፡ ለግዙፍ የሆቴል ግንባታዎች ብድር የሚያቀርቡት ሁለቱ የመንግሥት ባንኮች ንግድ ባንክና ልማት ባንክ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ሁለቱም ባንኮች አቅማቸው በመመናመኑ ምክንያት ሠላሳ ዓለም አቀፍ ሆቴሎች ገንባታቸው መስተጓጎሉ ታውቋል፡፡ አንዳንዶቹ ሆቴሎች የማጠናቀቂያ ማለትም  ቁሳቁሶችን  ከውጪ  ማስመጫ ገንዘብ  የሚያስፈልጋቸው  መሆኑን  አቅርበው  ገንዘብ ባለመኖሩ የጠየቁትን ብድር ባለማግኘታቸው ጊዜ  እየነጎደ አላግባብ ለተጨማሪ ክፍያ እየተዳረጉ መሆናቸውን በምሬት ያስረዳሉ

#ከኢትዮጵያ ህዝብ እሩቡ በአእምሮ ህመም እንደሚሰቃይ ተገለጸ
 በቅርቡ ይፋ ከተደረገ አንድ በአእምሮ ህሙማን ላይ ከተደረገ ጥናት መገንዘብ የተቻለው በበሽታው የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር  እየጨመረ  በመሄድ ላይ መሆኑን  ነው፡፡ ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድ  አራተኛ  የሚሆነው በተለያዩ የአእምሮ  ህመሞች እንደሚጠቃ  በጥናቱ  የተጠቆመው  አስደንጋጭ ነው ተብሏል፡፡  የበሽታው መስፋፋት መንስኤ ሆነው የቀረቡት የአልኮና የአደንዛዥ እጾች ሱሰኝነት፣ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው  የቤተሰብ  መዋቅር  መፈራረስ፣ የሥራ  ዋስትና  አለመኖር፣ የአእምሮ  ሀኪሞችና የስነልቦና  ባለሙያዎች  እጥረት፣  ከሁሉም  በላይ  ደግሞ  የሰላማዊ ሁኔታ መጥፋት እንደሆኑ መረዳት ተችሏል።

#ለዝርዝር ዜናዎች > ከታች ይጫኑ (to listen detail news click below)
To Read: http://www.finote.org/Fikarezena.pdf
To Listen PART 1: http://www.finote.org/Today_Part1.mp3
You Tube: https://youtu.be/3cpghLpfk_U
47
How An Exiled Activist In Minnesota Helped Spur Big Political Changes In Ethiopia
December 6, 20182:14 PM ET
Heard on All Things Considered

Eyder Peralta

Jawar Mohammed, 32, created the Oromia Media Network and used it to bludgeon one of the most brutal regimes on the African continent.
Maheder Haileselassie Tadese/AFP/Getty Images

In person, Jawar Mohammed is quieter, smaller than the big persona he has built online.

To see him, you arrive at what looks like an old embassy residence in Ethiopia's capital, Addis Ababa. It's hulking and white, multiple stories, surrounded by tall walls. You're frisked by plainclothes security officials and then guided through a series of empty rooms, one covered in Oriental rugs. Finally, you reach his small office, where he is sipping tea, monitoring his phones and keeping up with the latest political action on his laptop.

At 32, with a mischievous smile and a round, boyish face, he keeps the air of a startup CEO, but Jawar is without a doubt the most controversial man in Ethiopia. The previous government branded him a terrorist, because from exile in the U.S., he created a media network and used it to bludgeon that government — one of the most brutal regimes on the African continent.

The Ethiopian People's Revolutionary Democratic Front, the ruling party, was armed to the teeth and controlled the executive branch, Parliament and judiciary for almost three decades. An airtight intelligence operation meant there was little they didn't know, so any potential dissent was dealt with swiftly and violently. There is no comprehensive count, but human rights groups have for years decried vast abuses by the government.

People protest against the Ethiopian government during an Oromo festival in October 2017. Anti-government protests by young Oromo men began in 2015 and helped spur political change.
Zacharias Abubeker/AFP/Getty Images

"This was one of the most powerful regimes in Africa," Jawar tells NPR. "Supported by the West and China, Russia, together. Even a liberal like [Barack] Obama, who is committed to human rights and democracy, looked at them and said there is no way these guys are going to go." During a 2015 visit, and much to the dismay of Ethiopian civil society groups, President Obama was accommodating of the regime, even calling it "democratically elected."

But the regime had one big weakness: In a diverse country, it was mostly led by Tigrayans, a minority ethnic group that makes up less than 10 percent of the country's population. The Oromo — the largest ethnic group, representing more than a third of the population — had mostly been left out.

"[The Oromos] have been economically and politically, culturally marginalized for a long time, because the Oromos were always a threat to whoever was in power," Jawar says. "And to prevent Oromos from coming to power, to disempower them ... ridiculing them was very important, demoralizing them was very important."

Jawar, an Oromo, saw his opportunity. On his network, broadcasting from Minnesota to Ethiopia via satellite and social media, he decried injustice. He highlighted Oromo history and encouraged young Oromos to be proud of their culture.

"I called it the project of building collective self-esteem," he says.

The qeerroo protests

Confidence in their numbers — and in who they were — pushed protesters to the streets to demand better governance and equal representation from a minority-led government.

And it worked. Beginning in the fall of 2015, thousands of protesters — mostly young bachelors known as qeerroos in the Oromo language — organized boycotts and set up roadblocks, paralyzing commerce. Ethiopia is one of the fastest-growing economies in the world — its GDP expanding at breakneck pace — but the instability led to a 20 percent decrease in foreign direct investment. For a regime whose main promise was development, this was devastating.

Eventually, the Amhara, the second-biggest ethnic group in the country, joined the protests. The government crumbled with the resignation in February of Prime Minister Hailemariam Desalegn.

Abiy Ahmed (left) holds an Ethiopian flag with his predecessor, Hailemariam Desalegn, at the Ethiopian Parliament, following Ahmed's swearing-in ceremony as prime minister in April.
Zacharias Abubeker/AFP/Getty Images

In August, Jawar returned to Ethiopia as a hero. He had last been there in 2008. The government of new reformist Prime Minister Abiy Ahmed, an Oromo from the ruling coalition, dropped all terrorism charges against him, and Jawar transformed from an outside agitator, an activist, to a political figure with huge influence over the new government.

Thousands of people lined the streets, celebrating his return. But across the country, perhaps emboldened by their unlikely victory, young Oromos clashed violently with members of other ethnic groups, and the violence displaced hundreds of thousands of people.

On Twitter and in newspapers, critics wondered if the ethnically driven politics that helped push political change had become toxic — threatening to rip the country apart along ethnic lines.

Jawar brushes off those kinds of concerns, dismissing them as political barbs with no basis in reality.

"When you do things the way I do, you create a lot of losers," he says. "Of course you are going to have a lot of enemies."

"We were struggling for the whole Ethiopia"

Driving from Addis Ababa to Shashamane, you notice a couple of things: the vast factories quickly industrializing Ethiopia and the hordes of young, unemployed men hanging out on street corners, waiting for someone to give them any job.

Shashamane, a small town about a five-hour drive south of Addis Ababa, is in the heartland of the Oromia region and is one of the places where Jawar's theories about political activism came to life.

"You can call it the second Minnesota," Kemal Welyali says.

At the peak of the protest movement, images from Shashamane played all over Jawar's Oromia Media Network, showing young men running, crossing their arms in protest, or desolate streets during the nationwide strike earlier this year — not a single business open, not one truck shuttling goods out to the capital.

Ethiopian opposition leader Merera Gudina was freed from jail in January. In today's Ethiopia, he says, "There are a lot of clashes of dreams."
Eyder Peralta/NPR

Kemal played a central organizing role. He took every opportunity to speak about corruption and minority rule, even at funerals and weddings. It was time, he preached, to stand up to a cruel government. He says he spoke mostly to the older folks, because he knew when the young people took to the streets, they would need their elders' support.

Kemal stops his car in front of a strip mall. On the day Jawar came to Shashamane, in August, thousands showed up to welcome someone they viewed as their philosophical inspiration. But at some point, the crowd fixated on one man — a non-Oromo whom they accused of carrying a bomb.

Kemal points at a lamppost in front of him: That's where the crowd hung the man by his feet and beat him to death. No bomb was ever found.

"We were not the ones who hung him," Kemal says, blaming another group for trying to spark a new conflict between young Oromos and police.

Either way, as images of a mob of young men surrounding the man's limp body spread across Ethiopia, it sparked fears that the Oromos' uprising had empowered violent ethnic nationalism.

In the capital, the word qeerroo makes people shudder now. They are radicals, they say.

But Kemal says only people who don't know their movement brand them as radicals. Yes, he says, this movement emboldened Oromos and gave them pride, but that was part of a bigger plan. The point of this struggle, he says, was to first bring Oromos together to defeat the old regime and then bring along the rest of Ethiopia.

"Our struggle is to bring real democracy," he says. "We weren't struggling for the Oromo tribe only. We were struggling for the whole Ethiopia."

"A vacuum in the middle"

Jawar left Ethiopia for a university in Singapore in 2003. Two years later, he moved to the United States; he studied political science at Stanford and received a master's in human rights studies at Columbia University.

As a student in the U.S., he was thinking and writing about Oromos in Ethiopia. In the mid-2000s, he led protests outside the State Department to bring attention to what he said was the mistreatment of Oromos at the hands of the Ethiopian state. He settled in Minnesota, where his wife, also Ethiopian, was a student.

Jawar was controversial among Ethiopians from the very beginning of his political activism. In 2009, he wrote an essay highly critical of the Oromo Liberation Front, then a separatist group that had struggled against Ethiopian regimes for decades. It was time to move on, he argued, because it was clear the OLF could no longer serve the aspirations of Oromos.

Jawar says he spent time studying nonviolent protests of the U.S. and India, and he paid close attention to the Arab Spring movements.

His big moment came about three years ago, when the Ethiopian government moved to expand the capital city, in essence taking more land from the people of Oromia.

That sparked huge street protests. At the same time, Jawar launched his media network, which gave young protesters a voice. His Facebook page garnered more than 1.5 million followers and he plastered his feed — and his satellite channel — with graphic content showing clashes between protesters and police.

Critics say he exaggerated what was happening in Ethiopia — that he inflated death tolls and even reported falsely that the Ethiopian government had used helicopter gunships to mow down Oromo worshippers during their most sacred holiday. During this period, he was deemed an enemy of the Ethiopian state and was no longer able to return home. His critics said he fanned the flames by framing a lot of this in ethnic terms — as a Tigrayan conspiracy against Oromos.

But Jawar sees his role through a more academic lens. He says as this protest movement unfolded, he and other Oromo leaders did recognize the potential for radicalization — and that's why they pushed for democracy.

More recent episodes of violence, he argues, don't stem from ethnic division. Instead, he says, this is what happens during political transitions.

He's calm and unemotional when he talks about the violence across the country.

"When you move from dictatorship to democracy, people move from fearing the guns to respecting the law," he says. "But there is a vacuum in the middle; there is a gap."

The "not negotiable" demands

As Kemal pulls out of the Shashamane strip mall, a heavy rain begins to fall.

For years, Kemal was on the run. The previous government tracked his cellphones, so he switched SIM cards hundreds of times. He would stay in a town for a few days, talk to leaders about nonviolent protests and then move elsewhere.

His family stayed in Shashamane, and he encouraged his 18-year-old son, Wetumusa Kemal, to go out into the streets.

He motions to Wetumusa to show this reporter the consequences of that. Wetumusa rolls up his pant leg, revealing a scar from a bullet wound on his left knee.

During the struggle, Wetumusa says, the military was everywhere. It surrounded schools and beat the students in classrooms. Sometimes soldiers would round them up during protests and send them to re-education camps.

"They told us to lie down, then they beat us with the sticks and they ran over us with their big shoes," he says.

Even if you weren't protesting, he says, if the military determined you were young and Oromo, you would face a beating or imprisonment.

Over the past few years, human rights groups estimate, more than 1,000 Ethiopians were killed by the state and tens of thousands were thrown into detention centers, where torture, as Wetumusa describes, was common.

This, father and son both agree, was a painful struggle, but they have won. Their victory, they say, gives them a right to two other demands: that the capital should once again be administered by Oromia, and that the Oromo language should displace Amharic as the country's official language.

Reminded that those two demands could prove highly combustible, Kemal responds without hesitating: "They are not negotiable."

"Clashes of dreams"

The issue of Addis Ababa is not simple. It has long represented the clash between the Oromo majority and the ruling class, a point of contention since the late 1800s, when Emperor Menelik II — an Amhara — staked claim to what Oromos called Finfinne.

Today, Addis Ababa is a cosmopolitan city, a federal cutout in the middle of Oromia that is home to all ethnic groups and a source of much government revenue.

Jawar, though, seems unconcerned about the capital's future. Unlike Kemal, he leaves room for negotiation — the federal government and the city's multiethnic residents have rights that should be respected, he says — but to him, the big issue is already settled: The territory of Addis Ababa has to be returned to the Oromos.

"I don't see how that can be a radical proposition," he says, "if there is almost 100 percent consensus among Oromos."

Merera Gudina, an Oromo and once the country's most prominent opposition politician, was released from prison thanks in large part to unrelenting qeerroo protests. These unresolved issues are the biggest danger in Ethiopia, he warns.

"There are a lot of clashes of dreams," he says. If they can't be negotiated, he warns, the country will crumble.

One minute, Jawar can be a hard-liner who dismisses any negotiation, and the next, a pragmatist who insists controversial issues can be resolved once the Ethiopian government becomes "legitimate" and people come to respect the law.

In Ethiopia now, "No one has legitimacy," he says. Not even Ahmed, the prime minister, who came to his position by a decision of the ruling party rather than by popular vote.

The uprising, Jawar says, was never about creating an Oromo state, but it was certainly about Oromos asserting their rights.

"When I was in America, I was Oromo; I was African; I was American," he says. "We shouldn't be forcing people to choose; we should create a condition of complementary identities."

In his mind, free, fair and credible elections are the answer.

"Elections will enable us to have legitimate representatives of the various ethnic groups and a real ethnic bargain will begin," he says. "There will be conflicts; there will tensions. There will be communal violence every now and then, but that violence can be contained because you will have legitimate representatives."

And if the process is fair, he says, he is willing to accept whoever comes to power — Oromo or not.

"We fought for a democratic government," he says. "Not for a popular government. We don't care who is going to rule this place, but that person has to have the consent our people expressed through the ballots."

https://www.npr.org/2018/12/06/672196480/how-an-exiled-activist-in-minnesota-helped-spur-big-political-changes-in-Ethiopia
48
#Finote Democracy ፍካሬ ዜና -ኅዳር 23 ቀን 2011 ዓ.ም. (02 December 2018 Weekly NEWS SUMMARY)

#ርዕሰ ዜና #በወለጋ ቀውሱ እንደቀጠለ መሆኑ ተነገረ
#ጭንሀክሰን ሰቆቃዋ መደገሙ ተሰማ
#የሕገ­ወጥ የመሣሪያ ዝውውር አሳሳቢነቱ እየጨመረ መሆኑ ታወቀ #የአገዛዙ የንግድ ድርጅቶች በህግ ሊጠየቁ እንደሚገባቸው እየተነገረ ነው #የሥራ አጥ ወጣቶች ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ መሄዱን አንድ በጉዳዩ ላይ የተካሄደ ጥናት ጠቆመ

##ዝርዝር ዜናዎች##

#በወለጋ ቀውሱ እንደቀጠለ መሆኑ ተነገረ
 ከመንፈቅ  በላይ  እያስቆጠረ  ያለው  የምዕራብ  ወለጋና  የቤንሻንጉል  ጉሙዝ  አካባቢ  የጸጥታ  ሁኔታ  ከጌዜ  ወደ  ጊዜ እየተባበሰ መሄዱ  አካባቢውን ወደ  አልተጠበቀ ምስቅልቅል ቀውስ ሊያስገባ ይችላል  የሚል  ስጋት ማሳደሩ እየተነገረ
ነው  ተባለ፡፡  የቤንሻንጉል  ታጣቂ  ኃይል  መሆናቸው  የሚነገርላቸው  በቀስትና  በዘመናዊ  መሣሪያ  በአካባቢው  እየኖሩ የሚገኙትን ኦሮሚኛ ተናጋሪዎችን እና ሌሎችን ይውጡልን በሚል ቤቶች እያቃጠሉ፤ ንብረት እየዘረፉና ከብት እየነዱ፤ ሴቶችን እየደፈሩ፤ የሚሸሸውን ሕዝብ ከጀርባ ተኩስ በመክፈት በርካቶችን በአሰቃቂ ሁኔታ በመግደል ከመቶ ሺ በላይ ሕዝብ  መፈናቀሉ  እየተነገረ  ነው፡፡  ይህ  የሕዝብ  መፈናቀል  ለስድስት  ወራት  ያለማቋረጥ  መቀጠሉ  ዘረኛው  አገዛዝ በንፁሀን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን መከራ ለመታደግ ምንም ዐይነት እርምጃ አለመውሰዱ በአካባቢው የሚካሄደው ግጭት ወደ  የለየለት  የእርስ  በእርስ  ግጭት  እየሆነ  እንደሆነ  ሁኔታውን  የሚከታተሉ  የፖለቲካ  አዋቂዎች  ያስረዳሉ፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት ከአስር የሚበልጡ የኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ አባላት መገደላቸውን ተከትሎ በአምቦ፣ በነቀምት፣ …ወዘተ የተቃውሞ  ሰልፎች  መካሄዳቸው  ተሰምቷል፡፡  ለጉዳዩ  ትኩረት  እንደተሰጠው  ለማስመሰል  ኦዴፓ  ስብሳባ  ተቀምጦ ውሳኔ ማስተላለፉ ብዙዎችን  እያነጋገረ መሆኑ ታውቋል፡፡  እንዲህ ያለው  ሀገራዊ ጉዳይ  እንጂ  የአንድን አካባቢ ብቻ የሚመለከት  ባለመሆኑ ሊወሰድ  የሚገባው  እርምጃ  በሀገር  ደረጃ ሊሆን ይገባው  ነበር ተብሏል፡፡  በነቀምት  በተለያዩ መጠለያዎች  ተጠልለው  የሚገኙ  ተፈናቃዮች  እስካሁን  ተገቢ  የሆነ  ትኩረት  ባለማግኘታቸው  በቂ  እርዳታ፣  የህፃናት ምግብ፣ መድሀኒቶች፣ አልባሳት፣ …ወዘተ ባለማግኘታቸው ስቃያቸውን እያባባሰው መሆኑን ሲገልጹ ተሰምተዋል፡፡ ይህ ሁኔታ  በዚህ  ከቀጠለ፣  ከዚህ  ቀደም  ከምሥራቅና  ከምዕራብ  ሐረርጌ  የተፈናቀሉ  ለዓመታት  ወደ  ቀያቸው  ሳይመለሱ ተበታትነው እንደቀሩት ወገኞች ያለ ክስተት መከሰቱ አይቀሬ መሆኑን በርካቶች ያስረዳሉ።

#ጭንሀክሰን ሰቆቃዋ መደገሙ ተሰማ
 በጭንሀክሰን  ባሳለፍነው  ሳምንት  በኗሪዎቹ  ላይ  በተከሰተ  ድንገተኛ  ወረራና  ጥቃት  ከአስራ  አንድ  ሰዎች  በላይ መገደላቸውን መረዳት ተችሏል፡፡ የአካባቢው ሰላም መደፍረስ አሁን በእስር የሚገኘው አብዲ ኢሌ የሚያዛቸው ጀሌዎች የሚፈጽሙት  እንደነበርና  ሁኔታ  ሰውየው  ከታሰረ  ወዲህ  የሶማሌ  ልዩ  ኃይል  የተባለው ሙሉ  በሙሉ ትጥቁን  እንደፈታና  መዋቅሩ  መፈራረሱ  መነገሩ  የሚታወስ  ነው  ተብሏል፡፡  የሰሞኑን  ጥቃት  የፈጸመው  ኃይል ማንነቱ  ያልታወቀ  ተብሎ  መገለጹ  በርካቶች  ሁኔታውን  በጥሞና  መመልከት  እንደሚያስፈልግ  ያስረዳሉ፡፡  ይህ ማንነቱ  ያልታወቀ  የተባለው  ኃይልን  ከሶማሌው  ሽብርተኛ  ቡድን  አልሸባብ  ጋር  የሚያያይዙት  ጥቂቶች አለመሆናቸውን መገንዘብ ተችሏል።

#የሕገ­ወጥ የመሣሪያ ዝውውር አሳሳቢነቱ እየጨመረ መሆኑ ታወቀ
 በኢትዮጵያ ከምንጊዜውም በላይ በትንሹ ባለፉት ስድስት ወራት የጦር መሳሪያ ዝውውር ታይቶ በማታወቅ ሁኔታ በገፍ  ከጠረፍ  ወደ  መሀል  ሀገር፣  ከመሀል  ሀገር  ወደ  ተለያዩ  አቅጣጫዎች  እየተሰራጨ  መሆኑን  በተለያዩ  ጊዜያት ከፖሊስ  ከተሰጡ መግለጫዎች መገንዘብ  ተችሏል፡፡  የመሣሪያዎቹ  ዐይነቶች  በብዛት  ቱርክ ሠራሽ  ሽጉጦች፣ የእጅ ቦምቦች  እና  ክላሽን  ኮቮች  መሆናቸው  ጉዳዩን  አሳሳቢ  ያደርገዋል  ተብሏል፡፡  ሰሞኑን  ከታማኝ  ምንጭ  የተገኘው መረጃ አዲስ አበባ ውስጥ ተቀጣጣይ ቦምቦች መያዛቸው የመሣሪያ ዝውውሩ ጦስ ማስከተሉ አይቀርም የሚል ስጋት ማሳደሩ እያነጋገረ ነው ተብሏል።

#የአገዛዙ የንግድ ድርጅቶች በህግ ሊጠየቁ እንደሚገባቸው እየተነገረ ነው
 የዘረኛው አገዛዝ የፖለቲካ ድርጅቶች በሕዝብ ስም እና የፖለቲካ ድርጅቶቻቸውን የገንዘብ አቅም ለማጠናከር በሚል ብአዴን  በጥረት፣  ህወሓት  በኤፈርት፣  ኦህዴድ  በዲንሾ፣  …ወዘተ  ስም  የሚንቀሳቀሱት  የንግድ  ድርጅቶችን  በሕግ አግባብ  አደብ ማስያዝ  የግድ  ነው ተብሏል፡፡  እነዚህ  የንግድ ድርጅቶች  እራሱ  አገዛዙ  የደነገገውን ሕግ ተላልፈው የተቋቋሙና ለድርጅቶቹ የበላዮች ከፍተኛ የገንዘብ ምንጭ መሆናቸው በስፋት ይነገራል፡፡  በሌላ አንፃርም እነዚህ የአገዛዙ  የፖለቲካ  ድርጅቶች  የንግድ  ተቋማት  የንግዱን  እንቅስቃሴ  እድገት  በከፋ  ሁኔታ  እየተጸናወቱት በመሆናቸውና  ለበርካታ  የሀገር  ገንዘብ  ዘረፋና  በውጪ  ሀገራት  መከማቸት  እንደ  ዋነኛ  መተላፊያነት  እያገለገሉ መሆናቸውን በርካቶች ሲገልጹ ይሰማል፡፡ በርካታ የፖለቲካ አዋቂዎች እነዚህ የንግድ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ህዝብ አንጡራ ሀብት የተቋቋሙ በመሆናቸውና የጥቂት ፈላጭ ቆራጮች የሀብት ምንጭ በመሆናቸው ድርጅቶቹ ሊከበሩና ለህዝብ አገልግሎት እንዲውሉ ሊደረግ ይገባል ተብሏል።

#የሥራ አጥ ወጣቶች ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ መሄዱን አንድ በጉዳዩ ላይ የተካሄደ ጥናት ጠቆመ
 በድፍን  ሀገሪቱ  ወጣቶች  ከተለያዩ  የትምህርት  ተቋማት  ተመርቀው  ከወጡ  በኋላ  ሥራ  ማግኘት  ፍዳ  መሆኑን በምሬት ሲያስረዱ  ይሰማል፡፡  በተለያዩ  የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች  ለመቀጠር  አንዱ  ከዘረኛው  አገዛዝ  የፖለቲካ
ድርጅቶች ውስጥ የአንዱ አባል መሆን ከመመዘኛዎቹ ውስጥ ዋነኛው መሆኑ ይነገራል፡፡ በሁለተኛነት የሚጠቀሰው ሥራ  ለማግኘት  ዝምድና፣  አምቻ፣  መንደርተኝነት፣  ጉቦ  መክፈል፣  …ወዘተ  የሚጠቀሱ  ሲሆኑ  እነዚህም  ብዙዎቹን ለሥራ አጥነት እየዳረጉ ያሉ መሆናቸውን በሥራ ፍለጋ የደከሙ ወጣቶች ያስረዳሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት ደግሞ የህንፃ ግንባታዎች በተለያዩ ሰበቦች በመቋረጣቸውና በመቆማቸው የተለያዩ የህንፃ ግንባታ ባለሙያዎች ከሥራ እየተቀነሱና ለችግር በመጋለጣቸው የሥራ አጥ ወጣቶችን ቁጥር በመጨመሩ በኩል የራሱ ተጽእኖ እንዳለው ከአንድ በጉዳዩ ላይ ከተካሄደ ጥናት መገንዘብ መቻሉን ብዙዎች ያስረዳሉ።

#ለዝርዝር ዜናዎች > ከታች ይጫኑ (to listen detail news click below)

To Read: http://www.finote.org/Fikarezena.pdf
To Listen PART 1: http://www.finote.org/Today_Part1.mp3
You Tube: https://youtu.be/CBTKR908OVQ
49
Arts, Culture and Community Affairs / Habesha Cult
« Last post by staff3 on November 20, 2018, 07:38:22 AM »
ውድ የድረ ገጻችን ተጠቃሚ ስለላኩልን መልዕክት እናመሰግናለን

Habesha Cult
   
   
ውድ የድረ ገጻችን ተጠቃሚ ስለላኩልን መልዕክት እናመሰግናለን፥፥
በቅርብ የወጡ ሪፖርቶችን ከታች በሚገኙት ሊንኮችን በመጠቀም ማየት ይችላሉ

http://habeshacults.com/pages/ayu-chufa.html
http://habeshacults.com/pages/fakejesus.html
http://habeshacults.com/pages/fakejesus1.html
http://habeshacults.com/pages/fakejesus2.html
http://habeshacults.com/pages/fakejesus3.html
http://habeshacults.com/pages/victims.html


50
National Affairs: Civics, Activism, Politics etc... / Ethiopiachin Vol 3 No 2 Issue
« Last post by staff3 on November 18, 2018, 07:50:09 PM »
Ethiopiachin Vol 3 No 2 Issue
Also use the link below

http://www.ethiopiachen.org/images/pdf/Eth_Vol3/070311_1H1H-Ethiopiachin-Vol-3-No-2.pdf

To listen the audio use the link below.

https://www.youtube.com/watch?v=-iPg6ugTanE

Long Live Ethiopia!
God Bless Ethiopia!
AHAH Ethiopiachin
Pages: 1 2 3 4 [5] 6 7 8 9 10