Recent Posts

Pages: 1 2 3 [4] 5 6 7 8 9 10
31
ዱላችን በጃችን - በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ ዐድማ ስለመጥራት
ይነጋል በላቸው

ውድ ኢትዮጵያውያን በያላችሁበት ሰላምታየ ይድረሳችሁ፡፡ የኢትዮጵያ አምላክ በምሕረት ዐይኖቹ እንዲያየን እንጸልይ፤ በጸሎትና በንስሃ የማይፈታ ችግር የለምና ፊታችንን ወደርሱ እናዙር፡፡ ብዙዎቻችን ጆሮ ዳባ ያልነው የምንመስለው የሀገራችን ወቅታዊ ችግር እጅግ ከባድና ፈታኝ ነውና በየሃይማኖታችን ሱባኤ ገብተን እንጸልይ፡፡ ከፈሰሰ አይታፈስም፡፡ አደጋ ውስጥ ነን!!
አንድ የዐድማ ጥሪና ጥቂት ማሳሰቢያዎች አሉኝ፡፡

1. የሁላችን ሊሆን የሚገባው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ልክ እንደወያኔዎች ጊዜ ሁሉ በጎሠኝነት ባህር ተዘፍቆ ከአወቃቀሩና ከቅጥር አፈጻጸሙ ጀምሮ እየሠራው ያለውን የዘረኝነት ዕኩይ ድርጊት በአግራሞት እየተከታተልን ነው፡፡ በእግረ መንገድም ዐይን አውጣነትና ይሉኝታ-ቢስነት ወይም ሀፍረተ-ቢስነት በነገድ የማይከለሉ የሰው ልጆች የወል እርጉም ሀብቶች መሆናቸውን እየተገነዘብን ነው፡፡ ከወያኔ በላይ ይሉኝታቢስ የለም ብለን በድፍረት የተከራከርን እኔን መሰል ሰዎች በጊዜው ኦህዲዳዊ ተግባር ክፉኛ በሀፍረት ልንሸማቀቀቅና አቋማችንን ልናስተካክል ተገደናል፡፡ ከ58 የኢ. ን. ባንክ የሥራ ኃላፊዎች በጥቂት ወራት የሹመት አሰጣጥ ጊዜ ውስጥ 31ዱ ኦሮሞዎች ሆነው ከተገኙ አሠራሩ የልምድና ችሎታ ሳይሆን የዘረኝነት መሆኑ ሊካድ አይገባም፡፡ በሌሎች የመንግሥት የሥራ ዘርፎችም ሁኔታው ከዚህ ቢከፋ እንጂ እንደማይሻል እየሰማን ነው - በብዙ ቦታዎች በሚከናወኑ የውስጥና የውጭ ውድድሮች አማራና ሌሎች ዜጎች ውድድሩን ካለፉ ኦሮሞ እስኪገኝ መዝገቡ ይያዛል ወይም በዝውውርና በዕድገት ስም ከሌሎች የኦሮሞ ክልል በመጡ የጎሣው አባላት እንዲያዝ ይደረጋል - ያለ በቂ ችሎታና ልምድ እንዲሁም የትምህርት ደረጃ ( አለቃ ገ/ሃና በቤታቸው ሰልችቷቸው እጓደኛቸው ቤት የተሻለ ምግብ የሚያገኙ መስሏቸው ቢሄዱ ያቺው በቤታቸው የጠሏት ሽሮ ትሁን ጎመን በጓደኛቸውም ቤት ስትቀርብላቸው “በየት ዞረሽ ቀደምሽኝ” እንዳሉት የኛም እንደዚያው ሆኖኣል)፡፡  ይባስ ብለው እነዚሁ ዘረኛ የባንኩ የሥራ ኃላፊዎች እነሱ የማፈናቀል አበጋዞች ሆነው ለሚተውኑት አሳዛኝ ትያትር 36 ሚሊዮን ብር አካባቢ ለክልላቸው ያላንዳች ሀፍረት ሲመድቡ ለእውነተኞቹ የአማራ ተፈናቃዮች ግን 4 ሚሊዮን ብር ብቻ መድበው “እንዳያማህ ጥራው፣ እንዳይበላ ግፋው” የሚለውን ልጨኛ ብሂል እያስታወሱን ነው፡፡ ይህ ነገር አንድም በማንአለብኝት ላይ የተመሠረተ ድንቁርናና ንቀት ነው አለዚያም ዘመኑን ያልዋጀ የሞኞች ቁጭበሉ አጉል ሙከራ ነው፡፡ “በቅሎ ገመዷን በጠሰች…” ቢሉ….፡፡ ፉከራና ማስፈራሪያ እንዳይመስላችሁ - ዕጥፍ ድርብ ይከፍሏታል፡፡

ስለዚህ ይህ ሸውራራ የዘረኝነት አካሄድ እስኪስተካከል ጤነኛ ዜጎች ነን የምንል ሁሉ በዚህ ባንክ እንዳንጠቀም ግፈኞችና ዐረመኔዎች በሚመጠምጡት የኢትዮጵያችን ዕድለቢስ ጡቶች እማጸናችኋለሁ፡፡ በዚህ ባንክ የምንጠቀም ዜጎች ዛሬ ነገና ትንሽ ነው ብዙ ነው ሳንል ያለንን ገንዘብ በማውጣት በኢትዮጵያዊነታቸው በማይታሙ ባንኮች እናስገባ፤ በነሱም እንገልገል፡፡ ዘረኛ ባንኮችን በዚህ መልክ አደብ ማስገዛት ይቻላል፡፡ ይህ ትግል አንዱ የሰላማዊ ትግል ገጽታ ነውና አንቦዝን፡፡

የኢትየጵያ ንግድ ባንክ ዱሮውንም የሚገለገሉበት ኢትዮጵያውያን በተለይም አማሮች እንጂ ሌላውና በዘረኝነት መርዝ የተለከፈው ሀብታምና ተራ ዜጋ ዘሩን እያነፈነፈ ነው “የኔ ናቸው “ በሚላቸው ባንኮች ገንዘቡን ያስገባና ያወጣ የነበረው፡፡ ለምሣሌ አዋሽ ባንክ እያለለት ዘረኛ ኦሮሞ በሌላ ባንክ አይጠቀምም፡፡ ወጋገንና አንበሣ ባንኮች እያሉለት ዘረኛ ትግሬ በሌላ ባንክ አይጠቀምም፡፡ኅያዋን ሰዎች ብቻ ሳንሆን ባንኮችም በዘረኝነት የሚሰቃዩ ግዑዝ ነገሮች ናቸው፡፡ ኦህዲድ የቀማን ብቸኛ መጠቀሚያችንን ነው፡፡ እነሱ ዱሮውንም የማይጠቀሙበትን ባንክ ነው ያሳጡን፡፡ የግፍ ግፍ ነው፡፡ ስለዚህ ንጹሕ ኢትዮጵያውያን ይህን ባንክ መጠቀም ቢያቆሙ ንግድ ባንክ በቂጡ እንዘጭ እንደሚል ግልጽ ነው፡፡

2. ለፌስ ቡክ ተጠቃሚዎች የምለው አለኝ፡፡

ፌስቡክ ጥሩ ነው፡፡ ጥሩም አይደለም፡፡ በዚህ ማኅበራዊ ሚዲያ የሚባለውን ሁሉ እንደ እውነት ከተቀበልን እናብዳለን ወይም እንታመማለን፡፡ ለምሣሌ ከደቂቃዎች በፊት ከፍቼ ስመለከት “ኦሮሞና ትግሬ ወደው አይደለም አማራ ከብት ነው የሚሉት ከከብትም ከብት ነው፡፡ እንኩዋን አዲስ አበባ ተወለድኩ፡፡” የሚል አነበብኩ፡፡ “ከሰደበኝ ስድቤን አምጥቶ የነገረኝ” ለሚለው ወቀሳ እንኳን የማይበቃ እጅግ የወረደ “ስድብ” ስለሆነ ነው እንዳለ ያስቀመጥኩት፡፡ እናም እንዲህ ያለ አርቲ ቡርቲ የሚጽፉ “ሰዎች” ወያኔም ይመድባቸው፣ ኦነግና ኦህዲድም ድርጎ እየከፈሉ ያሰማሯቸው፣ በአእምሮ የማሰብ ችሎታ ማነስም ተገደው ከራሳቸው ያፍልቁት … በንቀት ስቀንባቸው መተው እንጂ ከነሱ ጋር መመላለስና መናደድ ዓላማቸውን እንደማሳካት ነው - ከነሱ ጋር መናቆር ሥራ ፈትነት እንጂ ገምቢ አይደለም፡፡ ማንም ይሁኑ ማን፣ ምድርም ይላካቸው ሰማይ - እነዚህን ዓይነት ወራዳ ሰዎች መከተል አውቆ ገደል እንደመግባት ነው፡፡ በሚባለው ሁሉ እየተወሰድን ወርቃማ ጊዜያችንን በከንቱ ማባከን የለብንም፡፡ ብዙ ባለጌና ዋልጌ በሞላባት ምድር ሁሉም ጻዲቅ እንዲሆን መጠበቅ የዋህነት ነው፡፡

ይህን እውነት ደግሞ እንረዳ፡- በአማራ ስም ኦሮሞንና ትግሬን ከአማራ ለማጣላት፣ በትግሬ ስም ትግሬንና አማራን ከኦሮሞ ለማጣላት፣ በኦሮሞ ስም ኦሮሞንና አማራን ለማጣላት የዱሮ ተረቶችንና አባባሎችን ሳይቀር በመጥቀስ ሰይጣናዊ ዘር የሚዘሩና ዕልቂት ለማፈስ የሚቋምጡ የሳይበር ጦርነት ፊታውራሪዎች ሞልተዋል - አስፈላጊው ሥልጠና ተሰጥቷቸውና ወፋፍራም ደሞዝ ተቆርጦላቸው፡፡ ስለዚህ አማራም ሆነ ትግሬ፣ ኦሮሞም ሆነ ጉራጌ፣ ሶማሌም ሆነ ከምባታ ይህን ዓይነቱን የተንኮለኞችና የሸረኞች መቀስ ንቆ በመተው አንድነቱን ማጽናት ይገባዋል፡፡ የተባለውን ነገር ሁሉ እንደወረደ መቀበል ወደ ጥፋት ይወስደናል እንጂ የምንፈልገውን የጋራ ልማትና ሰላም አያመጣልንም - ጎሣዊ መበሻሸቅ ደግሞ በየትም ሀገር ያለና የነበረ ነውና ባለፈ የሞተ ታሪክ አንነታረክ፡፡
ለክፉዎች በር አንክፈት፡፡ አንዱ ነገድ ተበድሎና ተጠቅቶ ሌላው ሰላምና መረጋጋት አይኖረውም፡፡ የሰላም አለመኖር ደግሞ ሁላችንንም በእኩል ይጎዳልና በጠላቶቻችን መረብ እየገባን ከመተላለቅ መቆጠብ አለብን፡፡ የፌስ ቡክ የስድብና የዘለፋ ዘመቻቸውን የምናከሽፈው ንቀን በመተው እንጂ በመናደድና እርስ በርስ በመነቋቆር አይደለም - ይሄ እነሱን  የልብ ልብ እየሰጠ ይበልጥ ያጠናክራቸዋል፡፡ በዚህ ረገድ ኢትዮጵያውያን የኦሮሞ፣ የአማራና የትግሬ አክቲቪስቶች ልትጫወቱት የምትችሉት አወንታዊ ሚና ከፍተኛ ነውና እየተከታተላችሁ ወጥመዶችን በጣጥሱ፡፡  ከዚህ ዓይነቱ ውኃ የማያነሣ አክሳሪ አካሄድ እናንተ ራሳችሁም ተጠበቁ፡፡ሁሉን ነገር ሁለቴ በማሰብ እናከናውን፡፡

በመጨረሻም ማለት የምፈልገው በሃሳብ የበላይነት እንጂ በዱላና በቡጢ አንመን፡፡ ለምሣሌ አንድ የፖለቲካ ቡድን ስብሰባ ቢጠራ ስብሰባው እንዳይካሄድ ሁከት መፍጠር ሳይሆን በስብሰባው ተገኝቶ ስህተቱን በመረጃና በማስረጃ አስደግፎ በመናገር ወይም ሌላ ስብሰባ በመጥራት ራቁቱን ማስቀረት ሲገባ ነገ ዕድሉን ብናገኝ የምናደርገውን ነገር ከአሁኑ ማሳየት ትልቅ የሀገር ሸክምና የትግልም እንቅፋት ነው፡፡ በዛቻና በማስፈራሪያ ለማስቆም መሞከር የያዝነው እውነት እንደሌለ ያሳብቃልና በዚህ ረገድ ጥንቃቄ ይደረግ፡፡ ሃሳብ ከጠበንጃ ይበልጣል፡፡ ሃሳብን ወደ መፍራትና በሃሳብም ወደመሸናነፍ ደረጃ ካልወጣን፤ ወደ ኃይልና ጉልበት አሸናፊነት ከወረድን ታጥቦ ጭቃ ነው፡፡ በኃይልና በጉልበት አንድን ዓላማ ለማሳካት መሞከር የስንኩል ወይም የደካማ አስተሳሰብ መግለጫ እንጂ የምጡቅ አእምሮ ባለቤትነትን አያሳይም፡፡ በዚህ መልክ ከተጓዝን ቅኔው ቢጎድልበት ቀረርቶ ጨመረበት እንደተባለው የየጁ ደብተራ መሆናችን ነው፡፡ በራስ የሚተማመንና አመክንዮ ያለው ወገን በኃይልና በቡጢ አያምንም፡፡ ዱላን ለማስወገድ አእምሮ እንጂ ዱላ አይጠቅምም፡፡ መጽሐፉ “ብዔል ዘቡል በብዔል ዘቡል አይወጣም” እንዲል፡፡ በአስተሳሰብ እንደግ፤ እንመንደግ፡፡ በከንቱም አንጠላለፍ፡፡

በተጨማሪም በስሜት እየተነዳን የዘረኝነት ስድቦችን ከማስወንጨፍ እንቆጠብ፡፡ ስንናደድ አንደበታችንንና ብዕራችንን መቆጣጠር ያቅተናልና ያኔ ቢቻለን ዝም እንበ፡፡ መጠጥና ንዴት ተመሳሳይነት አላቸውና ከነዚህ የውስጥ ድብቅ ገመናን አውጭዎች እንጠበቅ፡፡ ራሳችንን በጤናማ አስተሳሰብ እንገንባ፡፡ መርዘኛውንና አብሮ የማያኗኑረውን አስተሳሰብና ፍልስፍና በአንዴም ባይቻለን ቀስ በቀስ ከሰውነታችን እያወጣን በዘመናዊ አስተሳሰብ እንተካ፡፡ መሰዳደብና መጎነታተ ቂምን እየፈጠረ፣ የቆዬ ጥላቻን እያመረቀዘ ለበለጠ የጋራ መጠፋፋት ይዳርገናል እንጂ አንድም ጠቀሜታ የለውም፡፡ እንደኛ በነገርና በዱላ አቅን ሳይፈታተሸ ወደ ከፍተኛው የዓለማችን ሥልጣኔ ያመራ አንድም ሀገር እንደሌለ ደግሞ እንረዳ፡፡ የኛ ከሌሎቹ የሚለየው ባለንበት እየረገጥን ብቻ ሣይሆን ቁልቁል እየሸመጠጥን ሌላው ዓለም ካለፈው ብዙ ዘመናት ያስቆጠሩትን በምግብ እንኳን ራስን ወዳለመቻል እንስሳዊ ደረጃ መድረሳችን ነው፡፡ እናሳዝናለን፡፡ ወደፊት መራመድ ባይቻለን የነበረንን አንጻራዊ የአብሮነት ዘመን መልሰን በፍቅርና በመተሳሰብ ለመኖር እንጣር፡፡ በጎደለ ሙሉበት፤ ባጠፋሁ ይቅርታችሁን አትንፈጉኝ፡፡

yinegal3@gmail.com
34
Managing Ethiopia’s Unsettled Transition -by  International Crisis Group
https://www.ethiox.com/reports/Managing Ethiopia’s Unsettled Transition.pdf
35
News and Current Events / Humanities Institute
« Last post by staff3 on February 20, 2019, 01:00:06 PM »
Pan African Humanities Institute..event

https://www.ethiox.com/events/Humanities_Institute.pdf
36
Power shift creates new tensions and Tigrayan fears in Ethiopia
“Shaking up Ethiopia's government risks exacerbating several long-simmering ethnic rivalries”
James Jeffrey/IRIN
MEKELLE/ETHIOPIA, 14 February 2019

James Jeffrey

Freelance journalist specialising in Ethiopia and the Horn of Africa

Disagreements over land and resources between the 80 different ethnic groups in Ethiopia have often led to violence and mass displacement, but a fast and unprecedented shift of power led by reformist Prime Minister Abiy Ahmed is causing new strains, experts say.

“Ethnic tensions are the biggest problem for Ethiopia right now,” Tewodrose Tirfe, chair of the Amhara Association of America, a US-based advocacy group that played a significant role in lobbying the US government to censor the former regime. “You’ve got millions of people displaced – it’s a humanitarian crisis, and it could get out of control.”

During the first half of 2018, Ethiopia’s rate of 1.4 million new internally displaced people exceeded Syria’s. By the end of last year, the IDP population had mushroomed to nearly 2.4 million.

Tigrayans comprise just six percent of Ethiopia’s population of 100 million people but are perceived as a powerful minority because of their ethnic affinity with the Tigray People’s Liberation Front. The TPLF wielded almost unlimited power for more than two decades until reforms within the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front last year.

Since coming to power in April 2018, Prime Minister Abiy – from the Oromo ethnic group, Ethiopia’s largest – has brought major changes to the politics of the country, including an unprecedented redistribution of power within the EPRDF and away from the TPLF.
The politics of ethnic tensions

Despite the conflicting interests and disagreements between ethnic groups, the Ethiopian government has managed to keep the peace on a national scale. But that juggling act has shown signs of strain in recent years.

    “You’ve got millions of people displaced – it’s a humanitarian crisis, and it could get out of control.”

In 2017, an escalation in ethnic clashes in the Oromia and the Somali regions led to a spike in IDPs. This continued into 2018, when clashes between the Oromo and Gedeo ethnic groups displaced approximately 970,000 people in the West Guji and Gedeo zones of neighbouring Oromia and the Southern Nations, Nationalities and Peoples Region.

“The pace and scale of the change happening in Ethiopia is quite unbelievable,” said Ahmed Soliman, a research fellow with the Africa Programme at the London-based think tank Chatham House.

“The impact of inter-communal tensions and ethnic violence presents a serious challenge for the new leadership – in Tigray and elsewhere. Abiy's aggressive reform agenda has won praise, but shaking up Ethiopia's government risks exacerbating several long-simmering ethnic rivalries.”

Although clashes are sometimes fuelled by other disagreements, such as land or resources, people affected often claim that politicians across the spectrum use ethnic tensions as a means of divide and rule, or to consolidate their position as a perceived bulwark against further trouble.

“Sadly [around Ethiopia] ethnic bias and violence is affecting many people at the local level,” said a foreign humanitarian worker with an international organisation helping Ethiopian IDPs, who wished to remain anonymous due to the sensitivity of the issue. This includes fuelling the displacement crisis and worsening the humanitarian situation.

“The main humanitarian concern is that new displacements are occurring by the day, that due to the wide geographic scope, coordination and response in all locations is practically impossible,” the aid worker said.

“I would like to see more transparency as to what actions the government is taking to hold regional and zonal governments responsible for addressing conflict, for supporting reconciliation, and supporting humanitarian response.”
Tigray fears

Although Tigrayans constitute a relatively small part of overall IDP numbers so far, some Tigrayans fear the power shift in Addis Ababa away from the TPLF leaves them more vulnerable and exposed.

Already simmering anti-Tigrayan sentiments have led to violence, people told IRIN, from barricading roads and forcibly stopping traffic to looting and attacks on Tigrayan homes and businesses in the Amhara and Oromia regions.
James Jeffrey/IRIN
Tigrayans on the streets of Mekelle, the Tigray capital.

In the Tigray region’s capital of Mekelle, more than 750 kilometers north of the political changes taking place in Addis Ababa, many Tigrayans feel increasingly isolated from fellow Ethiopians.

“The rest of the country hates us,” Weyanay Gebremedhn, 25, told IRIN. Despite the reforms, Tigrayans say what hasn’t changed is the narrative that they are responsible by association for the ills of the TPLF.

Although he now struggles to find work, 35-year-old Huey Berhe, who does mostly odd jobs to pay the bills, said he felt safer living among his own community in Mekelle.

Huey said he had been a student at Jimma University in western Ethiopia, until growing ethnic tensions sparked fights on campus and led to Tigrayans being targeted. “I left my studies at Jimma after the trouble there,” he said. “It was bad – it’s not something I like to discuss.”
‘A better evil’

“There is a lot of [lies] and propaganda, and the TPLF has been made the scapegoat for all vice,” said Gebre Weleslase, a Tigrayan law professor at Mekelle University. He criticised Abiy for not condemning ethnic attacks, which he said had contributed to tens of thousands of Tigrayans leaving Amhara for Tigray in recent years.

But Amhara Association of America’s Tewodrose said the feeling of “hate” that Ethiopians have toward the TPLF “doesn’t extend to Tigrayans”.

“There is resentment toward them when other Ethiopians hear of rallies in Tigray supporting the TPLF, because that seems like they aren’t supporting reform efforts,” he said. “But that doesn’t lead to them being targeted, otherwise there would have been more displacements.”

☰ Read more: The complex Tigray evolution
 

Tigrayans, however, aren’t as reassured. Despite the vast majority enduring years of poverty and struggle under the TPLF, which should give them as many reasons as most Ethiopians to feel betrayed, even those Tigrayans who dislike the TPLF now say that turning to its patronage may be their only means of seeking protection.

“The TPLF political machinery extended everywhere in the country – into the judiciary, the universities… it became like something out of George Orwell’s ‘1984’,” Huey said. “But the fact is now the TPLF may represent a better evil as we are being made to feel so unsafe – they seem our only ally as we are threatened by the rest of the country.”

Others note that Abiy has a delicate balance to strike, especially for the sake of Tigrayans.

“The prime minister needs to be careful not to allow his targeting of anti-reform elements within the TPLF, to become an attack on the people of Tigray,” said Soliman.

“The region has a history of resolute peoples and will have to be included with all other regions, in order for Abiy to accomplish his goals of reconciliation, socio-political integration and regional development, as well as long-term peace with Eritrea.”

Although the government has a big role to play, some Ethiopians told IRIN it is essential for the general population to also face up to the inherent prejudices and problems that lie at the core of their society.

“It’s about the people being willing and taking individual responsibility – the government can’t do everything,” Weyanay said. “People need to read more and challenge their assumptions and get new perspectives.”

jj/si/ag


https://www.irinnews.org/analysis/2019/02/14/Ethiopia-ethnic-displacement-power-shift-raises-tensions?utm_source=IRIN+-+the+inside+story+on+emergencies&utm_campaign=c4d0178ee7-EMAIL_CAMPAIGN_2018_12_03_05_37_COPY_01&utm_medium=email&utm_term=0_d842d98289-c4d0178ee7-29270649
37
በዐማራ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ሊወሰዱ የሚገባቸው ከፍተኛ ጥንቃቄዎች!

Moresh Wegenie
   
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት    እሑድ የካቲት ፲ ቀን ፪ሺህ፲፩ዓ.ም.   ቅጽ ፯ቁጥር ፯
በዐማራ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ሊወሰዱ የሚገባቸው ከፍተኛ ጥንቃቄዎች!
https://www.ethiox.com/press/MWAO_IPR_PRESS_RELEASE_STRATEGY_V7N4_FEBRURAY17_2018.pdf


አንዱ ዐማራ ለሁሉ ዐማራ፤ ሁሉ ዐማራ ለአንዱ ዐማራ "
ትግሉ ይቀጥላል ፤ ዐማራነት ወንጀል አይደለምና!
እስከ መቼ ዋይታ! መከራና ለቅሶ!
በእኛ ላይ ይደርሳል መልሶ መላልሶ!


ሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት
38
National Affairs: Civics, Activism, Politics etc... / Policybrief Reform in Ethiopia
« Last post by staff3 on February 16, 2019, 10:55:57 AM »
Policy Brief Reform in Ethiopia

Reform in Ethiopia: Turning Promise into Progress
http://www.ethiox.com/articles2/policybrief_reform_in_ethiopia.pdf
40
«ዝምታችንን አትፈታተኑት!» ድምፃችን ይሰማ ከህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

January 30, 2019 – Konjit Sitotaw 

ድምፃችን ይሰማ

ከህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

«ዝምታችንን አትፈታተኑት!»

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ያለፈ በደል እያነሳን የምንቆዝምበት ዘመን ከተገባደደ ዓመታት ተቆጥረዋል። ነገር ግን ዛሬም ወደኋላ ሊጎትቱን የሚሹ የውስጥና የውጭ አካላት አሳፋሪ ሙከራዎችን ሲያደርጉ እያየን እንገኛለን። ለአገሪቱ ለውጥ ፋና ወጊ የሆነው ህዝበ ሙስሊም ይህንን በፍጹም አይቀበልም። ለአገሪቱ ወጣች የምትባል የትኛዋም የለውጥ ጸሃይ ህዝበ ሙስሊሙንም ትመለከታለች። እንደማትመለከት ለማስመሰል የሚደረግ ማንኛውም ጥረትም እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑ አያጠራጥርም።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የእምነት ተቋም ግንባታን ማሳለጥ የሚገባው መንግስት ቢሆንም በአዲስ አበባ እና በአካባቢዋ የሚገኙ የእምነት ተቋሞቻችንን «ህገ ወጥ» በሚል ሽፋን በተጠና መልኩ በዘመቻ የማፍረስ እንቅስቃሴ እየተካሄደ ነው። በህጋዊ መንገድ ተገነቡ የተባሉ የእምነት ተቋማት አሉ በማይባልባት አዲስ አበባ ባልተመጣጠነ ሁኔታ ተደሰቁው የሚገኙትን መስጊዶቻችንን ይባስ ብሎ ማፍረስ ዳግም ህዝበ ሙስሊሙን መተንኮስ ነው። ድርጊቱ እየተፈጸመ ያለው በአንዳንድ የመንግስት አካላት መሆኑ ሲታይ ደግሞ ዛሬም «የሃይማኖት አባት» እያሉ በቴሌቪዥን መስኮት ከማሳየት የዘለለ እኩልነት ስለመስፈኑ ዋስትና የሚሰጥ አይመስልም።

በተለያዩ ጊዜያት ሙስሊሙ በገዛ አገሩ የአኗኗር ሁኔታውንና ሃይማኖታዊ አስፈልጎቱን ያገናዘበ የአምልኮ እና የመቃብር ስፍራ እንዳያገኝ በማድረግ ስልታዊ በሆነ መልኩ በመከልከሉ ቦታ የማግኘት መብቱን በማጣት ለአምልኮ የማይመጥኑ ቦታዎችን በገንዘቡ እየገዛ እስከመጠቀም ደርሷል። ይህም ሆኖ ግን «ህገ ወጥ» እየተባለ ጥቃት ይፈጸምበታል። ቤተ አምልኮዎቹ ይፈርሳሉ። ምእመናን ይታሰራሉ። አካል ጉዳት ይደርስባቸዋል። ለህልፈተ-ህይወትም ይጋለጣሉ።

ህገ ወጥነት የሚደገፍ አይደለም። ነገር ግን በአገሪቱ ለቤተ እምነቶች ቦታ የሚያሰጥ ህግ በሌለበትና ህጉ ቢኖርም ያለአድልዎ ማስተናገድ በማይችልበት፣ በመስጊድነት የተያዙ በርካታ ትናንሽ ቦታዎችም ህጋዊ እንዳይደረጉ ሆን ተብሎ በሚቀረጽ ህግ በሚታገዱበት ከባቢ ውስጥ ህጋዊ አማራጮችን መከተል አልተቻለም።

ይህም ሆኖ መስጊዶች ብቻ ከብዙ ህገ ወጥ የአምልኮ ቦታ ግንባታዎች መካከል ተለይተው የህገ ወጥነት ስያሜ እየተሰጣቸው እንዲፈርሱ እየተደረገ ነው። መስጊድ ማፍረስ እንደቀላል እና ተራ ነገር እንዲታይ የማድረግ ጥረት የሚመስሉ ተግባራትንም እየተመለከትን ነው።

እኒህ ተግባራት በአስቸኳይ ሊቆሙ ይገባል። በመሆኑም ሙስሊሙን እርስ በርሱ እንዲጋጭ በማድረግ አጋጣሚውን ተጠቅሞ መስጊዶቹን ለመድፈር እና ለማስደፈር በየትኛውም አካል (እስካሁን የለውጥ ንፋስ ያልታየበትን መጅሊስ፣ አንዳንድ አመራሮቹን እና ደጋፊዎቹን ጨምሮ) የሚፈጸምን ተግባር ኮሚቴው በዝምታ የማያልፈው መሆኑን የሚመለከተው አካል ሁሉ እንዲገነዘብ እናሳስባለን! በተጨማሪም ውዲቷ አገራችን የሁላችንም እንደመሆኗ መጠን በእኩልነት የአምልኮ መፈጸሚያ እና የሃይማኖት ትምህርት መስጫ ተቋማቶቻችንን የምንገነባበት ቦታ በበቂ ሁኔታ ሊዘጋጅልን የሚገባ ሲሆን የሃይማኖት ተቋማትን የሚመለከቱ ህግጋትም የሙስሊሙን የእምነት ተቋማት ባህሪ እና ይዘት ግምት ውስጥ ባስገባ፣ ሙስሊሙንም ባሳተፈ መልኩ መቀረጽ እንዳለባቸው ለማሳሰብ እንወዳለን!

አላሁ አክበር!

የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ
https://mereja.com/amharic/v2/88726
Pages: 1 2 3 [4] 5 6 7 8 9 10