Author Topic: አስቸኳይ ወገናዊ ጥሪ  (Read 9187 times)

staff3

  • Global Moderator
  • Newbie
  • *****
  • Posts: 260
አስቸኳይ ወገናዊ ጥሪ
« on: February 25, 2012, 09:13:15 AM »
አስቸኳይ ወገናዊ ጥሪ

ለተከበራችሁ ኢትዮጵያውያን በያላችሁበት፤

በህጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ እና በአባ ገብረመድህን ወኪሎች
መካከል በአሜሪካ - አሪዞና ግዛት ከየካቲት 4 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ ሲያሄድ የሰነበተው ሁለተኛው ዙር የዕርቀ ሰላም
ውይይት ያለምንም ውጤት ተፈጽሟል፡፡ መግለጫም ወጥቷል።

ይህ በእንዲህ እያለ ይህንን የጉዞ አጋጣሚ ምክንያት በማድረግ በእኛ ዝንጉነትና ቸልተኝነት ኢትዮጵያን
የተቆጣጠሩት ወያኔዎች እዚህ ያለው አፈና አልበቃ ቢላቸው በዕርቅና ሰላም ሰበብ ወደ ዋሽንግተን በላኳቸው ያባ
ገብረመድህን ወኪሎች አማካኝነት በሰሜን አሜሪካ የሚገኙትን አብያተ ክርስቲያናት ለመቆጣጠር ሰፊ ዘመቻቸውን
ተያይዘውታል።

የዚህ ዘመቻ አስተባባሪ የድሮው አባ መላኩ የአሁኑ አቡነ ፋኑኤል ናቸው። አባ መላኩ ወያኔ ፈለጠኝ ቆረጠኝ
ወደ ሃገሬ ብመለስ ያሥረኛል፤ ይገድለኛል፤ ብለው የአሜሪካንን መንግሥት ዋሽተው የመኖሪያ ፈቃድ ያወጡና ጊዜውን
ጠብቀው የአሜሪካ ዜግነትን የወሰዱ ናቸው። ይህንን በሚያደርጉበት ጊዜ ከሃገር ወዳዱ ስደተኛ ጋር አጋር መስለው
በመቆም የወያኔን አስተዳደር ሲያወግዙና እንዲያውም እነዚህ ” ምናምንቴዎች “ እያሉ ወያኔዎችን ሲያወግዙ ቆይተው በኋላ
የአባ ጳውሎስ የጥቅም ሰለባ በመሆን በጵጵስና ቆብ ተሸጠው ምነዋ አባ ሲባሉ “ የእኔ ሬሣ እንደ ስደተኛው በሳጥን ወደ
ኢትዮጵያ አይላክም “ በማለት አዲስ አበባ ከአባ ገብረመድህን የጵጵስና ቆብ ተቀብለው ለአዋሳ ሃገረ ስብከት ተሾመው
ነበር።

እዚያ ከተመደቡ በኋላ በተዘፈቁበት ሙስናና ህዝብን የመከፋፈል ሤራ ምክንያት ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ
ያባረራቸው ሲሆን ከዚያ ሲባረሩ ደግሞ እዚህ ዘርፈውት በሄዱት ገንዘብ እንደገና አባ ጳውሎስን በጉቦ ተማፅነው ወደ
ዋሽንግተን በመመለስ በዋሽንግተንና አካባቢው የአባ ገብረመድህን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ክደውት በሄዱት ህዝብ
ላይ የተሾሙና አሁንም ህዝብ በላቡ በገዛው ቤተክርስቲያን አዛዥና ናዛዥ ሆነው የተቀመጡ ግለሰብ ናቸው።
ስለ አባ መላኩ ይህን ያህል ካወቃችሁ በዕርቅና ሰላም ሰበብ ወደ ዋሽንግተን ስለመጡት አባቶች የእሁድ ዕለት
ዉሎ ጥቂት ልግለፅላችሁ። ለምሳሌ እሁድ ዕለት ማለትም ፌብሯሪ 19 ቀን 2012 በዋሽንግተን ዲሲ የቡድኑ መሪ አቡነ
ገሪማ፣ የቀድሞው አባ መላኩ ያሁኑ አቡነ ፋኑኤል በሚመሩትና በሚያስተዳድሩት ደብረ ምኅረት ቅዱስ ሚካኤል፣ አቡነ
አትናቲዎስ ቀሲስ አማረ በሚመሩትና በሚያስተዳድሩት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም፤ ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ ቨርጂኒያ
በሚገኜው ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ከርስቲያናት በመገኜት የዕለቱን ቅዳሴ በየአድባራቱ የመሩ ሲሆን አያይዘውም በውጭ ሀገር
በስደት ስለሚገኙት አባቶች ተግባር ሲያጣጥሉና ሲያራክሱ ከማርፈዳቸው ሌላ አብያተ ክርስቲያናቱም በአባገብረመድህን (
አባ ጳውሎስ) አስተዳደር ሥር የመሆናቼውን አስፈላጊነት ሲቀሰቅሱ አርፍደዋል።

በዚሁ የዘመቻ ሥራ ለመጀመሪያ ጊዜ በደብረ ምኅረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የአባ ገብረ መድህን ስም
በጸሎት የተነሳ ከመሆኑ ሌላ አባ መላኩ ስደተኛው ምዕመን አፈር በልቶ በላቡና በጉልበቱ የገዛውን ቤተ ክርስቲያን ”ይህ
ቤተ ክርስቲያን ከዛሬ ጀምሮ በአባ ገብረመድህን ( አባ ጳውሎስ ) አስተዳደር ሥር የገባ መሆኑን እንድታውቁት” በማለት
ያለምንም ተጨማሪ ማብራሪያ በድፍረትና በንቀት ለምዕመኑ ገልፀዋል።

ከዚህም በኋላ አመሻሹ ላይ ሦስቱ ከአዲስ አበባ የመጡት እንግዶችና አባ መላኩ እንዲሁም ቀደም ብሎ ከደብረ
ገነት መዳኅኒዓለም የተባረሩት ቄስ-ሰብስቤና ዘማሪ-አቡኑ አንድ ላይ በመሆን አሌክሳንድሪያ ቨርጂኒያ በሚገኜው ሌላው
የወያኔዎቹ ቤተክርስቲያን ሥላሴ ውስጥ ከምሽቱ 5 ፒኤም ጀምሮ ስብሰባ በማካሄድ አባ መላኩ በስደተኛው ህዝብ ላብና
መከራ የተገዛውን የሕዝብ ንብረት የሆነውን ቤተ ክርስቲያን ለአባ ገብረመድህን (አባ ጳውሎስ) በማስረከባቸው እርሳቸውን
በመሳሰሉ ከሃዲ ካኅናት ሲወደሱ አምሽተዋል።

በመቀጠልም የህጋዊውና ስደተኛው ሲኖዶስ አባላት በድጋሚ በእንግዶቹ ሲዘለፉ ከማምሸቱ በላይ ወደፊትም
ዋሽንግተን አካባቢ እስካሁን የተቋቋሙትንና አዲስ የተከፈቱትን እንዴት በአባ ገብረመድህን ሥር አንደሚገቡ በአባ መላኩ
ሥር ያለው አስተባባሪ ኮሚቴ አጥብቆ የሚሠራ መሆኑን በራሳቸው በአባ መላኩ መግለጫ ተሰጥቷል። በመቀጠልም
በመጪው እሁድ ማለትም ፌብሯሪ 26 2012 አባ መላኩ ሌላውን በስደተኛው ላብ የተቋቋመውን ካንሳስ ሲቲ የሚገኜውን
የካንሳስ ኪዳነ ምኅረትን ቤተ ክርስቲያን በሌላው ከሃዲና አዲስ ሹመኛ ሊቀ ካኅናት አባ ተስፋ አማካኝነት ሊረከቡ ወደ
ካንሳስ ሲቲ እንደሚሄዱ ይፋ አድርገዋል።

ውድ ሀገር ወዳድና ሃይማኖታችሁን አፍቃሪ የሆናችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን፤ በመግቢያችን ላይ
እንደገለጽነው ይህ ሁሉ የሚፈጸመው በእኛ ቸልተኝነት እና አያገባኝም ብለን ጉዳያችንን ለተኩላዎቹ አሳልፈን በመስጠታችን
እንደሆነ ሁላችንም የምናምነው ጉዳይ ነው። ትናንት ትናንት ነው። ዛሬ ግን ችግራችንን ለመቋቋም አቅደናልና ሀገር ወዳድ
የሆናችሁ ወገኖቻችን ሁሉ ቀጥሎ በተዘረዘሩት አስቸኳይ ማሳሰቢያዎች ላይ ተባብረን በመቆም ይህንን አይን ያወጣ ግፍ
አብረን እንድንቋቋም እንማፀናለን።

1ኛ/ የአባ መላኩን አድራጎት አስመልክቶ አባ መላኩን ከቤተክርስቲያኑ ይዞታና አስተዳደር ለማስወገድ የተጠናከረ
ግብረ ሓይል እዚህ በዋሽንግተን ተቋቁሟል። ግብረ ሃይሉም በመጪው እሁድ ፌብሯሪ 26 2012 ከጧቱ 8 ፒኤም ጀምሮ
በደብረ ምኅረት ቅዱስ ሚካኤል 3010 Earl Pl Ne Washington, DC 20018 ታላቅ የተቃውሞ
ሰላማዊ ሰልፍ ስለሚያካሄድ ማንኛውም በአካባቢው የሚገኝ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በቦታው እንዲገኝልን። ይህንን መልዕክት
ያገኛችሁ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ዋሽንግተንና አካባቢው ለሚገኙ ዘመድ ወዳጅ ጓደኞቻችሁ በሙሉ ስልክ በመደወልና
ኢሜል በማድረግ በተቃውሞ ሰልፋችን ላይ እንዲገኙ እንድታደርጉልን።

2ኛ/ አባ መላኩ ወደ ካንሳስ ሲቲ በመሄድ የካንሳስ ሲቲውን ኪዳነምህረት እንደ ዋሽንግተኑ ደብረ ምኅረት ቅዱስ
ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በአባ ገብረ መድህን (አባ ጳውሎስ) አሥተዳደር ሥር ከማስገባታቸው በፊት ስደተኛው ሁሉ
በመረባረብ ይህንን አይን ያወጣ ደባና ዘረፋ እንዲቋቋም፤ በተጨማሪም በዕለቱ የተቃውሞ ሰልፍ በካንሳስ ሲቲም
ኪዳነምኅረት በማዘጋጀት አባ መላኩንና ተባባሪዎችን እንድንቃዎም። በየትኛውም አካባቢ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንም
ካንሳስ ሲቲ አካባቢ ለሚገኙ ዘመድ ወዳጅ ጓደኞቻችሁ በሙሉ ስልክ በመደወልና ኢሜል በማድረግ ሁኒታውን
እንድታስረዱልን በግብረ ሓይሉ ስም ወጋናዊ ትብብራችሁን እንጠይቃለን።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር


« Last Edit: March 04, 2012, 08:48:57 AM by staff3 »