Category Archives: Press Releases

Press Releases

የአማራ ሕዝብ የመቅሰፍት አደጋ አንዣቦበታል!

ግንቦት 5 ቀን 2006 ዓ.ም (May 13, 2014)
የአማራ ሕዝብ የመቅሰፍት አደጋ አንዣቦበታል!

ወያኔ ሥልጣኑን በባዕድ ድጋፍ ከተቆጣጠረና አገዛዙን ከመሠረተ ወዲህ ያለፈባቸውን 22 አመታት አቆነጃጅቶ ለመግለፅ መጠነ ሰፊ የሆነ ፕሮፓጋንዳ ቢጠቀምም ከእለት ዕለት ሀገራችንና ሕዝቧን ወደባሰ አዘቅት እየከታት ለመሆኑ የሕዝቡ የኑሮ ሁናቴ የሚመሰክረው ነው። በሱ የፖለቲካ መነፅር ለማየት ካልተፈለገ በስተቀር ኢትዮጵያ ሀገራችን በርካታው ሕዝብ በኑሮው በመማረር ለስደት የሚዳረግባት፤ ቀሳፊና ተላላፊ በሆኑ ብቻ ሳይሆን በቀላሉ ሊወገዱ በሚችሉ በሽታዎች እየተጠቃ ሕይወቱን የሚያጣው የዜጎች ቁጥር እየበረከተ ያለባት፤ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የሚደፈጠጡባት፤ በሀገሩ ለባይተዋርነት የሚዳረገው ብዙሃኑ የሆኑባት፤ መልካም አስተዳደር ጠፍቶ ግብር ከመክፈል ውጭ ዜጎቿ ማግኘት የሚገባችውን የሲቪል አገልግሎት የሚያጡባት፤ መንገዱ አልጋ በአልጋ እንደማይሆን እሙን
እየተባለ የደላቸው የአገዝዙ አባላት የሚያላግጡባት፤ ከሁሉ በላይ ድግሞ እንደ ሕይወት እስትንፋስ የሚያስፈልገው ነፃነቱን ባልተጎናፀፈባት ሀገሪቷ በእድገት ጎዳና እየተጓዘችና ሕዝቡም የእድገቱ ትሩፋት ተጠቃሚ እየተባለ አምባገነንና ጎጠኛ የአገዛዙ አባላት በጫንቃው ላይ ተቆናጠው ዘላለማዊ የሥልጣን ማራዘሚያ መሣሪያ ደግነው ምልአተ ሕዝቡ የሚበዘበዝበትና የሚበደልበት ሀገር ናት።

በተለይም በቋንቋና በዘር ልዩነት ላይ የተመሠረተው የፌደራል ሥርዓት ከመጀመሪያውኑ አንድን ብሔር በጠላትነት ሰይሞ በዘር ማፅዳት ተግባር ከኢትዮጵያ መልክዓ ምድር ለማጥፍትና የራሴ የግሌ የሚባል የግዛት አካባቢ ለማቋቋም ባለመ መልኩ የታሰበ ነበርና ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚያስከትለው ውጤት እጅግ
አስከፊና አሳዛኝ የሆነ በርካታ ችግሮችንም እየወለደ፤ ጸብና ግጭቶችን እያበራከተ፤ የዜጎች ሕይወትና የሕዝብ ኃብት በእጅጉ የሚባክንበት ሁኔታ እየተከሰተ ይገኛል። በምሥራቅ ኢትዮጵያ ደገሃቡርና ጅጅጋ፤ በምሥራቅ ሀረርጌ ጋራሙለታ፤ በደኖ አንስቶ በባሌና በአርሲ በሚገኙ አካባቢዎች በዘር ላይ የተመሠረቱ
ግጭቶችና የሰው ሕይወትና ንብረት የወደሙበት ሁኔታ በምሳሌነት ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው። በምዕራብ ኢትዮጵያም ቢሆን በተለያዩ ወቅቶች በአሶሳ በባምባሲ፣ በሰሪ፣ በጋምቤላ፣ በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ፣ ነቀምት፣ አምቦም በዚሁ አስከፊ ሁናቴ የሚጠቀሱ ናቸው። በአርሲ ክፍለ ሀገር በአርባጉጉ አውራጃ
ውስጥ በሚገኙ ጎሎልቻ፣ ጨሌ፣ጃጁ፣ መርቂ በተሰኙ ወረዳዎችና አካባቢዎች በርካታ መኖሪያ ቤቶች የወደሙበት፤ ሕይወት የጠፋበት፤ የሰው ልጅ እንድ ከብት አንገትና ጡቶች የተቆረጡበት አሰቃቂና አሳዛኝ በደሎች ተካሂደዋል። በሌላ ቦታ ደግሞ ከነነፍሰ ሕይወታቸው ወደገደል ተወርውረው
እንዲፈጠፈጡ ተደርገዋል።

በሀገራችን ባሁኑ ወቅት በአገዛዙና አክራሪ ፅንፈኞች አማካኝነት ጠላት ተብሎ በተፈረጀው በአማራ ተወላጅ ላይ ሽብርና የእልቂት ተግባር ለማካሄድ የመቅሰፍት ዘመቻ እየተጧጧፈ መሆኑን እንመለከታለን። በሀገር ቤትና በውጭ አገር የሚገኙ እብደት የተጠናወታቸው ፅንፈኞች አማራው እንዲጨፈጨፍ ጥሪ እንዲያቀርቡ ቅስቀሳ የተደረገላቸው ሲሆን የዚሁ አቀንቃኝ የሆኑቱ በምዕራቡ ቴሌቪዥንና የሬዲዮ ስርጭቶች ተገኝተው ለመስማት የሚሰቀጥጥ የጥላቻ ዘመቻቸውን ሲያናፍሱም ተደምጠዋል።

ርግጥም በአማራው ላይ ያንዣበበው የመቅሰፍት አደጋ እየተስፋፋ ያለ እንደሆነ እንመለከታለን። የአገዛዙን የጀርባ ታሪክ ለተከታተለና ለሚያወቅ ማንኛውም ዜጋ ያንዣበበውን አደጋ ሊገነዘበው የሚችል ነውና ክስተቱ የተሳሳተ አስተያየትና ግምት አለመሆኑን የሚረዳው ይሆናል። ወያኔ ራሱ በ1975 ዓ.ም.
ሲያካሂድ የነበረውን ትግል በቁጥር ብዛት ከኦሮሞ ቀጥሎ ይገኛል ተብሎ በሚገመተው በአማራ በተለይም በሸዋ አማራ ላይ ነው በማለት ገልፆት እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም። ሟቹ መለስ ዜናዊ በወቅቱ በሰጠው ቃለ መጠይቅም ያረጋገጠው መሆኑ አይዘነጋም። በጊዜው በጥሞና የሚያዳምጥና የሚያስተውል ጠፍቶ
እንጂ ወያኔ ፀረ አማራነቱን ምንጊዜም ቢሆን የደበቀው አልነበረም። አሁንማ ብሶባት ያለ ጉዳይ ነው። ወያኔ ሥልጣን ከመቆናጠጡ በፊት ከሻዕቢያና ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጋር በመተባበር በወለጋ የሚገኘውን የአሶሳ ከተማ በማጥቃት በመቶዎች በሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች ላይ የእልቂት እርምጃ ማካሄዳቸው
የሚረሳ አይደለም። ይህንን አሰቃቂና ዘግናኝ የሆነ ጭፍጨፋ በወቅቱ የእንቅስቃሴው መሪ የነበረው የኤርትራው ኮማንደር „ኩራት“ በተሞላበት ሁናቴ በአንድ ቃለ መጠይቅ መግለፁም የሚታወስ ነው። በዚህ ኢሰብዓዊነት በተጠናወተው ድርጊታቸው ከ300 በላይ የሆኑ አማራዎች ተገድለዋል፡ ተቃጥለዋል፡
ወይንም ታርደዋል። የዚህ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ውጤት በወቅቱ በቪዲዮ ተቀርጾ ለሕዝብ እይታ በቀረበበት ወቅት የብዙዎችን ሕሊና ማቁሰሉና የማይረሳ ጠባሳ ማሳረፉም የሚዘነጋ አይደለም። ለጭፍጨፋው ተጠያቂ የሆኑት ሶስቱ ግምባሮች ሁሌም በፀረ አማራና አለፍ ሲልም በፀረ ኢትዮጵያዊነታቸው የሚታወቁ
በዚህም በሕዝብ ዘንድ የተጠሉ ናቸው። እነዚህ ክፍሎች ለበርካታ አመታት አማራ መሆን ለኢትዮጵያ መቆም ነው በማለት ስለሚያምኑ ሁሌም የኢትዮጵያ ማንነትን ተቃርነው የቆሙ ናቸው። የአማራ ሕዝብ ከሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጋር በመሆን እንደ አይን ብሌኑ የሚሳሳላትን ሀገሩን ኢትዮጵያን ከተለያዩ
የባዕዳን ወራሪዎች ተከላክሎና ጠብቆ የኖረ ከሁሉም በላይ ደግሞ በቅኝ ገዢዎች መዳፍ ሥር እንዳትወድቅ ከፍተኛ መስዋዕት የከፈለ ሕዝብ መሆኑ በዚህም ለኢትዮጵያዊነት የፀና አቋም ያለው መሆኑ በነዚህ ኃይሎች አይወደድለትም። ለዚህም ነው አማራን ነጋ ጠባ አድሃሪ፣ ትምክህተኛ፣ ነፍጠኛ፣ የድሮ
ሥርዓት ናፋቂ ሌላም አፀያፊ ስሞች እየለጠፉበትና በጠላትነት እየፈረጁ ለማጥቃት የሚጥሩት። ወያኔ በኢሕአደግ ሽፋን ሥልጣን ከተቆናጠጠ በኋላ ጸረ አማራ የሆኑ ክፍሎች ሲያልሙት የነበረውን ጭፍጨፋቸውን በአማራው ላይ ለማካሄድ ሁናቴው ተመቻቸላቸው። በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ
በስደተኝነት ምናልባትም የዚሁኑ ሀገር ዜግነት ተቀብሎ በሚኖረው አሊ ሁሴን መሪነት በአርባጉጉ የተደረገው ጭፍጨፋ ለዚህ ጉልህ ምሳሌ ነው። እንዲሁም በኖርዌይ ሀገር ነዋሪና በወቅቱ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር መሪ በነበረው ሌንጮ ለታ መሪነት በኢትዮጵያ ምስራቅ በበደኖ በአማሮች ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ
ተካሂዷል። እርጉዝ ሴቶች በጥይት ተደብድበዋል፤ ሽማግሌዎችና ወጣቶች ከገደል ተወርውረዋል፡ እልቂት የሚለው ቃል ሁኔታውን ይገልፃል ቢባል እውነትነት ይኖረዋል። በምሥራቅ ወለጋም የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ምንም አይነት ወንጀል የሌለባቸውን ንጹሃን አማሮችን በመግደል ተካፋይ ነበር። ፅንፈኛው
የኦሮሞ እስላማዊ ቡድንም በአሰቦት ገዳም የሴትና የወንድ መነኩሴዎችን መጨፍጨፋቸው በጊዜው የስንቶቹን እንባ ያስፈሰሰ እንደነበር አይዘነጋም።

በቅርቡ አገርሽቶበት የተነሳው ፀረ አማራ ዘመቻ ከመቶ አመት በፊት በንጉስ ሚኒሊክና ወታደሮቻቸው ኦሮሞዎችን ገድለዋል የሚሉትን ተንተርሶ እየተናፈሰ የሚገኘው የጥላቻና የበቀል መንፈስ አማራን ለመወንጀልና በሱ ላይ የዘር ማጥፋት ተግባር ለማካሄጃ ረግረጉን ለማመቻቸት
ሲባል እንደሆነ በግልፅ የሚታይ፤ በተግባርም እየተደገፈ ያለ ነው። ይኸው የጥላቻና የበቀል ስሜት በይበልጥ ሕይወት እንዲላበስ ደግሞ በአኖሌ አካባቢ የተገነባው የሰማዕታት መታሰቢያ ሳይሆን የሙታን ቂም ማስነሻ ኃውልት በአገዛዙ ባለሥልጣናት መመረቁንና እሱን ተስታኮ እየተሰጡ ያሉ መግለጫዎች የሚያመለክቱት ናቸው። በቅርቡ እንኳን በአምቦ ከተማ በተማሪዎች በተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ፀረ አማራ መፈክር በፅንፈኞች ሲገለፅ መሰማቱ የዚሁ የጥላቻ ስሜት ውጤት
እንጂ ሌላ አይደለም። በሥልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ለዚሁ ይሁንታውን ከመስጠት አልፎ ከተለያዩ የደቡብ አካባቢዎች በአማራው ላይ የዘር ማፅዳትና ጠራርጎ የማስወጣት ዘመቻን ሲያናፍስና ሲያራግብም እንደነበር የተደመጠና የተስተዋለ ነው። በአገዛዙ አቀናባሪነትና ድጋፍ የግድያ ወይንም ደግሞ ለመቶ አመታትና ከዛም በላይ ተኪ፡ ኃብትና ንብረት አፍርተው እንደማንኛውም ዜጋ ከሌሎች ብሔረሰብ ተወላጅና እምነት ካላቸው ጋር ተስማምተው ከሚኖሩበት ቀዬ እንዲባረሩ የሚደረገው ዘመቻ አማራውን ለአደጋና ራሳቸውን እንዳይከላከሉ ተዳርገዋል።

ይህ ሁናቴ በርካታውን የአማራ ተወላጅና በኢትዮጵያ ሀገራዊ አንድነት የሚያምኑ ዜጎቻችን የከፋ መቅሰፍት ይደርስብናል የሚል የስጋትና የሰቀቀን ስሜት በልባቸው ውስጥ እያሳደረ ያለ ጉዳይ ነው። ይህንን ፀረ አማራ ዘመቻ የተሳሳተ ታሪክን ተቀብለው እንደገደል ማሚቶ በሚያናፍሱ አንዳንድ ባዕዳንና የዜና ተቋማት እየተደገፈና አማራውን እንደ ሕዝብ በፀረ ኦሮሞነት የሚወነጅሉም ተቀላቅለውታል። የኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት ሁሌም ከባዕዳን ኃይሎች ተቃውሞ
ያልተለየው ለመሆኑ ደግሞ ያለፈ የጀግንነት ታሪካችን የሚመሰክረው ነው። የኢትዮጵያን ሕዝብ እርስ በርስ ለማጋጨት ጥረት አድርገው የነበሩት የእንግሊዙ የናፒየር ጉዞም ሆነ የሙሶሎኒ ቅኝ የማድረግም ሙከራ በአብነት ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው።

በሌላ በኩል በሀገሪቱ በተጨባጭ ያለው ዕውነታ የአሁኑ አገዛዝ የተለያዩ ብሄሮችን አማራን፤ ኦሮሞን፤ ሶማሌን፤ ጉራጌን አኙዋክና ሌሎችንም በመጨቆን ላይ የተመሰረተ መሆኑ ነው። የወያኔ አገዛዝ በጋምቤላ፤ በኦጋዴን፤ በሲዳማ እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች ሕዝባዊ ጭፍጨፋ አካሂዷል።
ነገር ግን በአማራው ተወላጅ ላይ የማስፈራራት ስሜትና ዛቻ በአሁኑ ወቅት እየጨመረ ብቻ ሳይሆን በባዕዳን ሀገር በሚገኙ ከአሜሪካና ከእንግሊዝ የፖለቲካ ሥርአት ተጠቃሚ በሆኑ የሁሉም አማራ „ጉሮሮ እንዲቆረጥ“ ጥሪ በሚያቀርቡት ፅንፈኞችም እየተደገፈ ነው። የወያኔ አገዛዝ በአሁኑ ወቅት እየተውተረተረ ያለ በመሆኑ ይህንን ፀረ አማራ ዘመቻ በ 2007 ዓ.ም. ይደረጋል ተብሎ ለሚጠበቀው „ሕዝባዊ ምርጫ“ ለድጋፍ ማግኛ መጠቀሚያ ለማድረግ እየጣረ
ነውና የተቃጣው አደጋ እውንና የምርም ነው። ማንም ለኢትዮጵያ ሕዝብና ሀገሪቷ ቀናኢ የሆነ ሀገር ወዳድ ሁሉ በቸልታ ሊመለከተው የማይገባው ነው።

በመሆኑም ኢሕአፓ የአማራን ሕዝብና ሁሉ አቀፍ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ኃይሎች እያንዣበበ ካለው የጥፋት ሴራ ራሳቸውን እንዲከላከሉና የዘር ማጥፋት ተግባር፤ ጥላቻና፤ በአማራው ላይ የተቃጣውን የግድያ ዘመቻ አጥብቀው እንዲቃወሙ ሀገራዊ ጥሪውን ያቀርባል።

Source:
http://www.eprp.org/press_releases/YeAamarawu-Hiz-Adega-Anzsabobetal.pdf
http://www.eprp.org/press_releases/Danger-of%20Genocide-of-the-Amharas.pdf