http://www.ethiox.com/amharic/ad1ba.pdfአዲስ መጽሐፍ - ከበልጂግ ዓሊ በልጅግ ዓሊ በተለየዩ ድረ ገጾች ለረጅም ዓመታት የሃገራችን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታዎችም ሆነ በሕይወቱ ውስጥ የሕይወቱን ገጠመኞች ከኅብረተሰቡ ኑሮ ጋር በማጣመር ለንባብ በሚያጓጓ መልኩ ሲያቀርብ እንደነበር የሚታወስ ነው ። አሁን ደግሞ "ቀለበቴን ስጧት" እና ሌሎች መጣጥፎችን በመጽሐፍ መልክ አሳትሞ በቅርብ ቀን ለሕዝብ ያቀርባል። በመጽሐፉ ውስጥ ለንባብ ቀርበው ተደናቂነት ያገኙት "ሽጉጤ ደሜ"፣"የሁለት ትውልዶች ወግ"፣ "ለሞት የቀረበ" እና ሌሎችም ይገኙበታል። ይህ በሰሜን አሜሪካ በሚኒያፖሊስ ከተማ የታተመው መጽሐፍ አትላንታ ውስጥ በሚደረገው የሰሜን አሜሪካ የእግር ኳስ ጨዋታ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሕዝብ ይቀርባል። በተለያዮ የሰሜን አሜሪካና የአውሮፓ ከተማዎች ውስጥ የመጽሐፍ ፊርማ ሥነ ስርዓትና ከደራሲው ጋር የፊት ለፊት ውይይት ለማድረግ በዝግጅት ላይ ይገኛሉ ይገኛል ።
|