ethiox.com
ethiox.com
Donate!
web hosting service
SELECT command denied to user 'kcgvincw_fusion1'@'localhost' for table 'fusion_site_links'
Latest Links

  


  


  


  


  

Search

Enter Keywords:


የበሬ ግንባር የምታክል ቢሮ መምራት ያቃተው የመ.ኢ.አ.ድ
Press Releases

የበሬ ግንባር የምታክል ቢሮ መምራት ያቃተው የመ.ኢ.አ.ድ አመራር ኢትዮጵያን ሊመራ አይችልም !

እግዚአብሔርን የሚፈራ ታሪክ ለመስራት የተዘጋጀ ራዕይ ያለው ትውልድ ኢትዮጵያ ውስጥ ለምን አይፈጠርም ?

  የመ.ኢ.አ.ድን አመራር ጠቅላላ ስህተትና አምባ ገነናዊ አስተሳሰብ የምንቃወምና እንዲስተካከል የምንጥር የፓርቲው የላዕላይ ምክርቤት አባላት የተሰጠ መግለጫ

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ( መ.ኢ.አ.ድ) በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቋቋመ ህግዊ እውቅና ያለው ፓርቲ ነው፡፡ ፓርቲያችን መ.ኢ.አ.ድ በአደረጃጀቱም ሆነ ባመሰራረቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ልዩ ልዩ ብሔረሰቦችን በማቀፍ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚንቀሳቀስ ህብረብሔራዊ ፓርቲ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ሆኖም ግን ፓርቲውን የሚመሩት አመራሮች ከፓርቲው አላማና ግብ በተቃራኒው እየፈፀሙት ያለው ድርጊት ዛሬ ላይ ይህንን ዓይነት የተቃውሞ አቋም እንድንይዝ አስገድዶናል፡፡ ፍትህ አልበኝነትና ህገወጥነት ለመ.ኢ.አ.ድ አመራሮች የዕለት ተዕለት ተግባራቸው ሆኖ ቀጥሏል፡፡ ፓርቲው ጥቂት በሆኑ ግለሰቦች እጅ ስር የወደቀ የተለበለበ ግንድ በመሆኑና እነዚህ አመራሮች በወንዘኝነት የተጣመሩ በመሆናቸው ሁኔታውን ውስብስብ አድርጎታል፡፡ ፓርቲው ከሚያራምደው ዓላማ ውጪ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙት እነኚህ ቡድኖች ከፓርቲው ዓላማ በተጻረረ መልኩ እየተጓዙበት ያለው አካሄድ ፓርቲያችንን የሚጎዳ በመሆኑና እየከወኑት ያለው አንዳንድ እንቅስቃሴ ከግል ጥቅማቸውና ምኞታቸው አንጻር የመነጨ በመሆኑ ይህንን ህገወጥ አካሄዳቸውን መስመርና ስርዓት ለማስያዝ ህሊናችንና ሀገር ወዳድነቻን አስገድዶናል ፡፡

መ.ኢ.አ.ድ ንጹህ ኢትዮጵያዊ አባላትን የያዘ ፓርቲ ከመሆኑም ባሻገር የዲሞክራሲያዊ ስርዓት መስፈን፣ ለፍትህና ለእኩልንት መረጋገጥ ቀን ከሌሊት ደከምኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ለኢትዮጵያ አንድነት የሚታገሉ አባላት በገጠር በከተማ እንዲሁም በውጪ ሀገር የተሰበሰቡበትና ተስፋ የተጣ

ለበት ፓርቲ ነበር፡፡ የፓርቲው አመራሮች ግን ፍጹም በሆነ አምባ ገነናዊ ኮረቻ ላይ ተፈናጠው በጎጠኝነት ፣ በሙሰኝነት ፣በኢ-ዲሞክራሲያዊና ፍትሃዊነት ፈረስ ላይ ሽምጥ እየጋለቡ ይገኛሉ ፡፡

ነገር ግን እንደአለመታደል ሆኖ በሰላማዊ መንገድ ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት መስፈን የሚታገሉ ንጹህ የፓርቲው አባላት ዛሬም እንደትናንቱ ዲሞክራት የሆነ ከፊውዳል ስርዓት የተላቀቀ ከጎጠኝነት አስተሳሰብ የጸዳ ለህዝብ የሚያስብ ፍትሀዊ የሆነ ከሙስና የራቀ መሪ አላገኙም፡፡

የመ.ኢ.አ.ድ አመራሮች ከዚህ ፍላጎት በተቃራኒ ፍጹም አምባገነኖች የፊውዳል ስርዓት አስተሳሰብ ጥምቀት የተጠመቁ እንዲሰገድላቸው ብቻ የሚፈልጉ የጌታና የሎሌ ስርዓት አራማጆች መሆናቸው ነው፡፡ እነዚህ አመራሮች የፓርቲውን ህብረ ብሔራዊነት ፍጹም በሚጻረር መልኩ በዘረኝነት በጎጠኝንት የተተበተቡ በመሆናቸው የሚፈጽሙት እያንዳንዱ ድርጊት ቆምንለት ከሚሉት የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ውጪ እንደሆኑ ያጋልጣቸዋል፡፡ በሙስናና በምዝበራ የተጨማለቀው ስብዕናቸው ደግሞ በሕዝብ ፊት ዲሞክራት ሆኖ ለመቅረብ ፈጽሞ የሞራል ብቃት ያሳጣቸዋል፡፡ እነዚህ አመራሮች በሰላማዊ ትግል ሽፋን በንጹሁ የመ.ኢ.አ.ድ አባላት ስም የስልጣን ጥማታቸውን ለማርካት የቆረጡ የስልጣን ጥመኞች መሆናቸውን ያረጋገጠ ነው፡፡

የመ.ኢ.አ.ድ አምባገነንና ጎጠኛ መሪዎች የሚፈጽሙትን ኢ-ፍትሀዊ ድርጊት ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ ሲታሰብ ከጥላቻ የመነጨ ሳይሆን ከስራቸውና ከተግባራቸው በመነሳት በዲሞክራሲ ስም ካጠለቁት ጭምብል ስር ያለ እውነተኛ ማንነታቸውን ጠንቅቆ ለመራዳት ላይ የተመሰረተና ማስረጃ ያለው ነው፡፡

 1. የነዚህን አመራሮች ብልሹነትና ፍትህ አልበኝነት ለህዝብ ማሳወቅ ለነዚህ አስመሳዮችና የስልጣን ጥመኞች ህዝብ ዳግመኛ እንዳይታለል በአንክሮ ለማሳሰብ ነው፡፡
 2. የፓርቲው የላእላይ ምክርቤት አባላት ይህ አመራር የሚፈጽመውን ዘርፈ ብዙና ሁለንተናዊ ስህተት በመረዳት ዲሞክራሲያዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ብቻ እነዚህን አካላት በማስገደድ ተሰብስቦ ፓርቲያቸውን የማስተካከል ኃላፊነት እንዳለባቻው ለማስገንዘብ ነው፡፡
 3. ዓባላትና ደጋፊዎች በፓርቲ ውስጥ የፓርቲ ውስጠ ዲሞክራሲ አግባብና ስርኣት ባለው በንገድ ህግን መሰረት ያደረገ ትክክለኛና ፍትሀዊ መዋቅራዊ አሰራር እንዲኖርና እንዲሰፍን የበኩላቸውን እንዲያደርጉ እነዚህ አምባገነን መሪዎች ከእንግዲህ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ዳግመኛ የሚቀልዱበት እድል እንዳይኖራቸው ለማስገንዘብና ጥሪ ለማቅረብ ጭምር ነው፡፡

  በጥቅሉ የመ.ኢ.አ.ድ አመራር ዘርፈ ብዙ ችግር ተገልጾ የማያልቅ ቢሆንም ለአብነት ያህል ግን ዓባላት ለእነሱ ካልሰገዱ የእነሱ ጉዳይ አስፈጻሚ ካልሆኑ እነሱ የሚሏቸውን ብቻ ካላሟላችሁ ተብለው በአጠቃላይ በእኛ ሳንባ ካልተነፈሳችሁ እየተባሉ ያለምንም ማስረጃ ከፓርቲው ታግደዋል፡፡ አንዳንዶቹም በጥበቃ ተገፍትረው እንዲወጡ ተደርገዋል፡፡ ከነዚህም ውስጥ የሥራ አስፈጻሚና የላዕላይ ምክርቤት አባላት የቀጠና አስተባባሪና ከፍተኛ አደራጆች የዞንና የወረዳ ኮሚቴ አመራር አባላት ይገኙበታል፡፡ በዚህ አመራር ይህ አምባገነናዊ አስተሳሰብ ተግባራዊ ሲሆን አቤት የሚባልበት ወይንም ይግባኝ የሚጠየቅበት አሰራር በመ.ኢ.አ.ድ ውስጥ ፈጽሞ አለመኖሩ ደግሞ ድርጊቱን ሁሉ አስገራሚ አድርጎታል፡፡ በመሆኑም በመ.ኢ.አ.ድ ውስጥ የመንደርተኛው ቡድን አባላት፡-

   1. ሻለቃ ጌታቸው መንግስቴ
   2. አቶ ገ/ጻዲቅ ገ/ማርያም
   3. አቶ ማሙሸት አማረ ወዘተ ለሚባሉ የአንድ አካባቢ ሰዎች ግድ አቤት ወዴት ማለት ይገባል

በነዚህ ሰዎች ምክንያት በፓርቲ ውስጥ ባለው ብልሹ አሰራር አመራሮቹ አምባገነናዊ እንቅስቃሴ በመቃወም ከእነዚህ አመራሮች ጋር ላለመቀጠል አቋም የወሰዱ የፓርቲው አመራርና አባላት ለመጥቀስ ያህል

  1. ወ/ሮ አለማየሁ ሞገድ የመ.ኢ.አ.ድ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ
  2. ወ/ሪት ሞሰበወርቅ ቅጣው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የህዝብ ጉኝነት ኃላፊ
  3. ሻለቃ አርጋው ካብታሙ የስራ እፈጻሚ ኮሚቴ አባል
  4. አቶ ጌታቸው አበባ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል
  5. አቶ ከበደ ታዬ የላዕላይ ምክርቤት አባል ፣ ከፍተኛ አደራጅና የምዕራብ ቀጠና አስተባባሪ
  6. አቶ ጌታነህ አለም የላዕላይ ምክርቤት አባል ክፍተኛ አደራጅ እና የሰሜን ቀጠና አስተባባሪ
  7. አቶ ነብዩ ክንፈ የላዕላይ ምክርቤት አባል የአንድነት ጋዜጣ ምክትል አዘጋጅ
  8. አቶ ቸርነት እሸቱ የላዕላይ ምክርቤት አባልና የአዲስ አበባ ወጣቶች ምክርቤት አባል
  9. አቶ ስለሺ ገዛኸኝ የላዕላይ ምክርቤት አባል እና የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ጸሀፊ
  10. አቶ አሸናፊ አንተነህ የአዲስ አበባ ወጣቶች ምክርቤት አባል
  11. አቶ ከበደ ገብሬ የፓርቲው አባልና የአንድት ጋዜጣ ከፍተኛ አዘጋጅ
  12. አቶ አሸናፊ አስናቀው የፓርቲው አባልና የቦሌ ክፍለከተማ ዋና ጸሀፊ ሲሆኑ ይኸው አመራር በጥላቻ በቂም በቀል አሰራር ዘወትር እየተነዳ ከፈጸመው አምባገነናዊ ድርጊት መካከል አንደኛውና ዋናው የአዲስ አበባ ወጣቶች ምክርቤት ስራ አስፈጻሚ ኮምቴ አባላትን ያለበቂ ምክንያት አግዷል፡፡

ከታገዱት አባላት መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል

  1. ወጣት ኃ/ገብርኤል ታምራት ሊቀመንበር
  2. ወጣት ዮሀንስ ዘውዴ ምክትል ሊቀመንበር
  3. ወጣት ሀብታሙ ጉሌዋና ጸሀፊ
  4. ወጣት አሸናፊ ግርማ የማህበራዊ ጉዳይ ኃላፊ
  5. ወጣት ታዬ መዝገቡ የጥናትና ምርምር ኃላፊ ናቸው፡፡

ይህ ብቻ አይደለም በሚገርም መንገድ በአንድ ግለሰብ በአቶ ማሙሸት አማረ 180 አባላት ያሉትን የአዲስ አበባ ወጣቶች ምክርቤት ሙሉ በሙሉ ምክንያቱ ሳይገለጽና ሳይታወቅ እንዲፈርስ ተደርጓል፡፡ ይህ ለምን እንደተደረገ ከሥራ አስፈጻሚ ጀምሮ ጥያቄ ያቀረበ አካል መጥፋቱ ደግሞ የመኢአድ አመራር ሰሜን ሸዋ ውስጥ የተገኙ ያንድ መንደር ስብስቦች ፓርቲውን እንደግል ንብረት በባለቤትነት እንደያዙት አስረግጦ የሚያስረዳ ነው፡፡ እነዚህ አመራሮች እንደዚህ ይነቱን አሳፋሪ ስራ ሲሰሩ የሚጠቀሙባቸወ በመረጃ ያልተገደፉ እርካሽ ሊባሉ የሚችሉ ስልቶች አሏቸው፡፡ እነሱም እገሌ ኢህፓ ነው ፣ እገሌደግሞ የኢዲፓ ወኪል ነው በእነሱ አጠራር እገሌ ወያኔ ነው ፣ከአንድት የተላከ ሰላይ ነው ወዘተ በማለት የዳቦ ስም ይወጣለታል ፡፡

እነዚህ አመራሮች ፓርቲው በተለያየ መንገድ ከዚህ በላይ እንዲያድግ የማይፈልጉ ናቸው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ከዚህ በላይ ፓርቲው ካደገ የተሻለ ሰው መጥቶ ኃላፊነቱን ስለሚረከባቸውና ሌላ ስራ ሰርተው ለመኖር ብቃትና ችሎታ ስለሌላቸው ነው ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ፓርቲው እንዲጠፋ አይፈልጉም፡፡ ለእነሱ ብቸኛ መጦሪያቸው ስለሆነ እስከ ምጽአት ድረስ እነሱብቻ እንዲመሩት ይፈልጋሉ፡፡ በነዚህ ምክንያቶች እነዚህ ግለሰቦች በፓርቲው ውስጥ የያዙትን ኃላፊነት እንመልከት ለምሳሌ ሻለቃ ጌታቸው መንግስቴ የስራ አስፈጻሚ ኮምቴ አባል ምክትል ፕሪዘደንት የምስራቅ ቀጠና ኃላፊ፣ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ፣ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፣የምርጫ ጉዳዮች ኃላፊ ፣ የአንድነት ጋዜጣ ዋና አዘጋጅና ኢዲቶሪያል ቦርድ ሰብሳቢ ሆኖ ይሰራል፡፡

አቶ ማሙሸት አማረ ደግሞ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የመ.ኢአ.ድ ወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ የመ.ኢ.አ.ድ ዋና ጸሀፊ ፣ የመኢአድ ወጣቶች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በመሆን ይሰራል ፡፡

ታዲያ እነዚህ ሰዎች ይህንን ሁሉ ኃላፊነት ሰብስበው ይዘው በፓርቲው ሲቀልዱ ዝምብለን እንመልከታቸው ? ወይስ ሌላ የሚሰራ ሰው ጠፍቶ ነው ? ትዝብቱን ለመኢአድ የምክርቤት አባላት እና በሀገር ውስጥና በውጪ ለምትገኙ አባለትና ደጋፊዎች እንተወዋለን፡፡

ለመሆኑ እነዚህ ሰዎች ስልጣን የሚያጋሩት መቼ ነው ? ወይስ መኢአድ ለእነሱ ብቻ የታደለ ሰማያዊ መናነው?

ይህ በእንዲህ እንዳለ በቅርቡ ፓርቲው ከመንግስት ጋር ያደረገው የምርጫ ስነምግባር ደንብ ውይይት ከላይ ከተጠቀሱትና በተጨማሪ ሌሎች ጥቂት ግለሰቦች ውሳኔና ፍላጎት ብቻ ነው ፡፡

በርግጥ በዲሞክራሲ ሂደት ውስጥ እስካለን ድረስ መወያየትና መነጋገር ዘወትር ሊኖሩ የሚገባቸው ቁልፍ ነገሮች ቢሆኑም በብዙሃን ውሳኔና ፍላጎት መሆን አለበት፡፡

የመኢአድ አመራሮች ግን ወደ ውይይት ሲገቡ የምክርቤት አባላትን እንኳን ማወያየትና ማሳወቅ አልፈለጉም፡፡ እራሳቸው አቦኩት እራሳቸው ጋገሩት፡፡

አሁን ደግሞ ተስማምተናል ብለው በፊርማቸውም ጭምር አጽድቀው ሲያበቁ ደንብ ተጣሰብን ህግ ፈረሰብን በማለት አደስ ድራማ በመጀመር፣ ሲጀምሩ ያላማከሩትን አባል አሁን የቁራ ጩኸት መጮሕ ጀምረውለታል፡፡ ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት ይሏል ይህ አይደል፡፡

ስለዚህ በመኢአድ እንደ ሀገር አቀፍ ድርጅት ሊኖር የሚገባው የፓርቲ ዲሞክርሲ የለውም ፡፡ ፓርቲው የሚዘወረው ጥቂት በሆኑ በጎጠኝነትና በጥቅም በተሳሰሩ ሰዎች በመሆኑ በፓርቲው ውስጥ ሰፍኖ የሚታየው የፓርቲ ዲሞከራሲ ሳይሆን የጥቂት ግለሰቦች አምባገነንነት ነው ፡፡ ፈላጭ ቆራጭነቱ በአንባ ገነኖች እጅ ላይ ብቻ በመሆኑ አባላት ሁኑ የሚባሉትን ከመሆን ውጪ የፓርቲ ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም ሊያደርጉት የሚችሉት አንዳች ነገር የለም ፡፡

ስለሆነም በፓርቲው ውስጥ ዓባላትን መብት በመንፈግ ዲሞክራሲያዊ መብትን የሚረግጥ የፓርቲ አማራር እንዴት ስለሀገርና ስለህዝብ ቆሞ ሊከራከር ይችላል? በፓርቲው ውስጥ ፍትህን ያዛባ አመራር እንዴት ፍትህ ይከበር ብሎ በህዝብ ፊት ይቆማል?

ጎጠኝነትና ወንዘኝነት የተጠናወተው አመራር እንዴት ህብረ ብሔራዊነትን ሊሰብክ ይችላል ? በአጠቃላይ የመኢአድ አምባገነን መሪዎች የስልጣን ጥማቸውን ለማርካት በሚያደርጉት ሂደት ሁሉ በተለያየ መንገድና ሁኔታ መስዋዕትነት ለከፈለ አባል ደንታ ሳይኖራቸው ስለሰብአዊ መብት በአደባባይ እንዴት ሊሟገቱ ይችላሉ ?

በሀገር ደረጃ ፈላጭ ቆራጭ መሆን ቢያቅተን እንኳን በፓርቲያችን እንዳሻን እንሁን የሚሉት እነዚህ አመራሮች ነገ ስልጣን ቢይዙ አገር ሊያለሙ ወይስ ሊያጠፉ ?

ዛሬ የበሬ ግንባር የምታክልን ግቢ መምራት ያቃታቸው አንጂነር ሀይሉ ሻወል አገር እንዲመሩ ቢሰጣቸው ምን ያደርጉ ይሆን? ምንስ ይፈጠር ይሆን? ይህን ሕዝብ እራሱ ይፍረደው እንላለን፡፡ ስለዚህ በመኢአድ ውስጥ እየተካሄደ ያለው የጌታና የሎሌ ስርዓትና አካሄድ ለዚህ ዘመን አስተሳሰብ የማይመጥን በመሆኑ አጥብቀን እንቃወማለን፡፡

ዛሬ ይህን ይፋ የሆነ መግለጫ ለማውጣት የተገደድነው ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት ችግሮች መፍትሄ እንዲያገኙ ለፓርቲው ፕሪዝደንት ለኢንጂነር ሀይሉ ሻወል በቃልና በደብዳቤ ከቅንጅት መበታተን ማግስት ጀምሮ በተደጋጋሚ ብንጠይቅም መፍትሄ ሊሰጡ ባለመቻላቸውና ይልቁንም ሀሳባችንን ከምንም መቁጥር ባለመፈለጋቸው መግለጫውን ለመስጠት ተገደናል፡፡

ስለሆነም ለአንድ ጊዜም እንኳን አስካሁን ድረስ ተስብስቦ የማያውቀው የመኢአድ የላዕላይ ምክር ቤት ይህንን አምባ ገነን አመራር ህጋዊ በሆነ መንገድ ስብሰባ እንዲያደርግና ከዚህ በላይ ለተዘረዘሩ ችግሮች ሁሉ መፍትሄ ለማምጣት ስንል እና ተጽእኖ እንዲፈጥር በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም እናሳስባለን፡፡

በመጨረሻም የእነዚህ የስነ- ምግበር እና ብልሹ አሰራርን ችግር በመዘርዘርና በማስረጃ በማስደገፍ ለወደፊት ይፋ የምናደርግ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

እናመሰግናለን

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ


ቀን

ይድረስ ለክቡራን ወገኖቻችን

   1. ለፕሮፊሰር ጌታቸው ሀይሌ
   2. ለፕሮፊሰር ጋሻው
   3. ለዶ/ር አምባቸው
   4. ለዶ/ር ዘርጋባቸው
   5. ለአቶ አስራት
   6. ለወ/ሮ ሙሊን አንዳርጋቸው

ውድ ወገኖቻችን እንደምን አላችሁ እናንተ የዚህች አገራችን ኢትዮጵያ ብርቅ ልጆች በሀገራችሁ ላይ በዜግነታችሁ እና በሞያችሁ ተከብራችሁ ለወገኖቻችሁና ለቤተሰቦቻችሁ ጋሻ መከታ በመሆን ያላችሁን እውቀት ሁሉ በማበርከት እትብታችሁ በተቀበረባት ምድር እንዳትኖሩ ካደረጋችሁ ጉዳይ የመጀመሪያውና ዋናው የሀገራችን የፖለቲካ ምስቅልቅል ሁኔታ መሆኑ ለእናንተ መንገር ለቀባሪ የማርዳት ያህል ነው ፡፡

ፖለቲካው ሲነሳ ደግሞ በየወቅቱ እግር በእግር እየተተኩ ቅንነት በጎደለው መንገድ ፖለቲካውን የሚያሽከረክሩ ክፉ የሆኑ የዚህችው አገር ገዢዎች መነሳታቸው የሁልጊዜ ክስተት ሆኖል ፡፡ በአሁኑ ወቅት ባለንበት ተጨባጭ ነባራዊ ሁኔታ የተሸለና መልካም ሊባል የሚችል ስርኣት ያመጣል ያልነው ተስፋ የጣልንበት ብዙዎቻችን ብዙ መስዋዕትነት የከፈልንበት እየከፈልንም የምንገኝበት ፓርቲያችን የመላው ኢትዮጵያ እንድነት ድርጅት ( መኢአድ) ባመራሮቹ አምባገነናዊ ባህሪና ፍትህ አልበኝነት ምክንያት ችግር ውስጥ መሆኑን በዚህ የመረጃ ዘመን በጨረፍታም ቢሆን ስለመስማታችሁ ጥርጥር የለንም፡፡

በቅርቡ የተደረገውን እንኳን ለመጥቀስ ያህል ካባላቱ እውቅናና ስምምነት ውጪ ከገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ ጋር የተደረጉት የእጅ መንሻ ድርድር ጥሩና በቂ ማስረጃ ነው፡፡ ይህም በመደረጉ አባላትም ደጋፊዎችም በነዚህ አመራሮች ከፍተኛ ጥርጣሬና ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ገብተዋል፡፡ እነዚህ አምባ ገነንና የጎጠኝነት ባሕሪ በእጅጉ የተጠናወታቸው የመኢአድ መሪዎች እየሰሩ ያሉት እናንተ ለትግሉ ካላችሁ ፍቅር የተነሳ ከልጆቻችሁ ጉሮሮና ከኑሮአችሁ እየቀነሳችሁ በምትልኩት ገንዘብ የግላቸውን ኑሮና ሰብዕና ከመገንባት ባለፈ ለትግሉና ለሀገሪቷ ማሰብ ካቆሙ በጣም ቆይተዋል፡፡

በመሆኑም እናንተ ከመግቢያው ላይ ስማችሁ የተገለጸው ክቡራን ወገኖቻችን ከመኢአድ ሊቀመንበር ኢንጂነር ሀይሉ ሻዎል ሰ ሠዓትን ጠብቀው ገንዘብ አሰባስባችሁ ላኩልኝ ብለው ደብዳቤ እንዳጻፉላችሁ የመረጃ ዘመን በመሆኑ አረጋግጠናል፡፡

ይህ ጥያቄና ግብዣ ደግሞ ለፓርቲው ከማሰብና ለዲሞክራሲያዊው ትግል ግንባታ ታስቦ ሳይሆን በዚህ የምርጫ ግርግር የገንዘብ ጥማቸውን ከግብረአበሮቻቸው ጋር ዛሬም እንደትናንቱ ለመወጣት የታለመ ታርጌት በመሆኑ የግለሰቦች ኑሮ መገንቢያ እንድትሆኑ አንፈቅድም ይልቁንም እንዳታደርጉት በኢትዮጵያ ህዝብ ስም እንጠይቃለን፡፡

ይልቁንም እስኪ የመኢአድ መሪዎች ምን እየሰሩ እንዳሉ ምን ደረጃ ላይ ናቸው በማለት የበለጠ መረጃ ለማግኘት ሞክሩ፡፡ በእውነቱ ከሆነ መኢአድ የተለበለበ ግንድ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ይኸውም ለፍትህ ለእኩልነትና ለነፃነት ወዘተ በዘመናዊና በተሻለ ሁኔታና መንገድ ሲታገሉ የነበሩ አባላት በሙሉ ያለምክንያት ከፓርቲው እንዲወገዱ ተደርጎል ፡፡ በመኢአድ አመራሮች የተወገደ ደግሞ ይግባኝ የሚጠየቅበትና አቤት የሚባልበት መንገድ ፈጽሞ የለም፡፡

በዚህ ምክንያት ከፓርቲው እንዳይደርሱ የተደረጉ አባላት ለምሳሌ በስራ አስፈጻሚ ደረጃ የነበሩ 5 ሰዎች ቀጠና አስተባባሪ የነበሩ 2 ሰዎች የአዲስ አበባ ወጣቶች 180 ዓባላት ያሉት ምክር ቤት ስራ አስፈጻሚውን ጨምሮ በሙሉ እንዲፈርስ ተደርጎል ፡፡ የዞን ፣የወረዳና የክፍለ ከተማ አመራር አባላት ቁጥርእማ ባለቤቱ ይቁጠረው ባጭሩ የትየሌሌ ነው፡፡

ታዲያ የመኢአድ አመራሮች የሚሰሩትን ግፍ በእውቀትና በእድሚ የሚሻሉትን ሰዎች በማስወጣት ስልጣኑን ሁሉ በሞኖፖል ይዘውት ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል ሻለቃ ጌታቸው መንግስቴ የያዙትን ኃላፊነት ስንመለከት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል፣ ምክትል ፕሪዘደንት፣ የምስራቅ ቀጠና ኃላፊ፣ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ፣ የድርጅትና የምርጫ ጉዳዩች ኃላፊ፣ የአንድነት ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ፣የኢዲቶሪያል ቦርድ ሰብሳቢ በመሆን ሰብስበው ይዘውታል፡፡ እኒህ ሰው እየሰሩ ነው ወይስ እየተጫወቱበት ፍርዱን ለናንተው እንተዋለን፡፡ የሚገርመው ደግሞ በዚህ ሁሉ ኃላፊነት ደሞዝና አበል የሚከፈላቸው መሆኑ ነው፡፡ ታዲያ ለነዚ ሰዎች ዛሬም እንደገና ገንዘብ ሰጥተን ጡንቻቸውን እናሳብጠው ለዓብነት ያህል እሳቸውን ጠቀስን እንጂ የዚህ መሰል በረከት ተቋዳሾች ብዞዎች ናቸው ፡፡

በዚህ ምክንያት የመኢአድ የገንዘብ አጠቃቀም ስርዓት ግልጽነትና ተጠያቂነት የሌለው ነው፡፡ መኖር የሚገባው የኦዲትና ኢንስፒክሽን ተቋም እስካሁን ድረስ የሌለው መሆኑነው፡፡

መኢአድን የሚያክል ፓርቲ ገንዘብ ያዡ እንኳን በቅጡ 8ኛ ክፍልን ያጠናቀቀ አይደለም ለነሱ እንዲያመቻቸው ሲባል ብቻ የሰፈራቸውን ሰው አስገብተው ቀልድ አይሉት ፊዝ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እየተጫወቱበት ይገኛሉ ፡፡

በአጠቃላይ የመኢአድን አመራሮች ችግር በአንድ ጊዜ ዘርዝሮ ለመጨረስ አይቻልም፡፡ በእውነቱ ጊዜም አይበቃም፡፡

ስለዚህ ገንዘብ አሰባሰባችሁ እንድትልኩላቸው የተጠየቃችሁ ውድ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን ይህን አስቸጋሪ ጉዳይ በሚገባ እንድታጤኑት እና በተለያየ ሁኔታ ከልብ እንድታስቡበት በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም እንጠይቃለን፡፡ ማን ያርዳ የቀበረ ማን ይናገር የነበረ ነውና እውነቱን ሳንጨምር ሳንቀንስ እየነገርናችሁ ነው፡፡

ይሁን እንጂ የእኛ እምነት ፈጽሞ ይቋረጥ አይደለም ቢያንስ የላዕላይ ምክር ቤቱ ተሰብስቦ በሚደርስበት ሁለንተናዊ ጭብጥ መሰረት ይከናወን እንላለን ፡፡ ግ


posted on 0 Comments · 5933 Reads · Print
Comments
No Comments have been Posted.
Post Comment
Please Login to Post a Comment.
Ratings
Rating is available to Members only.

Please login or register to vote.

No Ratings have been Posted.
Special Links

Login
Username

PasswordNot a member yet?
Click here to register.

Forgotten your password?
Request a new one here.
Latest Articles
Ethiopia(ጋ&#48...
Manipulating Aid
An Ethiopian Scholar...
Somali Investment in...
Message from Maakelawi
Search

Enter Keywords: