Enter Keywords: Articles News Forum Posts Downloads Web Links Members
የትኛው ባል ያግባት?
ባሩድ ጥይት ጮሆ- ጠመንጃው ተባርቆ
ዱላ ተሰንዝሮ- ዱላ ተመክቶ
አንዱ ራስ አድኖ- ሌላው ተፈንክቶ
ፈሪውም በርግጎ- ዘራፍ ባዩ ገፍቶ
የተረፈው ተርፎ- የወደቀው ውድቆ
ማን ነው የሚወስዳት-ያችን ቆንጆ ከቶ?
ሽማግሌ ልኮ- ጨዋ የጨዋ ልጅ
ወይስ ዘራፍ ባዩ- ጀግና የጀግና ልጅ
የትኛው ነው ባሏ- የትኛው ነው እሚበጅ?
እስኪ ሰፈር ይስማ- ጠቢባን ጉባዔ
ሸኮች ድዋ አድርጉ- ካህናት ሱባዔ
“እጣ-ዮሴፍ” ይውጣ-ለሁለቱ ወንዶች
ቆንጆን ለሚያገባት- ለሚሆነን አማች።
ፍርዱን ህዝቡ ይፍረድ- ወንዶቹም ይጣሩ
እጣ እስኪወጣለት- የሚሆናት ባሉ
ግን እስከዚያው ድረስ- ለእኔ ለእኔ አይበሉ!